Site icon ETHIO12.COM

የሲሪላንካው “FamilyCracy” – ከመዓቱ እስከ ተውኔቱ


እስሌማን ዓባይ

የታሚል ታይገር ተገንጣይ አማፂያንን ከረጂም አመት ውጊያ በኋላ ድል ማድረጋቸው የብልሹ አሰራራቸውን ብሶት ማስታገስ አይችልም። የሲሪላንካው መሪ ራጃፓክሳ ሊተገበሩ የሚችሉ የመፍትሄ ርምጃዎች ላይ የታየባቸው ዳተኝነት ይባሱኑ ህዝባዊ ቁጣውም ጨመረባቸውንጂ፤

የሲሪላንካ ዜጎች ለከፍተኛ መከራ የዳረጋቸው ሙስና ብልሹ አስተዳደር ነበሩ። በተለይም ዋና ዋና የሀላፊነት ቦታዎች በዘመዳዝማድና ቤተሰብ የሰበሰበው FamilyCracy ነበር። በሲሪላንካ የኢኮኖሚ ቀውሷ በረታ…የኢኮኖሚ ውድቀቷን bankruptcy ከወራት በፊት ማወጇ ይታወሳል። የሀብት የፀጋ የተስፋ ምድር እንዳልተባለች በየቀኑ ሳይበሉ የሚያድሩ ዜጎች መገለጫዎቿ እስኪመስሉ ተቸገሩ። የሲሪላይካ ዜጎች ወደ አመፅ ተሸጋገረ። እውነተኛው የዜጎች መከራን እንደመልካም አጋጣሚ በመቁጠር የተሰራው የጂኦፓለቲካ ጨዋታ ግን አሳዛኝ ነበር፤ የመከራ ቀናትን በሰው ሰራሽ ማራዘሙ አንዱ ሲሆን የዜጎች የትግል ፍሬ ብዙም ሳይጓዝ ራሱ ጠልፎ የሚጥለው መሆኑ ዋናው ነበር። ለእውናዊ መከራው ከመጣው አጋር ይልቅ ለቢዝነስ በርካታ ኢንቨስት ተደረገባት። መጀመሪያ ከቀውስ አለመግባህ ነውንጂ …ከገባህማ ኤኛም በቅርቡ የገጠመንና የምናውቀውም ነው።

ቀውሱን ተከትሎ IMF ብድር ለመስጠት ተደጋጋሚ ጥረት አደረገ። ሀገሪቱ ሪፎርም ትሰራ ዘንድ ጠየቀ። መንግስቷ ደግሞ የቻይናን ብድር መረጠ። ሀገሪቱ ካለባት የእዳ ብዛት ቻይና ለማበደር ብትፈልግም ሲሪላንካ በአይኤምኤፍ የባሰ ቀውስ መዳረግ ሀሳቡን ወደ ኋላ አስባለ፤ ሌላው የምእራባዊያን የቻይና ብድር ወጥመድ የፈጠራ ፕሮፓጋንዳ ነበር ቤይጂንግ እጇን ሰብሰብ አርጋ ለመቆየት ምክንያት የሆናት
በዚህ መሃል ወራት ተቆጠሩ። ሲሪላንካ ከአይኤምኤፍ እንድትበደርና እዳዋን አቃልላ ሌላ መበደር እንድትችል ገለፀችላት።
ሰውየው እያመነታም እየዘገየም ከአይኤምኤፍ ቅርርብ ጀመረ። በዚህ መሃል የዩክሬይን ጦርነት ተጀመረ። በየካቲት ቪክቶሪያ ኑላን ኮሎምቦ ተጉዛ ነበር።
ቆይት ብለው የወጡ መረጃዎች እንዳመለከቱት ሲሪላንካ ሩሲያን እንድታወግዝና ከእዳ ስረዛ ጋር ከፍተኛ የብድር ፕሮፓዛል ቀረበላት። ገለልተኝነትን መረጠች። ሴትዮዋ በተመለሰች በሳምንቱ አመፁ መቀጣጠል ጀመረ።

ምእራባዊያን የቻይና የብድር ወጥመድ የሚሉት ፕሮፓጋንዳ ተጠናክሯል። የቻይና ብድር ሲሪላንካ ውስጥ ምን ይመስላል በሚል ባደረገሁት ዳሰሳ የውሸት መሆኑን የሚያሳዩ እውነታዎችን ተመለከትኩ። ሲሪላንካ ከቻይና በርግጥም እዳ አለባት። ነገር ግን አስር በመቶ ያልበለጠው ነበር ድርሻው። የሚገርመው ጃፓን ለሲሪላንካ ያበደረችው ከቻይና በላይ የ 11 በመቶ ብልጫ ያለው ነው።
ይቱንና የጃፓን የብድር ወጥመድ የሚል ማንበብ አልቻልኩም። ከአሜሪካኖች የመጣ ተንኮለኛ አጀንዳ አለ ማለት ነው።
በስሪላንካውያን ላይ ያን ሁሉ መከራ ያስከተለው የብድር ወጥመድ ነው ከተባለ እሱ አበዳሪ ማን እንደሆነ ፈትሹት..። ፈልጌ ያገኘሁት እሱ አይኤምኤፍ ነበር… ቁጥሮች ይህንኑ ያስረግጣሉ፤ የእዳዋ 79 በመቶ የአይኤምኤፍ ነበር።

ከመዓቱ እስከ ተውኔቱ ከተውኔቱ አጫጭር

▪️አሜሪካዊት ልኡክ ቪክቶሪያ ኑላንድ ሲሪላንካን ጎበኙ፤ አመፁ ከመነሳቱ ከሳምንት በፊት። ሌላው አሜሪካዊ ባለስልጣን ዶናልድ ሉ በወርሃ የካቲት በኮሎምቦ ተገኝተው ነበር።

▪️ አንድ የሲሪላንካ ባለስልጣን ስማቸውን ሳይገልፁ እንደተናገሩት “በአይኤምኤፍ በኩል ርዳታ ሊሰጡን ከተስማማን በኋላ አሜሪካ፣ ኔቶ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሩሲያን በማውገዝ መግለጫ እንድናወጣ አበረታተውናል።”

▪️ አመፁ እየተባባሰ ቀጠለ። የምእራባዊያን ስሪት የሲሪላንካ ማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች 🇱🇰 ስለ ቻይና ወጥመድ በማውራት ተጠምደዋል። የአለም ባንክ ወጥመድ ወይስ የጃፓን ወጥመድ? ይህን የሚጠይቁት የነገሮች መጠምዘዝ ያሳሰባቸው ሀገሬዎች ነበሩ።

▪️አመፁ እየተፋፋመ ሲሄድ በሲሪላንካ የሚገኙ የምዕራቡ ዓለም ዲፕሎማቶች አመፁን መደገፋቸውን ገልፀው የሲሪላንካ መንግሥት ተቃዋሚዎችን እንዲተዋቸው ግፊትና ጥሪ ማድረግ ቀጠሉ። ግልፅ ነው…። ይህ የአሜሪካ unipolar hegemony playbook 101 መሆኑን አትዘንጋ።

▪️የሲሪላንካ ተቃውሞ ሰልፎች በዩኤስኤአይዲ ገንዘብ የሚበጀትላቸው የሀገር ውስጥ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሎቢስቶች በአለም አቀፍ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች NGOs እና ቲንክ ታንክ ሰራተኞች እና ሊበራል ምእራባዊ ሲስተምን በሚደግፉ ተጽእኖ ልሂቃን ነው። የከተማ ነዋሪዎች የላይኛው መደብ የሆኑ ሊበራሎች ናቸው።

▪️የሚስተጋቡ መፈክሮች በሀገሪቱና አካባቢው ባልተለመደ የቋንቋ አጠቃቀም በአብዛኛው በእንግሊዝኛ የተጻፉ ሲሆኑ በመፈክርም ሆነ በአመፁ ኢላማ የተደረጉት የቻይና መንግስት አጋር ተቋማት/ሀገራት ናቸው።

▪️የተቃዋሚዎቹ አስተባባሪዎች ደጋግመው የሚያስተጋቡት የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት በሲሪላንካ ቀውስ ጣልቃ እንዲገባ ማበረታታት ነበር።

▪️በተቃውሞ ሰልፎቹ ፀረ-አይኤምኤፍ አይደሉም መልእክት አይስተጋባም። ሰልፈኞቹ አይኤምኤፍ ጋር መተባበር ሲገባው ከቻይና ጋር ለምን አደረገ የሚል ወቀሳ ደጋግመው ያቀርባሉ።

▪️ኢኮኖሚያችን ይበልጥ ሊበራል ይደረግ ሲሉም ጠይቀዋል።

▪️ታዋቂ የሆኑት የተቃውሞው አስተባባሪዎች ቀደም ባሉ ጊዜያት ከምዕራባውያን ዲፕሎማቶች ጋር እንዲገናኙ ተጋብዘዋል።

▪️የተወሰኑት ደግሞ በምዕራባውያን ሀገራት አመቻችነት ማህበራዊ ሚዲያን ተጠቅመው ተቃውሞን ሀገራቱ ወደ ፈለጉት አላማ ማስኬድ ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎች በቅርብ ጊዜያት ስልጠና የተሰጣቸው ናቸው፤ የተቃውሞ አስተባባሪነት ላይም ሲሳተፉ ተስተውለዋ።

▪️የተወሰኑት የተቃውሞው ተዋንያን በውጪ ሀገራት በሚገኙ ነገር ግን በስም ባልታወቁ ድርጅቶች “የጋዜጠኝነት ስልጠና” በተባሉ መርሃ ግብሮች የተሳተፉ ናቸው።

የዓባይልጅ

Exit mobile version