ሱዳን ተጨማሪ ሰራዊት ወደ ኢትዮጵያ ድንበር አስተጋለሁ አለች፤ ሊንዳ ቶማስ የሱዳን መንግስት የተረጋጋ እንዲሆን ሊታገዝ ይገባል ብለዋል

ካርቱም ላይ ከግብጽ ጋር የነበረው ምክክር ካለቀ በሁዋላ የሱዳን የፀጥታና የመከላከያ ምክር ቤት በቅርቡ በድንበር አካባቢ የኢትዮጵያን ወታደራዊ የመከላከያ ሃይሏን አተናክራለች በሚል በምስራቅ ሱዳን ድንበር ያሰማራውን ሃይል ለማጠናከር መወሰኑ ተሰማ። ተጨማሪ ሃይልም ወደ ስፍራው እንደሚልክ ይፋ ሆኗል።

የሱዳን ወታደራዊ ባለሥልጣናት ማክሰኞ ዕለት ከጋዳሬፍ ግዛት ጋር በሚዋሰነው በአማራ ክልል ተጨማሪ የኢትዮጵያ ጦር ተጨማሪ ወታደሮችን ማሰማሩን ለሱዳን ትሪቢዩን አስታወቁ ፡፡

የሱዳንን ወታደራዊ ባለስልጣናት ጠቅሶ ሱዳን ትሪቡን እንደዘገበው ውሳኔው የተወሰነው ባለፈው ሐሙስ በሉዓላዊው ምክር ቤት ኃላፊ አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን በተመራው የፀጥታና የመከላከያ ም / ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ውይይት ከተደረገበት በሁዋላ ነው።

እንደምንክንያት የቀረበው የኢትዮጵያ ሚሊሺያዎች በሱዳን አርሶ አደሮች ላይ ጥቃታቸውን አጠናክረው መቀጠላቸውና የተወሰኑትን ካገቱ በኋላ መሬታቸውን ጥለው እንዲወጡ አስገድደዋል በሚል የአንድ ወገን መረጃ በመጥቀስ ነው ሱዳን ትሪቡን ያስታወቀው።

ሱዳን የአማራ ሚሊሻ የሚለውን ጉዳይ ደጋግማ ብታነሳም ዋናው ጉዳይ ግን ግብጽ ለሰጠቻት የቤት ስራ መነሻ ምክንያት ለመፍጠር እንደሆነ ይታወቃል። በሱዳን ያለው አለመረጋጋት መርገብ እንዳለበት ከወትሮው በተለየ ሊሰራ እንደሚገባ በተመድ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ትግራይን አስመልክቶ ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ተወካዮችና ሌሎች ዓለም ዓቀፍ አካላት ጋር በተካሄደ የጠርጴዛ ዙሪያ ውይይት አንስተዋል።

ሱዳን የያዘችውን አቋም የማይደግፉ ባለስልጣናትና የወታደራዊ መኮንኖች መኖራቸው በሚሰማበት፣ የውስጥ አለመግባባቱና ትርምሱ በገነነበት፣ አመጽ በየቀኑ በሚስተናገድባት፣ የዳርፉር ጉዳይ እያገረሸ በሄደበትና የሱዳን ወደብ ከተማ አካባቢ በአስቸኳይ አዋጅ ስር ባለበት በአሁኑ ወቅት ቶማስ ሊንዳ ሱዳን ልትታገዝ እንደሚገባ አጽንዖት መስጠታቸው አካሄዱን ግልጽ እንደሚያደርገው ባለሙያዎች ወዲያው ነው የተቹት።

በሲኤኔን ጋዜጠኛ መሪነት በተካሄደው ኢትዮጵያን የመደብደብ ስብሰባ ሊንዳ ልክ እንደ ሱዳን ሁሉ የአማራን ስም በመጠቀስ ሲናገሩ ፊታቸው ላይ ከሚታየው ንዴት በላይ ድምጻቸውና ጥሪያቸው አንዳች ልዩ ጫና የመፍጠር ስሜት እንዳላቸው በሚያሳብቅ መልኩ ነበር።

ሊንዳ ብቻ ሳይሆኑ ሳማታን ፓወርም በተመሳሳይ ሱዳን ስለሟን እንድታስጠብቅ ልትረዳ ይገባል በሚል አንስተዋል። ሱዳን ወታደሮቿን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ለማንቀሳቀስ መወሰኗን በይፋ ማስታወቋን ተከትሎ ከኢትዮጵያ በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም። ይሁን እንጂ በድንበር አካባቢ ኢትዮጵያ በቂ ዝግጅት እንዳላትና የህዳሴው ግድብ ዙሪያ ምን ቀልድ እንደሌለ ማስታወቋ፣ አካባቢው ላይ ለሚሞከር ማናቸውም ጥቃት ሙሉ ዝግጅት መኖሩን መግለጿና ሙከራ ለሚያደርጉ ማስጠንቀቂያ መስጠቷ አይዘነጋም። ሱዳን ሰልጥኖ ወደ ቢኒሻንጉል ሊዘልቅ የነበረ ሃይልም በቅርቡ ሙሉ በሙሉ መደምሰሱ ያታወሳል።


Leave a Reply

%d bloggers like this: