Site icon ETHIO12.COM

አስራ ሶስት አመት ያልሞላት ህፃን ልጁን የደፈረው አባት በፅኑ እስራት ተቀጣ

የዐቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረዳው ከሆነ ተመስገን ገረመው ጉደታ የተባለው ተከሳሽ ቀኑ፣ ወሩ እና ሰዓቱ በውል በማይታወቅ በ2004 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ልዩ ቦታው ኡራኤል ሰፈር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የራሱ ልጅ የሆነችውን የ10 ዓመት ህጻን እናቷ ስራ በሄደችበት ሰዓት ከህፃኗ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ፈጽሟል፡፡ ይህ ድርጊቱ አልበቃም ብሎ ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ቀኑ፣ ወሩ እና ሰዓቱ በልታወቀ በ2006 ዓ.ም የግል ተበዳይ እናት ለስራ ወደ አረብ ሀገር የሄደች እና ህፃኗ ከአባቷ እናት ጋር እየኖረች እያለ ተከሳሽ ሰክሮ በድንገት ተበዳይ ወደምትኖርበት ቤት በመሄድ ዛሬ ከእኔ ጋር ነው የምናድረው በማለት ወደ እራሱ መኖሪያ ቤት ከወሰዳት በኋላ በድጋሚ አስገድዶ ደፍሯታል፡፡ ተበዳይ ከባድ የሞራል እና የስነ-ልቦና ጉዳት ይደርስባታል በግንቦት 06/2013 ዓ.ምም ጉዳዩ ፖሊስ ዘንድ ይደርሳል፤ እናም ፖሊስ ምርመራ በማካሄድ ግንቦት 18/2013 ዓ.ም መዝገቡን ለዐቃቤ ህግ ያደርሳል፡፡ በጠቅላይ በዐቃቤ ህግ ዘርፍ የቦሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዐቃቤ ሕግም ምርመራ መዝገቡን በተረከበ በ5 ቀናት ውስጥ በግንቦት 25/2013 ዓ.ም ተከሳሽ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 627/4/ሀ/ ስር የተመለከተውን ተላልፏል ሲል በህፃን ልጆች ላይ የሚፈፀም የግብረስጋ ግንኙነት ወንጀል ከሶ ፍርድ ቤት አቅርቦታል፡፡

ተከሳሽ በችሎት ቀርቦ ክሱ ደርሶትና ተነቦለት የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ ”እኔ ድርጊቱን አልፈፀምኩም ጥፋተኛም አይደለሁም ”ሲል ቃሉን ሰጥቷል።

ዐቃቤ ህግ በበኩሉ የተከሳሽን ጥፋተኝነት ለፍርድ ቤቱ ያስረዱልኛል ያላቸውን ዝርዝር ምስክሮችን እና የሰነድ ማስረጃዎችን በበቂ ሁኔታ ለችሎቱ አቅርቦ በማስረዳቱ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ እንዲከላከል ብይን ቢሰጥም ተከሳሽ ማስተባበል ባለመቻሉ የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ 6ኛ ወንጀል ችሎት በተከሳሽ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፏል።

በዚህም መሰረት ተከሳሽ ከዚህ በፊት የጥፋተኝነት ሪከርድ የሌለበት߹ የቤተሰብ አስተዳዳሪ߹ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ እና የጤና እክል ያለበት መሆኑ በድምሩ አራት የቅጣት ማቅለያዎች ተይዘውለት በ15 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል።

Federal general attorney

Exit mobile version