ETHIO12.COM

የስንዴ አብዮት!! ኦባሳንጆ [ ኢትዮጵያ ልማት ላይ ነች] ሲሉ መመስከራቸው ብስጭት ፈጠረ

የተባበሩት መንግስታት ከአስራ አምስት ጊዜ ላላነሰ ስብሰባ የተቀመጠለት የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር መቀመጫ የሆነውን መቀለን ረግጠው በተመለሱ ማግስት ባሌ ሲናና ወረዳ መታየታቸው ብስጭት መፍተሩ ተሰማ። ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ምሳሌ የሚሆን ልማት ላይ መሆኗን መመስከራቸው የስንዴን አብዮት ጉልበት ያሳየ ነው ተብሏል።

ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስር አብይ አህመድ በመሩት “ጉብኝት” የቀድሞው የናይጄሪያው ፕሬዝደንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ በሲናና ወረዳ በ3 ሺህ 200 ሔክታር መሬት ላይ በክላስተር የለማውን የሥንዴ ማሳ መጎብነታቸው የተዘገበው በመንግስት መገናኛዎች ነው። የአፍሪካ ልማት ባንክና የዓለም ባንክ ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃለ የገቡለትን የስንዴ እርሻ ኦባሳንጆ ” ለአፍሪካ ምሳሌ የሚሆን” ሲሉ ምስክርነታቸውን አሰምተዋል።



የስንዴ ፖለቲካ አስቀድሞ የገባቸው አብይ አሕመድ በቅርቡ ለፓርላማ ” ስንዴ ኤክስፖርት ማድረግ እንጀምራለን” በሚል ሲናገሩ ማታ ማታ “የዛሬ” እያሉ የሚተቹ ሲሳለቁባቸው ነበር። ከተቅላይ ሚኒስትሩ እግር እገር ስር እየተከተሉ ስራቸውን ሊያቆሽሹ የሚሞክሩትን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማታ የሚጮሁ እንቁራሪቶች ብዙ እንደሚመስሉ፤ ግን ሲያጠምዷቸው ከሶስት እንደማይበልጡ የሚናገረውን ምሳሌ ጠቅሰውላቸው እንደነበር አይዘነጋም።

“ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነች የሚገኘው ስራ አበረታችና ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ተሞክሮ መሆን የሚችል ተግባር ነው” ሲሉ ምስክረነታቸውን እዛው ማሳው ላይ ሆነው የሰጡትይ አደራዳሪ፣ “ይህን ማለታቸው ከድርድሩ ጋር ምን ያገናኘዋል” በሚል ቁጣቸውን የገለጹባቸው ድምጻቸውን ያሰሙት ወዲያው ነው።

ስለጀመሩት ድርድር ልክ ዶክተር ለገሰና አምባሳደር ዲና እንዳሉት የጦርነቱ ሁኔታ መሻሻሉን፣ ሰብአዊ እርዳታ በብዛት መግባቱን፣ በጥቅሉ መሻሻል መታየቱንና ይህን መሻሻል ወደ ሚጸና የተኩስ አቁም ስምምነት ለማሸጋገር እንደሚተጉ፣ ነገር ግን ጊዜ እንደሚወስድ ከመግለጽ ውጪ ሌላ የተለየ አስተያየት አልሰጡም። ባንክና ኤሌክትሪክ መስለ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ ቀደም ሲል ጀምሮ ሲሰማ የነበረውን ከመሰረታዊ መግባባት በሁዋላ ሊተገበር የሚችል አሳብ በድጋሚ ገልጸዋል። ኦባሳንጆ ለቢቢሲ ይህን ብለው ሲያበቁ በስንዴ ማሳ ውስጥ የአገሪቱ የደህንነት ሹም ባሉበት መታየታቸው ” በአፍሪቃ ቀነድ ዙሪያ መክረናል” ላሉት ክፍሎች በሽታ እንደሆነ ተሰምቷል።

“የአፍሪካ ሀገራት ለግብርናው ዘርፍ ትኩረት ሰጥተው ከሰሩ የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥ ባሻገር ምርታቸውን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ኢኮኖሚያቸውን ሊያሻሽሉ እንደሚችሉም ይህ ምስክር ነው” ሲሉ ለአገር ውስጥ ሚዲያዎች ያስታወቁት ኦባሳንጆ፣ ይህ አስተያየታቸው ከተሾሙበት ሃላፊነት የስራ ድርሻ ጋር አንዳችም ግንኙነት እንደሌለው ጠቅሰው ነቀፌታ ሰንዝረዋል። ትህነግም ደስተኛ እንዳልሆነ ቢሰማም በኦፊሳል ኦባሳንጆ ማሳ ጎብኝተው ” በሶፍ ኦማር ዋሻ ውስጥ ከቀረጻና ሳተላይት እይታ ውጪ ሆነው መሜስጠራቸው ሴራ ነው” ሲል አልተሰማም።

አፍሪካ በምግብ ምርት ራሷን ትችላለች። ኢትዮጵያን ተመልከቱ የስንዴ ምርቷን በታላቅ እመርታ ወደ 2.6 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን አሳድጋዋለች። በሚቀጥሉት ጥቂት አመታት ኢትዮጵያ ለጎረቤቶቿ ስንዴ ኤክስፖርት የምታደርግ ሀገር እንደምትሆን እርግጠኞች ነን። የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያ ግብርና እመርታ ደጋፊ በመሆኑ ኩራት ይሰማዋል።
አኪንውሚ አዲሳን የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት

በ42 ሺህ 901 ሔክታር መሬት ላይ ተንጣሉ እስክስታ የሚወርደውን የስንዴ ነዶ ሲጎበኙ ” የደህንነት አለቃው አቶ ተመስገን ምን ይሰራሉ? ስንዴና እሳቸውን ምን አገናኛቸው” ሲሉ የጠየቁ ነገሩ ሌላ እንደሆነ፣ ለዓለም እንዲተላለፍ የተፈለገው አሳብና ዜናም የተለየ እንደሆነ ይገምታሉ።

ኦባሳንጆ በተሾሙበት የስልጣን ማዕቀፍ መቀለ እንደሆኑ በተገለጸ ማግስት ከኢትዮጵያ ባለስልጣናትና የደህንነት ሹም ጋር ማሳ እየጎበኙ መነጋገራቸው በትህነግ ላይ እየላላ የሄደ ጉዳይ መኖሩን እንደሚያሳይም የገለጹ አልታጡም። በተቃራኒ ግን ትህነግ ገና ከጅምሩ ” አልጣሙኝም” ያላቸውን ሰው ያወግዛል የሚል ግምት የሰጡ አሉ። እነዚህ ክፍሎች የቀድሞውን የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት “ቺምፓንዚ” ሲሉ የትህነግ ደጋፊዎች መሳደባቸውንም ያስታውሳሉ።

የአፍሪካና የዓለም ባንክ አይናቸውን እንዳጠገበው የመሰከሩለት የስንዴ እርሻ ይበልጥ ሜካናይዝድ እንዲሆን፣ በሌለኦችም አካባቢዎች እንዲሰፋ ድጋፍ እንደሚያደርጉ በገለጹበት ቅጽበት፣ ኦባሳንጆ ” በኢትዮጵያ ከጦርነቱ ዜና በተለየ በልማት ላይ የሚሰራዉ ስራ ጎልቶ የወጣ ነው” ማለታቸው የአብይን መንገድ ስልትና ስሌት ሲረግሙ ለነበሩ ራስ ምታት፣ ለአድናቂዎቻቸው ደግሞ ” ልክ ነኝ” የሚል ምላሽ የሚያሰጥ ሆኗል።

Exit mobile version