Site icon ETHIO12.COM

“አሸባሪው ህወሓት በለኮሠው እሳት መልሶ እየተለበለበ ይገኛል” መከላከያ

ሠራዊታችን የድል ሠራዊት ነው !!

በየትኛውም ቦታና ጊዜ ፤ አስቸጋሪ መልክአ ምድርንም ሆነ የአየር ፀባይ ተቋቁሞ ግዳጁን በድል አድራጊነት የሚወጣው ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን ጠላትን በአስተማማኝ መመከት የሚችል ኃይል ነው።

መከላከያ ሠራዊታችን ከራሱ ይልቅ ህዝብን ያስቀደመ፤ ለሀገር እና ለህዝብ እራሱን አሳልፎ የሠጠ ብሔራዊ ኩራታችን ነው። ጠላቶቻችን ህዝባዊ ባህሪውን በውል ስለሚገነዘቡ ህፃናትንና ሴቶችን ከፊት አሰልፈው ክፍለ ዘመን ባለፈበት ጦርነት በህዝብ መአበል መዋጋታቸው የሠራዊታችንን አይበገሬነትና ጀግንነት ጠንቅቀው ስለሚያውቁት ነው።

በመሆኑም ጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን ካለፈው የህልውና ዘመቻዎች የጠላትን አሠላለፍ በውል በመገንዘብ አሸባሪውን የህወሓት ቡድን እንደ አመጣጡ አፀፋዊ ምላሽ እየሠጠው እና እየደመሰሰው ይገኛል።

ጠላት ለዜጎቹ ደንታ እንደሌለው ባሳየው በዚህ የኋላ ቀር ጦርነት ሠራዊታችን በከፍተኛ ጥንቃቄ እና የኃላፊነት መንፈስ ግዳጁን እየተወጣ ያለ ሲሆን አሸባሪው ህወሓት በለኮሠው እሳት መልሶ እየለበለበው ይገኛል።

ድል ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን!!

መከላከያ – ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም

Exit mobile version