Site icon ETHIO12.COM

አብን የከፍተኛ አመራሮቹን የሥራ መልቀቂያ ውድቅ አደረገ

የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ የከፍተኛ አመራሮቹን የሥራ መልቀቂያ ውድቅ ማድረጉ ተገለጸ።

የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዷል።

በፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር በለጠ ሞላ በኩል ‘‘አሁን ላሉ በርካታ ጉዳዮች ላለፉት 4 ዓመታት በከፍተኛ አመራርነት ያገለገልን አመራሮች ለቀን በአዲስ እንተካ’’ የሚለውን ሀሳብ ፓርቲው ጊዜ ሰጥቶ የተወያየበት መሆኑን የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ጣሂር ሞሀመድ ተናግረዋል።

ሆኖም ሊቀመንበሩ ያቀረቡትን የመልቀቂያ ሀሳብ ማዕከላዊ ኮሚቴው አልተቀበለውም።

‘’አሁን እየታየ ላለው ችግር የመፍትሄ አካል ለመሆንም አዳዲስ አመራሮችን ወደፊት በማምጣት እንተካካ’’ የሚለውን ሀሳብም ፓርቲው ሐምሌ 18/2014 በሚያካሂደው ስብሰባ በጥልቀት እንደሚያየውና እስከዚያም ፓርቲው በትኩረት ስራውን እየሰራ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

እንደ አሚኮ ዘገባ የፓርቲው ውስጣዊ አንድነት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ፓርቲው እንዴት ያያቸዋል የሚል ሀሳብ ከመገናኛ ብዙሀን ሙያተኞች የተነሳላቸው ኃላፊው ፥ ማህበረሰቡ ውስጥ ላሉ ልዩ ልዩ ሃሳቦችና ለድርጅቱም አቅምና ውስጣዊ አንድነት የሚበጁትን ሃሳቦችና ውሳኔዎች የምናሳርፍበት ስብሰባ ሀምሌ 18 ይካሄዳል ብለዋል።

Exit mobile version