መከላከያ የደብረ ብርሃን ዙሩያ አጸዳ፤ባህር ዳርና ጎንደር ዙሪያ ሙሉ ኦፕሬሽን ሊጀመር ነው

ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በአማራ ክልል ያለው ግጭትና አለመረጋጋት ሰላማዊ መፍትሔ እንዲበጅለት

ራሳቸውን ” የፋኖዎች ሕብረት” በሚል የሚጠሩት ታጣቂዎች የደብረ ብረሃን ከተማን ለመቆጣጠር በመውጪያዎቿ ዙሪያ ጥቃት ከፍተው እንደነበር በተለያዩ አግባቦች ሲገልጽ መቆየቱ ይታወሳል። “በስጋት ውስጥ ነው ያለነው” ሲሉ ነዋሪዎቹ ዛሬ ማለዳም በከተማዋ ያለው ሁኔታው ከትናንትናው የተለየ እንዳልሆነ ነገረውኛል ብሎ ቢቢሲ እንደዘገበው ሳይሆን ዛሬ ደብረብርሃን ዙሪያ ያለው ወጊያ መከላከያ ከገባ በሁዋላ እየገፋ ወደ ጣርማ በር እንዳደረሰው ያነጋገርናቸው ወገኖች ገልጸዋል።

በደብረብርሃን ከተማዋ ዙርያ የጥይት ተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበር ያስታወሱት እነዚህ ክፍሎች ታክቲካል የሆነውን ጉዳይ ባይረዱም መከላከያ ራሱን አደራጅቶ በሁሉም አቅጣጫ ጥቃት መክፈቱን መስማታቸውን፣ ይህ በሆነ ሰዓታት ውስጥ ውጊያው ወደ ጣርማ በር መራቁንና አሁን ላይ ይህ ሲጻፍ ያለው ሁኔታ ይህን እንደሚመስል ከምስክሮች ለመረዳት ተችሏል። ትናንትና ከትናንት በስቲያ የነበረው ስጋት መቀነሱንም እነዚሁ ወገኖች አመልክተዋል። ደብረ ብርሃን እንጅግ እያደገች ያለች የአይቲ ከተማ መሆኗ፣ በርካታ ኢንደስትሪዎች እየሰፉባት የመታች ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ዝርፊያ ተፈርቶ እንደነበርም የጠቀሱ አሉ። ይህን የጠቆሙት ወገኖች አሁንም ቢሆን ስለማ ሊቀድም እንደሚገባ ገልጸዋል።

የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ወዳጅና ዕቅድ አስፈሳሚ በመሆን የኢትዮጵያን መከላከያ ” የደርግ ወታደር” በሚል እንዲበተን ማሴራቸው በይፋ ምስክር የሚቀብባቸው፣ በረሃ አለንጋ ከሞት አፋፍ ላይ ካሉ ወገኖች ብር ዘርፈው የከዱትን ሻለቃ ዳዊት መሪና ነጻ አውጪ አድርጎ የተነሳው የአማራ የትጥቅ ትግል ጎንደርን መቆጣጠሩን፣ ባህር ዳርን እያሸተተ እንደሆነ፣ መሳይ መኮንን መከላከያ ላይ ተሳልቆ በፌስ ቡክ ገጹ ” አሁን የደረሰኝ መረጃ” ሲል አመልክቷል።

የባህር ዳር አየር ማረፊያና መገናኛ ጣቢያ በፌደራል ልዩ ሃይል እየተተበቀ መሆኑንን የተለያዩ መረጃዎች ያሳያሉ። ሆኖም ግን ባህር ዳር ውጥረት ቢኖርም ይህ እስከተዘገበ ድረስ በዙሪያዋ ከሚሰማ የጥይት ድምጽ በቀር በክልሉ መንግስት እጅ ናት። ጎንደር ተመሳስለው የገቡ የታጣቂዎቹ ሃይሎች ቢኖሩም ሙሉ በሙሉ ጎንደር በእጃቸው ስራ ስለመሆኗ አሳማኝ መረጃ የለም። ይልቁኑም መንግስት ልክ በደብረ ብረሃን እንዳደረገው በሙሉ ሃይሉ ማጽዳት ለመጀመር ያሰባሰበውን ሃይል ለማሰማራት ዝግጅቱን ማተናቀቁ ተሰምቷል። ይህ ኦፕሬሽን ነገሮችን ይቀይራቸዋል ተብሎ እንደሚገመት ታውቋል።

See also  በጎርጎራ ገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ለመሰማራት 134 ባለሀብቶች የቦታ ጥያቄ አቀረቡ

እስካሁን ምንም ትንፍሽ ያላሉት የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ሁመራ አካባቢዎች በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ስለ አካባቢዎች በተከታታይ የሚጽፉ ግልጸዋል። የኮሎኔል ደመቀ ሃይል፣ የአርበኛ መሳፍንትና አጋያ ጦር ለሻለቃ ዳዊትን እንቅስቃሴ ድጋፍ አለመስጠቱን የሚገልጹ በደብረ ብርሃን እንደሆነው ሁሉ በጎንደር እንደሚደረግ እየገለጹ ነው።

አባይ ማዶ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በሻለቃ ዳዊት ሃይሎች ስር ግብቶ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ መልኩ መቀየሩን የስፍራው ምንጮች ገልጸዋል። ይህ ወንድምን ከወንድም የሚያጋድል ጦርነት በሰላማዊ መነገድ እንዲቋጭ ያሃይማኖት ተቋማት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ድርጅቶች እየወተወቱ እንደሆነ ይታወቃል።

ዛሬ ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተመሳሳይ ጥሪ አቅርበዋል። በአማራ ክልል የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት፤ በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች የተጀመሩ “የሰላም ጥረቶች እና ስምምነቶች” በክልሉም መደረግ የሚችልበት ዕድል እንዲፈለግ ዘጠኝ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጠየቁ። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም ወቅት የጸጥታ አካላት “ያልተመጣጠነ ኃይል እንዳይጠቀሙ”፣ “ብሔርን መሠረት ያደረጉ ማግለሎች እና ጥቃቶች እንዳይስፋፉ” እንዲሁም የጅምላ እስሮች” እንዳይፈጸሙም ድርጅቶቹ ጠይቀዋል።

ዘጠኙ ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ይህንን ጥያቄ ያቀረቡት፤ በአማራ ክልል የተከሰተው “ግጭት እና አለመረጋጋት በከፍተኛ ጥንቃቄ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲገኝለት” ዛሬ ሰኞ ነሐሴ 1፤ 2015 ባቀረቡት ጥሪ ነው። ይህንን ጥሪ ካቀረቡት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መካከል የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ)፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል፣ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር እና የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት ይገኙበታል።

“ግጭቶችን የመከላከል እና ሰላም የማስፈን” ጥረት ጊዜ የማይሰጠው “አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን እናምናለን” ያሉት ድርጅቶቹ፤ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭት “እጅግ እንዳሳሰባቸው” በመግለጫቸው ላይ ጠቅሰዋል። የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶቹ፤ “ግጭቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ስር እየሰደዱ እና እየተስፋፉ” መሆኑን ያነሱ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት “ግጭቶችን ለማስቆም የሚወሰዱ እርምጃዎች የብዙሃንን ደህንነት፣ የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች እና ነጻነቶች አደጋ ላይ የማይጥሉ” ሊሆኑ እንደማይገባ ኢትዮ ኢንሳይደር አመልክቷል።Leave a Reply