Site icon ETHIO12.COM

ብአዴንን ለአማራ ዳግም ማዋለድ – በሲአይኤው ቅምጦች እነ ሻለቃ ዳዊት

ዳግማዊ ኢህዴንን/ብአዴንን በአማራ በኩል ለማዋለድ በእነ ያሬድ ጥበቡ፣ ታምራት ላይኔ እና በሲአይኤው ቅምጥ ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ መሪነት የሚደረገው ጥረትና የአማራን ሕዝብ እረፍት የመንሳት ፕሮጀክት እንቅስቃሴ ዛሬም የቆመ አይደለም። ዳግማዊ ኢህዴንን/ብአዴንን ለመፍጠር የሚንቀሳቀሰው ሃይል በአማራ ስም የሲቪክ ማህበራትን እና የዩትዩብ ሚዲያዎችን በማቋቋም ዲያስፖራውን ለመቆጣጠር ሲያደርግ የነበረው እንቅስቃሴ ከሞላ ገደል አልተሳካለትም ማለት አይቻልም። ከተጨባጩ አገራዊ ቀጠናዊና አለማቀፋዊ ሁኔታ ጋር በማይገናኝ ትንተና እና የተሳሳተ መረጃ ዲያስፖራውን በማደናገር ከመዘወር ባሻገር በሐገር ቤትም የአማራ ሕዝብ ከትናንት የተሻገሩ መሰረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ እንዳያገኙ ለራሳቸው እኩይ አላማ ለመጠቀም ሲደክሙና ሲተጉ ታይተዋል።

ዳግማዊ ኢህዴንን/ብአዴንን ለመፍጠር እንቅስቃሴ ላይ የገባው ይህ የወያኔ ጉዳይ አስፈፃሚ ሃይል ከባሕር ማዶ እስከ ሐገር ቤት በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ የሞቀ እንቅስቃሴ ማጧጧፍ የጀመረው በዋናነት በሕወሓት ጠርናፊነት በመቀሌ የፌደራሊስት ሃይሎች ስብሰባ ላይ በብሔር ከተደራጁ ድርጅቶች መካከል በአማራ ስም የተደራጀው አብን በስብሰባው ላይ ካለመገኘቱ ባሻገር በአገራዊ አጀንዳዎች የሚይዘው አቋም ከፌደራሊስት ሃይሎች ጋር ፈፅሞ የማይታረቅና በአማራ ፖለቲካ ወያኔ አጀንዳውን እንዳይሸጥ እንዳይለውጥ ቀዳዳ ለማሳጣት መሞከሩን ተከትሎ ጎልቶ የታየ ነው።

በመቀሌ የፌደራሊስት ሃይሎች ተሰብስበው ተልዕኮ ተሰጣጥተው የተለያዩ መሆናቸውን ተከትሎ ብዙ ነገሮች ተቀያይረዋል።

በኦሮሞ በኩል የእነ ጃዋሩና በቀለ ገርባው ኦፌኮ በመቀሌው የፌደራሊስት ሃይሎች ከተገኙት አንዱ ነው። በፌደራሊስት ሃይሎች ጠርናፊና አንበል ሕወሓት በጠራው ስብሰባ ላይ ለመካፈል በቀለ ገርባ በመቀሌ ኦፌኮን ወክሎ የተገኘው ለደብረፅዮን ወይም ለጌታቸው ረዳ ትልቅ አክብሮት ወይም መውደድ ስለነበረው ወይም እነሱን ስለፈራ ወይም ትናንት አስረው የሰሩበትን ግፍ ረስቶት ሳይሆን በመስመር ወይም በአላማ TPLF አንዱና ቀዳሚው አጋር ሆኖ ስለተገኘ ነበር።
ኦፌኮ ሕወሓትን በሚዲያም መሬት ላይም ቄሮን በማንቀሳቀስ ጭምር በእነሱ አጠራር የአሃዳዊ መንግስት ያሉትን የዶ/ር አብይን መንግስት በውጭ ሃይሎች እገዛ ለማስወ*ገድ ይህ የማይሆን ከሆነ ደግሞ አገር ለማፍረስ ከመስከረም 30 በኋላ ሕጋዊ መንግስት ስላለመኖሩ ለአብይ አህመድ መንግስትም መከላከያ እንደማይታዘዝ በኋላም አዲስ አበባ ጀምረን አዲስ አበባ እንጨርሰዋለን በሚል ያልሰበቁት ጦር አልነበረም።
የፌደራሊስት ሃይሎች አንበል የሆነው ወያኔ በመደበኛ ጦርነት የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊትን በየትኛወም መንገድ ገጥሞ መገዳደር እንደማይችል ስለሚያውቅ ከፋፍሎ ለማዳከምና ኢትዮጵያን የመበታተን እኩይ አላማውን ለማሳካት በፈጠራቸው ሳተላይት ድርጅቶች በኩል ሙከራውን አቋርጦ አያውቅም።

በአማራ በኩል የፌደራሊስት ሃይሎች ተብለው መቀሌ ከተሰበሰቡት ውስጥ በአማራ ክልል በኩል አገው ሸንጎና ቅዴፓ በድርጅት ደረጃ ሲገኙ አማራን እወክላለሁ ብሎ በድርጅት ደረጃ መገኘት የቻለ ባይኖርም ስብሰባው ላይ በግለሰብ ደረጃ የተገኙ አማራዎች ስለመኖራቸው ግን መረጃዎች ያሳያሉ።
ከመስከረም 30 በኋላ ሕጋዊ መንግስት ስለማይኖር በሽግግር መንግስት በተለይ ደግሞ ከጥቅምት 24 የሰሜን ዕዝ ጥቃት በኋላ በጦርነቱ ወያኔ አሸናፊ ስለሚሆን በአማራ በኩል ከወያኔ ጋር ሊደራደር የሚችል አንድ አካል ያስፈልጋል በሚል በእነ ያሬድ ጥበቡና ታምራት ላይ መዝገብ የሚንቀሳቀሱ ዳግማዊ ኢህዴንን/ብአዴንን ለመፍጠር በርካታ አማራዎች ተንቀሳቅሰዋል።

በአማራው በኩል ለውጥ አምጥተንና ለውጡን አዋልደን ነገር ግን ከብልጽግና ተገፍተን ወጥተናል ብለው አልቃሽና ሙሾ አውራጅ አክቲቪስቶችን ያሰማሩት ቆሞ ቀሮች ዳግማዊ ኢህዴን/ብአዴንን ከውጭ ሆነው ለመፍጠር ከሚንቀሳቀሱት ጋር እየተመጋገቡ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በኦሮሚያ በኩልም ተገፋሁ በሚሉት የጀርባ መሪነት ዳግማዊ ኦህዴድን የመፍጠር ዘመቻው በሰፊው ተሰርቶበታል። በኦሮሚያ በኩል ያለው ሀይል ሰላማዊ አማራወችን በማስገደል ግፍ ሲፈፅም በአማራው በኩል ያለው ደግሞ የአልቃሽነት ሚና ይዞ ህዝቡን ብሶት ውስጥ በመክተት መንግስት የጭፍጨፋና ግ*ድያ አስፈጻሚ እንደሆነ የአዛኝነት ሙሾ በማሰማት ይገልፃሉ። በዚህ ሂደት ህዝቡ ጀርባውን ለመንግስት እንዲሰጥ በማድረግ የምንፈልገውን ውጤት እናገኛለን የሚል በሰው ህይወት ፖለቲካ ለመቆመር ሲዳክሩ ይታያሉ።

ከፌደራሊስት ሃይሎች የመቀሌ ስብሰባ በኋላ አብን በስብሰባው ካለመገኙት ባሻገር የሚያራምዳቸው ሐሳቦችና የሚይዛቸው አቋሞች የአማራን ሕዝብ ሁለንተናዊ ጥቅሞችን አገራዊና ቀጠናዊ ሁኔታዎችን ከግምት ያስገባ የጠራ አቋም መያዝ የጀመረ መሆኑ በአብን ላይ የተጠናከረ ከፍተኛ ዘመቻዎች ተጠናክረው እንዲከፈቱ አድርጎታል።

ወያኔ ለ27 ዓመት በብአዴን በኩል የአማራን ሕዝብ ጠርንፎ እንደያዘው ሁሉ በአብን በኩል ደግሞ የአማራን ሕዝብ ጠርንፎ አጀንዳውን ለመሸጥና በፌደሬሊስት ሃይሎች ምድብ ለማካተት የነበረው እቅድ መክሸፉን ተከትሎ በአብን ላይ ያልተቋረጠ ዘመቻ ከመክፈት ጎን ለጎን አማራን ጠርንፎ ሊይዝላቸው የሚችል ሌላ አጋር ሃይል ወደማዋለዱ እንቅስቃሴ ለመግባት ተገደዋል።

በዳግማዊ ኢህዴን/ብአዴን ስር በአብን፣ በብልፅግና፣ በሲቪክ ማህበራት፣ በባልደራስ፣ በሚዲያዎችና በፋኖ ስም የሚንቀሳቀሱ አካላት በቀጣይ ራሳቸውን ችለው በድርጅታቸው ለይቶላቸው ይወጣሉ ወይስ ባሉበት ሆነው ከትህነግ ጋር ጥምረት በመፍጠር የዶ/ር አብይ አህመድን አስተዳደርን እናስወግ*ዳለን ብለው ተማምለው ግንባር ፈጥረው ይዋጋሉ የሚለውን ጉዳይ በሂደት የምናየው ይሆናል።

ቶማስ ባንጃው

Exit mobile version