Site icon ETHIO12.COM

ኡጋንዳ ፀረ-ኢትዮጵያ ለሆኑ ሃይሎች ከለላና ድጋፍ እንደማታደርግ አስታወቀች፤ የሚወራው ሃሰት ነው አለች

ኡጋንዳ ፀረ-ኢትዮጵያ ለሆኑ ሃይሎች ከለላና ድጋፍ እንደማታደርግ አስታወቀች፤ የሚወራው ሃሰት መሆኑንንም አስታውቃለች። ሰሞኑንን የመከላከያ ሚኒስትሩ በቲውተር ገጻቸው ዓለም ስለዩክሬን ብቻ እንደሚጮህ ጠቅሰው “ወንድሞቻችን” ላሉዋቸው የትሀንግ ሃይሎች ያላቸውን ስሜትና ድጋፍ ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ፣ የተለያዩ መረጃዎች ይፋ በመሆናቸው የኡጋንዳ የመከላከያ ባለስልጣናት አዲስ አበባ ገብተዋል።

“የኢትዮጵያ እና የኡጋንዳ የመከላከያ ኃላፊዎች በአዲስ አበባ ውይይት አካሄዱ” በሚል የመንግስት መገናኛዎች እንዳሉት ኡጋንዳ ” ኢትዮጵያ የአፍሪካ እናት ናት” ሲሉ የሚወራው ሁሉ ሃሰት ነው።

የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከኡጋንዳው የመከላከያ ሚኒስትር ጋር በሁለቱ አገሮች ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው ይህ የተሰማው። ዜናው ስብሰባው መደረጉን እንጂ ኢትዮጵያ ጥሪ ስለማቅረቧ ወይም ኡጋንዳ ስብሰባውን ስለመጠየቋ አላብራራም።

በዜናው ሁለቱ አገሮች የመከላከያ ዘርፍ ስምምነት ያለበት ደረጃ ላይ መክረዋል። በቀጣይ ስምምነቱን ለማደስ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ ሥምምነቱን የማደስ ሥራ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እንዲፈፀም ተገልጸዋል።

በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘገብ ስለነበረው አሸባሪው የሕወሓት ቡድን የሥልጠናና ሌሎች ድጋፎችን በኡጋንዳ አማካኝነት እገዛ እያገኘ ነው የሚለውን ወሬ የኡጋንዳ መከላከያ ሚኒስትር ፈፅሞ ከዕውነት የራቀ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትሩ ሀገራቸው ኢትዮጵያን የአፍሪካ እናት አድርጋ እንደምትመለከታትና ማንኛውም ፀረ-ኢትዮጵያ የሆነ ኃይል በኡጋንዳ ለመንቀሳቀስ ፈፅሞ እንደማይፈቀድለት ተናግረዋል።

በኢትዮጵያና በኡጋንዳ መካከል ያለውን የረዥም ጊዜ የጠበቀ ግንኙነት ለማደፍረስ እየሰሩ በመሆኑ ከእነዚህ አፍራሽ ኃይሎች መጠንቀቅ እንደሚገባ ሚኒስትሩ ማሳሰባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በተመሳሳይ ዜና አናሳ ብሄር ወክለው ኡጋንዳን እየገዙ ያሉት ሙሴቪኒ በቅርቡ የሱዳን አይነት ቀውስ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል እየተነገረ ነው። መቀመጫቸውን ደቡብ ሱዳን ያደረጉ አንጋቾችን ጠቅሰው ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ወገኖች እንደሚሉት ሙሴቪኒ አሁን መጀመሩት ኢትዮጵያ ላይ የማደም ተግባር ከቀጠሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ችግር ሊገጥማቸው ይችላል። ለዚህም ይመስላል የሙሴቪኒ ልጅ የተባሉት የአገሪቱ የመከላከያ አዛዥ የቀድሞውን ቲውተራቸውን በሚጣላ መልኩ ቅስቀሳቸውን ቀይረው “ኢትዮጵያ” እያሉ ነው።

የሙሴቪኒ መንግስት ከአሜሪካ 200 ሚሊዮን፣ ከግብጻ ደግሞ ስልሳ ሚልዮን በመቀበል በስድስት የማሰልጠኛ ጣቢያዎች ስማቸውና ማእረጋቸው በተገለጸ የዩጋንዳ የጦር መኮንኖች የትህነግና ተባባሪዎቻቸው ሃይሎች እየሰለጠኑ እንደሆነ የደህንነት ምንጮቻቸውን በመጥቀስ የማህበራዊ አውድ አንቂዎች መረጃ ማሰራጨታቸው ይታወሳል።

Exit mobile version