Site icon ETHIO12.COM

በተሻለ ጥቅም ለትህነግ ነዳጅ በበርሜል ይሸጋገራል፤ ወልደያና ቆቦ ችግሩ ተባብሷል

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ወልደያና ቆቦን በወረረበት ወቅት ምን እንደፈጸመ የሚያስታውሱ ከዚሁ አካባቢ ነዳጅ በበርሜል ለዚሁ ድርጅት እንደሚሸጋገር መስማት ያስደነግጣል የሚሉ ወገኖች ጥቂት አይደሉም። አማራ ክልል ላይ ከደረሰው ግፍ አንጻር ለጊዚያዊ ጥቅም ተብሎ መልሶ አማራን ለማስመታት ለወራሪውን ሃይል ነዳጅ የሚያሸጋገሩትን ክፍሎች ሕዝብ እንዴት ዝም አለ? የሚለውም ሌላ ጥያቄ ነው። ከሁሉም በላይ ግን የአካባቢው አስተዳደሮችና የጸጥታ መዋቅር “ምን እየሰራ ነው?” የሚለው አሳሳቢ ነው።

ለዳግም ወረራ ዝግጅቱን እንዳተናቀቀ ይፋ ያደረገው ትህነግ በዓለም ዓቀፍ ጫና ነዳጅ እየገባለት እንደሆነ ያስታወሱ፣ ከአማራ ክልል በድብቅ ነዳጅ የሚያሸጋገሩለት መኖራቸው ያከማቸውን ሃይል ለወረራ እንዳሻው እንዲያነቃንቅ ያግዘዋል። ይህ እየታወቀ ቆቦና ወልደያ ያሉ የአስተዳደር አካላት መተኛታቸው እጅግ ፈጣን የሆነ ምላሽ ሊሰተው እንደሚገባ እየተተቆመ ነው።

በወረራው ወቅት ከውስጥ ሆነው የሚያስተኩሱ፣ ሆን ብለው መዋቅር የሚያፈርሱና ህዝብ አካባቢውን ጥሎ እንዲወጣ የሚያዙ አመራሮች ያደረሱት በደል ሳይረሳ፣ በጥቅም ተደልለው ነዳጅ የሚሸጡና የሚያሸጋገሩትን በሙሉ ህዝብ ሊያጋልጣቸው እንደሚገባ ተመልክቷል። ይህ ብቻ ሳይሆን አመራሩና የበታች መዋቅሩ ሊፈተሽ እንደሚገባ በርካቶች በተደጋጋሚ ይናገራሉ።

ትህነግ የአማራውን መሪ ድርጅት ብአዴንን ሲያቋቁም በብዛት ከተተቀሱት አካባቢዎች በሰበሰባቸው ካድሬዎች እንደሆነ የሚያውቁ፣ ትህነግ ታገልኩ በሚልበት ዘመን በተተቀሱት አካባቢዎች ይመሽግና የችግር ጊዜውን ያሳልፍ እንደነበር መረጃው ያላቸው የጸጥታ ሃይሉ ጥብቅ ቁጥጥርና ማጥራት ሊያደርግ እንደሚገባ ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የነዳጅ ኮንትሮባንዱን አስመልክቶ የሚከተለውን አስነብቧል።

ወደሰሜን ኢትዮጵያ በተለይም ወደ ወልዲያና ቆቦ አካባቢ የሚጓጓዝ ከፍተኛ የሕገወጥ ነዳጅ ፍሰት መኖሩን የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ኃይለማርያም በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ወደወልዲያና ቆቦና አካባቢዎች የሚጓጓዘው ሕገወጥ የነዳጅ ዝውውር መጠን እየጨመረ ስለመሆኑ በየጊዜው መረጃዎች ይደርሳቸዋል።

“በሚደርሱን መረጃዎች መሰረት በበርሜል የታሸገ ሕገወጥ ነዳጅ ከኮምቦልቻ ጀምሮ በብዛት ተጭኖ እንደሚሄድ ማወቅ ተችሏል” ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው፤ የነዳጅ ፍሰቱ ወደሰሜን የመጨመሩ ምክንያት ምናልባትም ከአሸባሪው ሕወሓት ጋር ሊገናኝ ይችላል ብለዋል።

“ሁል ጊዜም የተጨማሪ ገበያ ሲኖር ሕገወጥ የነዳጅ ፍሰቱ እንደሚጨምር ይታወቃል” ያሉት አቶ ታደሰ፤ ወደትግራይ ክልል ነዳጅ በብዛት የማይገባበት ሁኔታ ስላለ በኮንትሮባንድ መልክ የማስተላለፍና ከፍተኛ ክፍያ የመቀበል ሁኔታ ሊኖር እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡

ይህ ሁኔታ ለነዳጅ ሕገወጥ ዝውውር አመቺ ሁኔታ ስለሚፈጥር ከአማራ ክልል ቢሮዎችና ከሚመለከታቸው የፌዴራል ተቋማት ጋር የበለጠ ጉዳዩን ማየትና የመፍትሄ እርምጃ ማስቀመጥ እንደሚጠይቅ ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም ወደ ሞያሌና ያቤሎ መስመር የኬንያ ድንበር እንዲሁም በሶማሌ ክልል የድንበር አካባቢዎች ከፍተኛ የሕገወጥ ነዳጅ ፍሰት ይስተዋል እንደነበር ያስታወሱት ዋና ስራ አስፈጻሚው፤ ችግሩን በነዳጅ ኮታ አቅርቦት አሰራር ማስተካከል መቻሉን ገልጸዋል።

አሁን ላይ የሚታዩ ህገወጥ የነዳጅ ፍሰቶችንና ተያያዥ ችግሮችን ለመከላከል ከኮታ አቅርቦት ባለፈ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምንም ማሳደግ እንደሚገባ አቶ ታደሰ ተናግረዋል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር በነዳጅ አመላላሽ ተሽከርካሪዎች ላይ በአስገዳጅነት የእንቅስቃሴ መቆጣጠሪያ (ጂፒኤስ) ቴክኖሎጂ እንዲገጠም የሚያስገድድ መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

ጂፒኤስ ቴክኖሎጂው ከተገጠመ የእያንዳንዱን ነዳጅ ጭነት መስመርና ያረፈበትን ቦታ መከታተል ስለሚቻል ሕገወጥ የነዳጅ ዝውውርን ለመቆጣጠር ይረዳል። በተለይም በውጭ ምንዛሬ ተገዝቶ የገባው ነዳጅ ተመልሶ ከአገር እንዳይወጣ ለመከላከል የቴክኖሎጂው አስፈላጊነት የጎላ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ኃላፊነቱ ነዳጅ ከውጭ አገራት ማስገባት ነው፤ በዚህም መሰረት በዚህ ዓመት 600 ሺህ ሜትሪክ ቶን ቤንዚን፣ 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ናፍጣ እንዲሁም 400 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአውሮፕላን ነዳጅ ቀርቧል።

ዋናው ትልቁ ስራችን ነዳጅ ማቅረብ ነው ያሉት አቶ ታደሰ በዚህ ረገድ አዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የነበረውን የነዳጅ አከፋፋዮች ችግር ለመቀነስ ከነዳጅ ዴፖ እንዲወጣ በማድረግ ችግሩን መቅረፍ ተችሏል ሲሉ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በአማካይ በየቀኑ ከሁለት ነጥብ ሰባት እስከ ሶስት ሚሊዮን ነዳጅ እያሰራጨ መሆኑን አስታውቋል።

በተለያዩ ጊዜያት ወልዲያ ከለተማ ላይ ሕገወጥ ነዳጅ የሚያጓጉዙ ሰዎች ተይዘዋል። ግንቦት ወር ጨመረሻ ላይ በአፋር ክልል በኩል በሕገወጥ መልኩ ወደ ትግራይ ክልል ሲጓጓዝ የነበረ ከአምስት ሺህ ሊትር በላይ የሚገመት ነዳጅ መያዙ የሚታወስ ነው። ችግሩ በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር፣ በሰሜን ጎንደርና በተለያዩ አካባቢዎችም ይስተዋላል።

Exit mobile version