Site icon ETHIO12.COM

ቢቢሲ ዜና ቀየረ፣የኦባሳንጆ መቀለ መግባት ከጠ.ሚ አብይ የናይጀሪያ ቆይታ ጋር አያያዘ

በኤርትራና በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር መካከል ተደረገ የተባለውን የአንድ ወገን ዜና የዘገበበትን አውድ መቀየሩን ቢቢሲ አስታውቆ ዜናውን አሻሻለ። የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ናይጄሪያዊው ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ትግራይ ክልል እንደሚገኙ አቶ ጌታቸው በቲውተር ገጻቸው ያሰፈሩትን ምስል ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። በዘገባውም በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲናፈስ የነበረውን ትክክለኛ ምንጭ የሌለው መረጃ በመሽረፍ የኦባሳንጆን መቀለ መሄድ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የናይጀሪያ ጉብኝት ጋር አገናኝቷል።

በኤርትራና በይትህነግ መካከል ጦርነት መካሄዱን፣ በጦርነቱም አቶ ጌታቸው እንዳሉት ትህነግ ድል እንደቀናው የዘገበውን ዜና በኤርትራ ቆስቋሽነት እንደተጀመረ ሮይተርስን በመጥቀስ አናቱን የቀየረው ቢቢሲ፣ በድጋሚ አቶ ጌታቸው “ከቀጠናዊ ጉዳዮች ጋር ለመምከር ዛሬ ፕሬዝደንት ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የአፍሪካ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሳንጆን ተቀብለዋል” ከማለት ውጪ ምንም እንዳላሉ ያመለከተው የቢቢሲ ዜና የኦባሳንጆን የመቀለ መገኘት ማስረጃ ሳያቀርብ መላምቱን አኑሯል።



የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ” ዓላማው ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማጋጨት የታሰበ ትንኮሳ ነው” በማለት ምኞቱ ሊሳካ እንደማይችል ከማስታወቃቸው በፊት፣ ቢቢሲም ዜናውን ከማሻሻሉና የኦባሳንጆን የመቀለ ቆይታ ከማስታወቁ አንድ ቀን በፊት በስፋት ኤርትራና ኢትዮጵያን የሚያጋጭ የፈጠራ ዜና ጭምሮ ባንኮችን፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትንና የጸጥታ ተቋማት ላይ ያነጣጠረ የሃሰት ዘመቻ እንደሚከፈት በማህበራዊ ገጽ “አጋሩት” በሚል ተበትኖ ነበር።

Exit mobile version