Site icon ETHIO12.COM

ሱዳን ትሪቡን ያሰራጨው አሳሳች ምስል!

ethiopian and its niberors

CAPTION: Map of the Greater Horn of Africa Region – roughly speaking the IGAD (Intergovernmental Authority on Development) block of nations. Uganda has borders with South Sudan and Kenya)

EthiopiaCheck Fact Check

ሱዳን ትሪቡን የተባለ ድረ-ገጽ በትናንትናው ዕለት ‘Sudanese forces attack Ethiopian troops in Al-Fashaga area’ በሚል ርዕስ ስር ሱዳን በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት መሰንዘሯን የሚያትት ዘገባ ሰርቷል።

ድረ-ገጹ ከዘገባው ጋር የተቃጠሉና ጉዳት የደረሰባቸውን ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች የሚያሳይ ፎቶ ያያዘ ሲሆን በፎቶው ላይ የሚታዩት ተሽከርካሪዎች በትናንትናው ዕለት ሱዳን በሰነዘረችው ጥቃት በረኸት በተባለ መንደር የተጎዱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ንብረቶች እንደሆኑ የሚገልጽ ማብራሪያ ጽፏል።

ከሱዳን ትሪቡን በተጨማሪ በርካታ የሱዳን ሚዲያዎች ይህን ፎቶ ከተመሳሳይ መልዕክት ጋር ሲያሰራጩ ተመልክተናል። የቢቢሲ ሬድዮ በበኩሉ ምስሉን ማረጋገጥ ባይችልም የተቃጠሉ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተሰራጩ እንደሆነ ጠቁሟል።

ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ፎቶው የተነሳው ከ11 ወራት በፊት በትግራይ ክልል፣ ማዕከላዊ ዞን፣ ይጭላ ከተማ አቅራቢያ መሆኑን አረጋግጧል።

ሱዳን ከቀናት በፊት በወታደሮቼ ላይ ግድያ ተፈጽሟል የሚል ክስ ካቀረበች በኋላ አጸፋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሯን የሀገሪቱ ሚዲያዎች በመዘገብ ላይ ሲሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ሱዳን ያቀረበችውን ክስ ውድቅ በማድረግ ሠራዊቱ ግጭቱ በተከሰተበት ስፍራ እንዳልነበርና የኢትዮጵያን ግዛት ዘልቆ የገባው የሱዳን ኃይል ከአካባቢው ሚሊሻዎች ጋር መጋጨቱን መግለጹ ይታወቃል።

ለዚህም ኢትዮጵያ ቼክ የሮይተርስ ጋዜጠኛ ጁሊያ ፓራቪቺኒ እ.አ.አ ሀምሌ 10/2021 ዓ.ም በትግራይ ክልል፣ ማዕከላዊ ዞን፣ በይጭላ ከተማ አቅራቢያ ያነሳችውን ፎቶ ለማነጻጸሪያነት ተጠቅሟል። በንጽጽሩም ሱዳን ትሪቡን ባጋራው ፎቶ የሚታዩ ጉዳት የደረሰባቸው ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ዛፎች ከሮይተርስ ፎቶ ጋር ተመሳሳይ መሆናቸውን አረጋግጧል።

ENA

Exit mobile version