ETHIO12.COM

ትህነግ “የብልጽግና መንገድ እንጀምር” አለ፤ ለትግራይ ህጻናት ዕልቂት ተጠያቂው ማን ነው?

ብልጽግናን እንደማይቀላቀል አስታውቆ ወደ ትግራይ ያፈገፈገው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ ” በአዲሱ አመት ግጭቱን አቁመን ለሰላም እድል በመስጠት የሰላም እና ብልጽግና መንገድ እንጀምር ” ሲል በይፋ የተናጠል ተኩስ አቁም ማወጁን አስታወቀ። መግለጫውን ተከትሎ “ላለቁት የትግራይ ህጻናት ተጠያቂ ማን ሊሆን ነው? ለዚህ ለዚህ ለምን ውጊያ ውስጥ ገባ?” በሚል ደጋፊዎቹ ጥያቄ እያነሱ ነው።

ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት “አፍንጫቸውን ይዘን ቅድመ ሁኔታ ተቀብለው ወደ ድርድር እናመጣቸዋለን። ካልሆነም እንወጋቸዋለን” በማለት ዶክተር ደብረጽዮን መግለጫ ሰጥተው ነበር። መንግስት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በየትኛውም ቦታ ለመደራደር ፈቃደኛ መሆኑ ባስታወቀ ማግስት የትህነግ አመራሮችና የሰራዊት መሪ በሃይል ሁሉንም እንደሚያከናውኑ ደጋገመው ሲናገሩ ደጋፊዎቻቸው ድል እንደሚያደርጉ ያምኑ ነበር።

ከመንግስት ወገን አንድም መረጃ በይፋ ሳይሰጥ “ወረራውን መከትኩ፣ በሚገባው ቋንቋ አነጋገርኩት” በሚል ከሚሰጥ መጠነኛ ምላሽ ውጪ ዝርዝር የማይቀርበበት ጦርነት እያደር በትህነግ ሰዎች መግለጫና የድረሱልኝ ጥሪ የጠራ መልክ እየያዘ መምጣቱን በርካቶች በማህበራኢ ገጾቻቸው እየዘገቡ ነው። የምስልና የድምጽ መረጃዎችም አልፎ አልፎ እያቀረቡ ነው። በትህነግ በኩልም ዝርዝር የማይቀርብበበትና ደጋፊዎቹም እንደወትሮ ይህ ተያዘ፣ ይህ ተለቀቀ በማለት መረጃ ያማያካፍሉበት ይህ ጦርነት በሳምንት ውስጥ መልኩን ቀይሮ ወደ ተማጽኖ ተቀይሯል።

ትህነግ ዛሬ ባሰራጨው መግለጫውብ ከመንግስት ጋር ለሚጀምረው የሰላም ንግግር አቶ ጌታቸው ረዳንና የቀድሞውን ጀነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ያከተተ ተደራዳሪ ቡድን መሰየሙን መሰየሙን አመልክቷል። መንግስት አስቀድሞ ተደራዳሪ የሰየመ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ትህነግ ዛሬ ላወጣው መግለጫ በይፋ ያለው ነገር የለም። ከቀናት በፊት ግን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ አቶ ሬድዋን ” የሚያሸንፉ ሲመስላቸው ዝም ይላሉ፣ ሲሸነፉ ይጮሁላቸዋል” ሲሉ መንግስት ስራውን እንደሚሰራ አስታውቀዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም የአገር መከላከያ በፈለገው የአገሪቱ ክፍል የመቀመጥ መብት እንዳለው፣ ትግራይ የኢትዮያ፣ ኢትዮጵያም የትግራይ እንደሆነች አስታውቆ ትህነግ በትግራይ ህዝብ ላይ እንዲፈነጭና አግቶ እንዲያሰቃይ ካሁን በሁዋላ እንደማይፈቀድለት በይፋ አስታውቋል።

የተሰየሙት የተዳራዳሪ ቡድን አባላት ወደፊት በሚደረገው ድርድር “የትግራይን መንግስት” እንዲወክሉ ስልጣን እንደተሰጣቸው ጠቅሶ ትህነግ ባሰራጨው መግለጫ ተደራዳሪ ቡድኑ በአጭር ጊዜ ወደ ድርድር እንደሚገባ አመክቷል።

የአፍሪካ ህብረትን ሲዘልፍና ገለልተኝነቱ ሲያጣጥል የነበረው ትህነግ በህብረቱ ጥላ ስር በሚካሄደው ድርድር እንደሚሳተፍ ያረጋገጠው አሜሪካ በይፋ በድጋሚ የአፍሪካ ህብረትን አደራዳሪነት እንደምትቀበል ይፋ ካደረገች በሁዋላ ነው። ግልጽ ባይሆንም በትናትናው ዕለት አሜሪካ በወኪሏ አማካይነት የኢትዮጵያን አንድነትና ብልጽግና እንደምትደግፍ ይፋም አድርጋ ነበር።

“ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር አፋጣኝና በጋራ ስምምነት ለሚደረግ ተኩስ አቁም ዝግጁ ነኝ” ያለው ትህነግ መንግስት ትህነግን ለመንቀል እስከ መጨረሻ የሚገፋ ከሆነ ምን ሊያደርግ እንደሚችል አልገለጸም። መንግስትም ይህ እስከተጻፈ ድረስ ያለው ነገር የለም።

መጀመሪያ “አማራ ወዳጅ ነው። የመናወራርድበት ሂሳብ የለም” በሚል መግለጫ የተጀመረው የትህነግ አዲስ አካሄድ የተፈለገውን ውጤት ሳያመጣ፣ እንዲያውም ደጀኑንን ያነቃነቀና ያነሳሳ በመሆኑ ” የተባበሩት መንግስታትና የጸጥታው ምክር ቤት በሃይል ይድረስልን” ወደሚለው የ “ድረሱልን” ጥሪ ተቀየረ። በድብዳቤው የኤርትራና ኢትዮጵያ ጦር ከኤርትራ እንዲወጡ፣ መሰረታዊ አገልግሎት ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲጀመር፣ የተያዙ አካባቢዎች እንዲለቀቁ እንዲደረግ” የጠየቀው ደብዳቤ ይዘት በቀናት ውስጥ ተቀይሮ “ልደራደር ዝግጁ ነኝ” ወደሚለው አጭርና ግልጽ ደብዳቤ ተቀይሯል።

“ለተከሰተው አሳዛኝ ግጭት ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት የምንችለው በሰላማዊ ውይይት ብቻ እንደሆነ እናምናለንም” ሲል ጥሪውን ያቀረበው ትህነግ “አትታመንም” የሚል ምላሽ በማህበራዊ ሚዲያ እየጎረፈለት ነው። ደጋፊዎቹ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ዝም ሲሉ “ትህነግን ማመን ቀብሮ ነው” በሚል መንግስት እንዳይታለል “ውርድ ከራስ” በሚል የሚያስጠነቅቁ ጥቂት አይደሉም።

በሁለቱም ወገን ተቀባይነት ያላቸው ሸምጋዮች እንደሚጨመርና ፤በሂደቱ በሁለቱም ወገኖች መካከል የእርስ በርስ መተማመን እንዲፈጠር የሚያግዙ፣ አፈጻጻምን የሚከታተሉ እንዲሁም አስፈላጊውን መመሪያና ምክር የሚሰጡ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች እንደሚሳተፉም እንደሚፈልግ አስታውቆ ትህነግ ለበተነው መግለጫ መንግስት ምን ምላሽ እንዳለው እስካሁን ይፋ አልሆነም።

አቶ አሕመድ የተባሉ በማህበራዊ ገጻቸው መንግስት እንዳይታለል፣የሠራዊቱ ድካም ከንቱ እንዳይሆን ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ሲያሳስቡ ያለፉት 7 ቀናት ትህነግ ምን እንዳለ አመልክተዋል።

  • August 22: በምንም ተአምር አፍሪካ ኅብረት አደራዳሪ አይሆንም
  • August 24: ተወረናል፣ የሰላም በሮች ዝግ ናቸው፣ ማንኛውንም እርምጃ ወስደን ወረራውን እንቀለብሳለን
  • August 31: እስካሁን የተካሄደው ጦርነት ትጥቃችንን 100% ጨምሮታል፣ ሺህ ገል፣ ሺህ ማርከናል
  • September 1: የትግራይ ሀይል በሙሉ ወረራውን ይቀልብስ
  • September 7: የጸጥታው ምክርቤት በኃይል ጣልቃ ይግባ
  • September 9: አሜሪካ የትግራይ ሀይሎችን መርዳት አለባት
  • September 11: ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የአፍሪካ ኅብረት ያደራድረን፣ ለአዲስ አመት ብልፅግና ስንል ሰላምን መርጠናል

መንግስት በይፋ ባይገልጽም የትግራይ ክልልን እየመራ ያለው ትህነግ ልክ እንደ ቤኒሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ ሃረሪ፣ ሲዳማ፣ ወዘተ ክልል በውክልናው መጠን የሚደርሰውን ተቀብሎ ለመኖር እንዲወስን፣ በአገሪቱ በጀት የተገዛውን ክባድ መሳሪያ፣ መድፍ፣ ታንክ፣ ሮኬት እንዲፈታ፣ የፖሊስ ሃይሉን ልክ እንደ ሌሎች ክልሎች ህገመንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት እንዲያደራጅ፣ የወሰንና የቦታ ይገባናል ጥያቄ በህገመንግስቱ መሰረት እንደሚታይ አምኖ ወደ ሰላም እንዲመጣ መሰረታዊ የመርህ ጥያቄ ሲያቀርብ መቆየቱን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሃመር ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከህወሓት ባለሥልጣናት ጋር መወያየታቸውን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ማስታወቁ አይዘነጋም።

አፍሪካ ህብረት የትህነግን ውሳኔ አድንቆ ሁሉም ወገኖች ለድርድር እንዲዘጋጁ ጥሪ በማቅረብ መግለጫ አውጥቷል። ከአፍሪካ ህብረት ጋር ሃመር መነጋገራቸውንና ተጨማሪ አደራዳሪ ሃይሎች እንዲሳተፉ ከስምምነት መድረሳቸውን ትላንት አስታውቀው ስለነበር የትህነግ መግለጫ እንደ ትልቅ ጉዳይ የሚታይ እንዳልሆነና የሚረዷቸው አካላት ያሏቸውን ከጭነቅታቸው የተነሳ ማድረጋቸውን በርካቶች እየገለጹ ነው።

ሙሳ ፋኪ ማህማት በዛሬው መግለጫቸው፤ በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሚደረገው ድርድር “ዓለም አቀፍ አጋሮችን” እንደሚያካትት ማመላከታቸው ዛሬ በወጣው መግለጫ ተመልክቷል።

Exit mobile version