Site icon ETHIO12.COM

የኢትዮጵያን ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት አቅም የሚያሳይ የጥናት ሰነድ ይፋ ሆነ


ኢትዮጵያ ያላትን የነዳጅ ሀብትና የተፈጥሮ ጋዝ አቅም የሚገልፀው የአዋጭነት ጥናት ሰነድ ዛሬ ይፋ ተደርጓል።

ጥናቱ ባለፉት አምስት ወራት በአሜሪካው ኔዘርላንድ ሲዌልና አሶሺዬት ካምፓኒ አማካኝነት የተከናወነ ሲሆ የጥናቱን ሰነድ ለማዕድን ሚኒሰቴር ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተረክበዋል።

በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የሰነዱ መዘጋጀት የኢትዮጵያን ንግድና ኢቨንስትመን ለአለም ማህበረሰብ ይበልጥ በማስተዋወቅ ትልልቅ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የጎላ አበርክቶ እንደሚኖረው ጠቁመዋል።

ጥናቱ በአሜሪካ ካምፓኒ መደረጉን ያስታወሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ ይህም የሁለቱን ሀገራት መልከ ብዙ ትብብር የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል።

የማዕድን ሚኒስትሩ ክቡር ኢንጂነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው ሰነዱ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢንቨስትመንት መስክ ከፍተኛ አቅም ያላቸውን ኩባንያዎች ለመጋበዝ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።

በዘርፉም የመንግስትን የመደራደሪያ አቅምን የሚያጎለብት ነው ብለዋል።

ሰነዱ የተፈጥሮ ጋዝና ድፍድፍ ነዳጅ የማልማት ሀገራዊ እቅዳችንን አንድ እርምጃ ያራመደ በትልቁ የመንግስትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ የስራ ውጤት ነው ብለዋል። (ኢ ፕ ድ)

Exit mobile version