ETHIO12.COM

ባልደራስ የሱዳን ልሳን – የሱዳን የውስጥ ቀውስ ማስተንፈሻ ዜና ያራባል

ባልደራስ ሆይ መንግስትን መቃወም፣ ለስልጣን መሮጥና ኢትዮጵያ ይለያያሉ።

ባልደራሶች! በቀላሉ አትገመቱ! ዜናውን ለሚዲያ ተውት! ባልደራስ በርካታ ጉዳዮችን በፌስቡክ ገፁ ይለጥፋል። በአዲስ አበባ ጉዳይ ብዙ ያከናውናል፣ ይሰራል የተባለው ፓርቲ በተቃራኒ የሚያስገምቱትን ተግባራት መፈጸም መለያው ሆኗል። የተራ የ “አክቲቪስት” መልዕክቶችን እየለቀመ ሲያሰራጭና ሲያራባ ይውላል። ይህ አካሄዳቸው አልረባቸውማና ባልደራሶች ቁመናቸውን ቢያስተካከሉ መልካም ይሆናል።

ሁሉን ተተነው ለምሳሌ ከስር ያለውን ዜና ብቻ መመልከት ይቻላል። የዜናው ዋና ምንጭ ሱዳን ናት። የሱዳን መገናኛ ብዙሃን አገራቸው ውስጥ የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ጥረትና ሩጫ እያደረጉ ነው። የውስጥ ቀውሳቸውን አቅጣጫ ለማሳት ላይ ታች እያሉ ነው።

በቅርቡ ከባድ መሳርያዎችን እየተኮሰ ያለው የሱዳን ሰራዊት የኢትዮጵያን ሰራዊት ቦታ እንዳስለቀቀ አድርገው የሚያወሩትና ዜና የሚረጩት ለዚሁ ዓላማ ነው። እነሱ የሉአላዊነት ጉዳይ አንስተው አቅጣጫ ማስቀየር ፈልገዋል የሚረጩትን ዜና ሮይተርስም ተቀብሎ ይደግምላቸዋል። ባልደራስ ደግሞ ይህን ተቀብሎ የሱዳን ችግር ማብረጃ ዜና አገሩ ላይ ይረጫል።

ባልደራስ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያለው። ኢትዮጵያ ብሎ የሚምላና በባንዲራዋ የሚጠቀለል ድርጅት ነው። ከዚህም በላይ ለታይታ ሲል ያገናቸው የነበሩት ፋኖዎች ሱዳን ድንበር ነው ያሉት። ቢያንስ ለእነሱ ደውሎ ጉዳዩን ማረጋገጥ በቻለ ነበር። ለእነሱም ባይደውል ከሱዳን ጎንደር ያሉ ዕልፍ ምንጮችን ቢጠይቅና ቢያጣራ ይቀርበው ነበር። ማረጋገጥ ይችል ነበር። ይህን አድርጎ ቢሆን ኖሮ እንደዚህ ዓይነት የሞራልና የስብዕና ቅርቃር ውስጥ ባልገባ ነበር።ከሁሉም በላይ ደግሞ ይህን ዜና ተርጉሞ መዘገብ ስራቸውም አለነበረም። ጥሬ የመሆን ችግር ያመጣው ጣጣ ነው።

ባልደራስ የሆነ ያልሆነውን እያጋራ በደጋፊዎቹም ጭምር ከሚገመት ሌላ የድርጅት ስራ ላይ ቢያተኩር ይሻለዋል። ለምሳሌ በዚህ ዜና ጉዳይ መንግስትን ምን እየሆነ ነው ብሎ ቢጠይቅ፣ የአገር ሉአላዊነት የሚያስከብር መንግስት አይደለም ብሎ ቢተች ወዘተ የተገባ ነው። እንዲህ ያለ ዜና ግን ባልደራስን መዘባበቻ ከማድረጉ ውጪ አንዳች አይፈይደለትም።

የግድ ዜና ካልሰራን ካላችሁ ደግሞ የወገን ዜና እንዲህ አይሰራም። ሱዳን ተጨማሪ የኢትዮጵያን መሬት ከያዘች ወረራ ነው የሚሆነው። ወረራ ነው የሚባለው። ወረራም ከሆነ ወረራውን ለማክሸፍ መትጋት እንጂ በዘጋቢነት ተሰልፎ እነሱ ለውስጥ ችግራቸው ማርከሻ የሚረጩትን ወሬ እንዳለ ተቀብሎ እንደ ባዕድ ማዳረስ አይደለም መፍትሄ የሚያመጣው።

ዝግጅት ክፍላችን – ይህ ጽሁፍ የተወሰደው ከጌታቸው ሽፈራው ነው። ጌታቸው ሽፈራው በግርድፍ የጻፈውን መጠነኛ የማስተካከያ ቃላቶችን አክለናል። ዛሬ አምስት ሺህ የሚጠጉ የትህነግ ሰልጣኞች በኡጋንዳ አራት ካምፖች እየሰለለጠኑ ነው። ዛሬ ሱዳንና ትህነግ ታታቂዎቻቸውን በደ ኢትዮጵያ ድንበር እያስጠጉ ነው። ትህነግ ዝግጅቱን ጨርሶ ለውጊያ መዘጋጀቱን፣ አዲስ አበባ ያሉትን ጨምሮ ደጋፊዎቹ ውጊያ እንዲከፈት እያስገደዱት መሆኑን ጠቅሶ ” በቅርብ ቀን” ብሏል። የኡጋንዳውን ኦፕሪሽን ለመምራት አሜሪካ 200 ሚሊዮን ዶላር ሰጥታለች። አሁን የቀረው ኢትዮጵያን ከሰሜን ጀመሮ እስከ ምዕራብ ጫፍ ማጥቃት ነው። ባልደራስ ይህን ዕቅድ ይፋ ለማድረግ የተጀመረውን ዜና ነው ኢትዮጵያዊያን ላይ እያራገበ ያለው። መንግስትን መቃወም፣ ለስልጣን መሮጥና ኢትዮጵያ ይለያያሉ።

Exit mobile version