Site icon ETHIO12.COM

በሕግ ማስከበር ዘመቻ ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ዋሉ

ሰሞኑን በተካሄደ የሕግ ማስከበር ዘመቻ በተለያዩ ወንጀሎች የተጠረጠሩ ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአማራ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡ ቢሮው የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። የቢሮው ኃላፊ አቶ ዳሳለኝ ጣሰው በሰጡት መግለጫ÷ መንግሥት የክልሉን ዘላቂ ሰላም የማስጠበቅ ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

እስካሁን ድረስ በተሰራው የህግ ማስከበር ሥራ በተለያዩ ወንጀሎች የተጠረጠሩ ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል ነው ያሉት።

ከዚህ ውስጥ ከ40 በላይ የሚሆኑት በፍርድ ቤት ተፈርዶባቸው የነበሩ እንደሆኑ ጠቅሰው፥ 210 በነፍስ ግድያ የተጠረጠሩ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡ አሁን ላይ ሕገ ወጦችን ለመያዝ ከሚደረግ ሥራ ውጭ ክልሉ አስተማማኝ ሰላም ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። መንግሥት የክልሉን ዘላቂ ሰላም የማስጠበቅ ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኃላፊው በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡ ትክክለኛውን የፋኖ ስም የማይወክሉ፣ በፋኖ ስም ተደራጅተው በሕዝብ ላይ የተለያዩ ሕገ ወጥ ድርጊት የሚፈጽሙ ቡድኖችን መንግሥት እንደማይታገስም አቶ ደሳለኝ ገልጸዋል። ትክክለኛ የፋኖ አባላትን በመንግሥት መዋቅር ሥር በማድረግ እንዲሠሩ እየተደረገ መሆኑንም ኃላፊው አስታውቀዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version