Site icon ETHIO12.COM

ዲያስፖራው 3.3 ቢልዮን ዶላር በህጋዊ መንገድ ወደ አገሩ አሰገባ፤ በ97.6 ቢልዮን ብር ኢንቨስትመንት ተሳተፉ

ዶያስፖራው ብሩን በህገወጥ መንገድ በመላክ ኢትዮጵያን ለማጥፋትና ኢኮኖሚያዋን ለሰባበር የሚተጉትን ሳያውቅ እየደገፈ እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲገለጽ እንደነበር ይታወሳል። ይህንኑ አካሄድ መከተል አገር አልባ እንደሚያደርግ በማስረዳት በተደረገ የማነቃቂያ ስራና ከወረራው ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ግንዛቤ በርካታ የጊያስፖራ አባላት ኢትዮጵያዊነታቸውን አሳይተዋል።

ዛሬ አዲስ ዘመን እንዳስታወቀው በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዘጠኝ ወራት ውስጥ ሶስት ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ዶላር ወደ አገር ቤት መላካቸውን የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ መናገሩን ሪፖርት አድርጓል። በተከፈቱ የውጭ አካውንቶችም 6 ሺ የሚጠጉ የዲያስፖራ አባላት ከአምስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ተቀማጭ ማድረጋቸውም ተመልክቷል።

የኤጀንሲው የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን ግርማ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በዲያስፖራው አማካኝነት ከሀምሌ 1 ቀን 2013 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ሶስት ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ዶላር ወደ አገር ቤት ተልኳል ።

የውጭ ምንዛሬ ፍሰት እንዲጨምር ዲያስፖራው በሕጋዊ መንገድ ገንዘቡን ወደ አገር ቤት እንዲልክ ክትትልና ድጋፍ መደረጉን ያመላከቱት አቶ ወንድወሰን እስከ ሶስተኛው ሩብ አመት ሶስት ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ዶላር ወደ አገር ቤት መላኩን ተናግረዋል ።

Get new recipes delivered to your inbo.

አቶ ወንድወሰን 5 ሺህ 965 የዲያስፖራ አባላት የውጭ ምንዛሬ አካውንቶችን በመክፈት ከአምስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ተቀማጭ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

የዲያስፖራ አባላት በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በቱሪዝም እንዲሳተፉ የተለያዩ ድጋፎችን መስጠታቸውን የገለጹት አቶ ወንድወሰን፤ ይህንንም በተመለከተ 97 ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሳተፍ ፍላጎት ላላቸው 1ሺህ 489 ዲያስፖራ አባላት የተለያዩ ድጋፎች መሰጠታቸውንም ገልጸዋል ።

በማህበር ተደራጅተው ሪል ስቴት ለመገንባት 7 ሚሊዮን ዶላር የቆጠቡና ወደ ስራ የገቡ 120 የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በጅማ ከተማ የግንባታ ቦታ መረከባቸውንም አቶ ወንድወሰን አመላክተዋል ።

በአገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍና የተጎዱ መሰረተ ልማቶች መልሶ ለማቋቋም 300 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍና የተጎዱ መሰረተ-ልማቶች መልሶ ለመገንባት 1 ነጥብ 14 ቢሊዮን ብር በዓይነትና በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ መሰብሰቡን አቶ ወንድወሰን ተናግረዋል ።

አቶ ወንድወሰን የሀገር ሉአላዊነትን ለማስከበር ዘብ ለቆመው የመከላከያ ኃይላችን እና ለህልውና ዘመቻ ከ109 ሚሊዮን 813 ሺ ብር በላይ ማሰባሰብ መቻሉንም ተናግረዋል ።

አቶ ወንድወሰን ግብረ-ሰናይ ድርጅቶችን፤ የዲያስፖራ ማህበራትን፣ ሙያ ተኮር በጎ አድራጎት ድርጅቶችንና ታዋቂ ግለሰቦችን በማስተባበር 32 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በመሰብሰብ ለበጎ አገልግሎት እንደዋለ አዲስ ዘመን ዘግቧል።

Exit mobile version