የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሀገሩ ክብር የሚከፍለው መስዋዕትነት በተግባር ከታየባቸው ቀናት መካከል ጥቅምት 24፣ 2013 ዓ.ም አንዱ ነው፡፡ በዕለቱ በመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ የደረሰው ጥቃት በሀገራችን ታሪክ ጥቍር ጠባሳ አሳርፎ ያለፈ ክስተት ነው፡፡ ይህ በሠራዊቱ አባላት ላይ የተፈጸመዉ ጥቃት መቼም ቢኾን፣ በየትኛውም ቦታ ሊደገም የማይገባውና ታሪክ የማይረሳዉ አስከፊ ድርጊት ነው፡፡
በሠራዊታችን ላይ የተፈጸመዉ ጥቃት ሀገራችንን ከፍተኛ ዋጋ ያስከፈለ፣ ወደ አውዳሚ ጦርነት ጎትቶ ያስገባንና ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ያደረሰ በመኾኑ ሊረሳ የማይችልና ሊደገም የማይገባዉ አሳፋሪና አሳዛኝ የታሪክ አንጓ ነው፡፡ ምንም እንኳን ጥቃቱን ተከትሎ የተገባበትን ጦርነት በሠላም ስምምነት መቋጨት ቢቻልም ቀኑ በታሪካችን እንደ ነውር መቆጠር ያለበት ተግባር የተፈፀመበት ቀንና ትምህርት የሚወሰድበት ክስተት በመሆኑ ዕለቱ ሁሌም ሊዘከር ይገባል፡፡
ይሄንን ቀን የምናስበው ለቂምና ለበቀል አይደለም። ያ ስሕተት እንዳይደገም ነው። እናቶች የሚያለቅሱበት፤ ወጣቶች የሚማገዱበት፣ የሕዝቦች ትሥሥር የሚላላበት፤ ቤተሰብ የሚበተንበት፣ የሀገር ሀብት የሚወድምበት የጦርነት መንገድ ይብቃ ለማለት ነው።
ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የተፈጸመዉን ጥቃት በመቀልበስ በኢትዮጵያ ላይ ተከፍቶ የነበረዉን ጦርነት በጋራ ርብርብ መክተን የሀገራችንን የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት አስጠብቀናል፡፡ ይህም ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚደረግ ማንኛውም ጥረት ሊሳካ እንደማይችል ፅኑ ማሳያ ነው:: በመሣሪያ ኃይል ሥልጣን ለመቆጣጠር የሚደረግ ጥረት በኢትዮጵያ ምድር ሊሳካ እንደማይችል አረጋግጧል፡፡
መንግሥት ለዘላቂ ሀገራዊ ሰላምና ለሀገር አንድነት ሲል ችግሩን በሠላማዊ መንገድ ለመቋጨት የወሰነው፤ ተመሳሳይ ስሕተቶች በየትኛውም አካባቢና ጊዜ እንዳይደገሙ ትምህርት እንዲወሰድበት ለማስቻል ነው፡፡ መከላከያ ሠራዊትን ማጥቃት መደገም የሌለበት ትልቅ ስሕተት መኾኑን በዚህ ወቅት በየጥሻዉ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች ሊገነዘቡት ይገባል፡፡
መከላከያ ሠራዊታችንን ማጥቃት የሀገራችን የኅልውናዋ የመጨረሻ ምሽግን መንካት እንደኾነ ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ በየመንደሩ እየዞሩ የሕዝብን ሰላም የሚነሱ፣ ዝርፊያ የሚፈጽሙና ሀብት የሚያወድሙ አካላትም እየሄዱበት ያለው መንገድ የስህተት መሆኑን ተገንዝበው መከላከያ ሠራዊታችን ላይ የሚፈፅሙትን ትንኮሳ ሊያቆሙ ይገባል፡፡
ወንዝ የማያሻግር የፅፈኝነት ዓላማ አንግበው የሚንቀሳቀሱ የመንደር ታጣቂዎች፤ ትልቅ ሀገራዊ ራእይ ሰንቆ የተሰለፈዉን መከላከያ ሠራዊታችንን በማጥቃት ምንም አይነት ድል እንደማያገኙ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ዘብ የቆመው ሰራዊታችን ዛሬም በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል፡፡
መከላከያ ሠራዊታችን በጥቅምት 24 የደረሰበትን ጥቃት አልፎ፣ ሀገራችን ላይ የተከፈተውን ጦርነት መክቶና የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት በመሥዋዕትነቱ አስከብሮ ኢትዮጵያን ከታላቅ አደጋ ታድጓል፡፡ በዚህ ወቅት መከላከያ ሠራዊቱ ለሀገራችን እየከፈለ ያለዉን ክቡር መሥዋዕትነት በማቃለል የሐሰት ቅስቀሳ የሚያሰራጩ አካላትም ከባለፈው ስህተት ተምረው ከእኩይ ተግባራቸው ሊታቀቡ ይገባል፡፡
ጥቅምት 24 ጥቃት የተፈጸመበት ጀግናዉ ሠራዊታችን አሁን ላይ የበለጠ ዐቅሙን በሰው ሃይል፣ በስነምግባር፣ በመሳሪያ፣ በቴክኖሎጂና በወታደራዊ ሳይንስ ገንብቶ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱን ከማንኛውም የውስጥም ሆነ የውጭ ጥቃት ጠብቆ ኢትዮጵያን ወደላቀ ከፍታ ለማሸጋገር በሚችልበት አስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ምንግዜም ፍላጎታቸው ሰላም፣ ልማትና አብሮነት ብቻ ነው፡፡ የሀገር መከላከያ ሠራዊታችንም እነዚህን የሕዝብና የመንግሥት ፍላጎቶች እውን ለማድረግ ማንኛዉንም መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነው፤ እየከፈለም ነው፡፡ ይሁን እንጅ አንዳንድ ቅጥረኞች የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የሐሰት ዘመቻዎችን ከፍተው የሰራዊቱን ክቡር ስም ለማጠልሸት ሲሞክሩ ታይቷል፡፡ ሆኖም ሠራዊታችን እንኳን ከሃሰተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ በጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በተፈጸመበት ጥፋት እንኳ የማይንበረከክ ፅኑ መሰረትና ኢትዮጵያዊ ጀግንነት የተላበሰ መኾኑን ወዳጅም ጠላትም ያውቀዋል፡፡
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም በተለመደው ደጀንነቱ ሠራዊቱን ለላቀ ድልና ክብር እያበረታታ ይገኛል።ይህንን ተግባሩንም አጠናክሮ ሊቀጥልበት ይገባል፡፡ መከላከያ ሠራዊትን የማጥቃት የባንዳነት ተግባር በማንኛውም ወቅትና ሁኔታ ሊወገዝ የሚገባው ተግባር ነው፡፡ ለዚያም ነው ዘንድሮ የጥቅምት 24ን ለሦስተኛ ዓመት ስናስብ ይህ አይነት የሃገር ክህደት እንዳይረሳም እንዳይደገምም የምንዘክረው፡፡
ክብር ለሀገር ሉዓላዊነት ለተሠዉ ጀግኖች!!
ይቅር እንላለን ግን አንረሳም፡፡
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
- የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስአንድ ሰው የደም ግፊት መጠኑ ከፍተኛ ከሆነ እና በጊዜው ሕክምና ካላደረገ ለከፍተኛ የልብ በሽታና በደም ዝውውር ማነስ ምክንያት ለሚከሰት የአዕምሮ ሥራ መታወክ (ስትሮክ) የመጋለጥ ዕድሉ እጅግ… Read more: የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስ
- የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶችየስኳር ህመም በደም ውስጥ የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ሆኖ በሚገኝበት ሰዓት የሚከሰት ተላላፊ ያልሆነ የህመም አይነት ነው። በዋናነት አራት የስኳር ህመም አይነቶች አሉ፤ እነርሱም አይነት አንድ፣… Read more: የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶች
- ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ማንኮራፋት ከሚያንኮራፉት ሰዎች ጎን በሚተኙ ሰዎች አካላዊ እና አእምሮ ጤና ላይ ጉዳት ያስከትላል። ትዳርንም ሊያፈርስ ይችላል። “ስለ ባለቤቴ ማንኮራፋት ቀላል… Read more: ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?
- Ethiopia Working To Secure New Development Bank MembershipThe Ministry of Foreign Affairs disclosed that Ethiopia is working hard to become member of BRICS’ New Development Bank. In a media briefing regarding the country’s… Read more: Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን ቢቢሲ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ከአለማጣ እና አካባቢው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከሃምሳ ሺህ በላይ ማሻቀቡ… Read more: የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”