Site icon ETHIO12.COM

ከ800 በላይ የአልሸባብ ተዋጊዎች ተገደሉ፣ መቶ ተማረኩ ” ዳግም ድርሽ አይልም”

ወደ ኢትዮጵያ ዘልቆ በመግባት ወረራ ለመፈጸም የሞከረው የአልሸባብ ሃይል በተደጋጋሚ መመታቱ ሲገለጽ ቆይቷል። ዛሬ ይፋ እንደሆነው ደግሞ ከ800 በላይ የአልሸባብ ታጣቂዎች የተገደሉ ሲሆን መቶ ተማርከዋል።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ በቲውተር ገጻቸው ምስል አስደግፈው ይፋ እንዳደረጉት ይህ በጥቅም ተደልሎ ወደ ኢትዮጵያ ለመዝለቅ ያሰበው ሃይል የተመታው ሁለተኛ እንዳያስብ ተደርጎ ነው።

በሚያራምዱት አቋምና አካታች ፖለቲካ ጥርስ የተነከሰባቸው፣ አልፎም “አሸባሪ” እየተባሉ ሰሞኑንን ዘመቻ የተከፈተባቸው ሙስጠፌ ሰራዊቱን በማስተባበርና ሞራል በመስጠት የቅርብ እገዛ ሲያደርጉ እንደነበር ተመልክቷል።

“አሸባሪው ወደ ድንበር ለመጠጋት እንዳያስብ ተደርጎ ተመቷል” ሲሉ በቲውተር ገጻቸው አስፍረዋል።

ስለጥቃቱ መረጃ የሰጡ እንዳሉት የኢትዮጵያ አየር ሃይል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የአሸባሪዎን ሃይል ከያለበት በመለብለብ ለግረኛው ሃይል ሰፊ ድጋፍ አድርጓል።

አሰቅድሞ የሎጂስቲክ አቅማቸውን ያመከነው የኢትዮጵያ አየር ሃይል የውሰደው እርምጃና እግረኛው ሃይል ተናቦ ያካሄዱት ጥቃት ለሌሎችም ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን የገለጹ “አሁን የኢትዮጵያን መከላከያ መተናኮስ ከቴክኖሎጂ ጋር መጫወት ነው። አያዋጣም። ትህነግም ውጊያ ካሰበ ተመሳሳይ እርምጃ ይወሰድበታል” ሲሉ አሁን ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ የደረሰበትን አቋም ገልጸዋል።

የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል በሚያስደንቅ ብቃትና ዕልህ ግዳጁን በመወጣት ላይ መሆኑንን ያመለከቱት ክፍሎች አክለውም ” ሙስጣፊ ላይ የተከፍተው ዘመቻ ለምንና በምን መነሻ እንደሆነ ዛሬ ግልጽ ሆኗል” ብለዋል።

አቶ ሙስጣፌ የትህነግትን የቀደመ ሶማሌ ክልልን የማተራመስ እቅድ በማክሸፍና ክልሉን በማረጋጋት ኢትዮጵያዊያን በሰላም ሳይፈሩ አብረው እንዲኖሩ በማድረጋቸው እንደ ምስሌ የሚጠቀሱ መሪ ናቸው። ይህንን የሚጠሉ በተቃራኒው ” ለምን ዕቅድቻንን አፈረስክ” በሚል የጥላቻ ዘመቻ እንደሚከፍቱባቸውና እየከፈቱባቸው እንደሆነ ይታወቃል።

Exit mobile version