ETHIO12.COM

ከትህነግ መዳከም ጋር ተያይዞ አልሸባብ መሽመድመዱ እያነጋገረ ነው

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ መዳከሙን ተከትሎ በሶማሌ አልሸባብ ነባር ይዞታዎቹን እያጣና ክፉኛ እየተመታ መዳከሙ እያነጋገረ ነው። አልሸባብ በሶማሊያ ለአስራ ሶስት ዓመታት ሲቆጣጠረው የነበረው ዋና መንገድ መነጠቁ ተሰማ።

“አልሸባብ የትህነግ የንግድ ተቋም ነው” በሚል ለበርካታ ጊዜያት ጥቆማ ሲሰጥና ትህነግ አልሸባበን በቀጣናው ሳይነቀል እንዲቆይ በስምምነት አብሮት የሚሰራ ተቋም እንደሆነ በማስረጃ ሲሞግቱ የነበሩ መኖራቸው ይታወሳል። ትህነግም ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብት ጥያቄ ሲነሳበት ማስፈራራሪያው “ሶማሌን ጥዬ እወጣለሁ” የሚልና አንዳንዴም ከውስን አካባቢዎች ለቆ ሲወጣ በሰዓታት ውስጥ አልሸባብ ያለአንዳች ተኩስ አካባቢውን ሲይዝ መስማት፣ የትህነግ ሃይል ሲመለስ ለቆ የመሄድ ወሬ ዳግም ሲሰራጭ ማድመጥ የተለመደ ነበር።

አሚሶም ከሚባለው የሶማሌ ሰላም አስከባሪ ውጪ በራሱ የሚታዘዝና አሚሶምን የማያዳምጥ ሁለት ሺህ ሰራዊት በሶማሌ ምድር አስልፎ የነበረው ትህነግ በዚሁ ድርጊቱ ከሰላም አስከባሪው አመራሮች ጋር ግጭት ውስጥም መግባቱ በተለያዩ ሚዲያዎች መዘገቡ አይዘነጋም። በጋራ ሰላም ለማስከበር የዘመተ ሃይል እያለና፣ ሃይሉ በአንድ ዕዝ ስር የሚመራ ሆኖ ሳለ ለተመሳሳይ ዓላማ ሶማሌ ውስጥ ካሰማራው ሃይል ገሚሱ ከአሚሶም የዕዝ ሰንሰለት እንዲወጣ የተደረገበት ምክንያት በትህነግ በኩል ዝርዝር መረጃና ምክንያት የቀረበበት አልነበረም።


አልሸባብ የትህነግ – ሌላው ኤፈርት

በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ውስጥ መሰል ታጣቂዎችን እንደ ጫና ካርድ  መጠቀም አለም የሚያውቀው ነው። ህወሃት በአሜሪካም ሆነ በሌሎች የሽብር ድርጅት ዝርዝር ውስጥ third tier terrorist ድርጅት ተብሎ የተቀመጠ ነው። ይህን አሸባሪነቱን እንደመዘገበች ነበር አሜሪካ ደርግን ለመጣልና ህወሃት ተላላኪ መንግስት ይሆንላት ዘንድ የፈቀደችው። አሜሪካ ከህወሃት በተጨማሪ አልሸባብን ቦኮ ሀራምን እንዲሁም በሶሪያ አልቃኢዳን አጋሯ አድርጋለች። ….


በቅርቡ በሶማሌ ክልል አድርጎ ወደ ኦሮሚያ ለማምራት በተንቀሳቀሰው የአልሸባብ ሃይል ላይ ፈጣንና ከባድ ምት እንዲያርፍበት ተደርጎ ሲማርክና ሲደመሰ የትህነግ አባላትም መገኘታቸውን በመንግስት ሚዲያ መገለጹ ይታወሳል። ይህ ቡድን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ክፉኛ እየተመታና በሶማሌ ለረሽም ዓመታት ያለአሳብ ግዛቱ አድርጓቸው የነበሩትን ቦታዎች እይጣ ነው።

ኤርትራ ለሁለት ዓመታት ያስለጠነቻቸው የሶማሌ ጦር ሰራዊት አባላት የኢትዮጵያ ሃይል እያሳደደ የገፋቸውን የአልሸባብ ተዋጊዎች እየመታቸውና ስፍራቸውን እያሳጣቸው መሆኑ ” ሻዕቢያ አልሸባብን ሲያደራጅ ነበር” በሚል ሲከሰና ማዕቀብ ሲጣልበት የነበረው በሃሰት እንደሆነ ማሳያም እንደሆነ እየተገለጸ ነው።

አልሸባብ በተለይም ላለፉት አስራ ሶስት ዓመታት በቁጥጥር ስር አድርጎት የነበረው የበሂራን ክልል ቡልቡርዴ፣ እዲሁም በበለድዌይን ወረዳዎች አካፋይ አውራ መንገድ የሶማሌ ጦር ሰራዊት በህዝብ ድጋፍ በጁ ማስገባቱን ነዋሪዎችን ጠቅሰው በርካታ ሚዲያዎች አመልክተዋል። ዘመቻው በስፋት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ተጨማሪ ኪሳራ እንደሚደርስበት እየተሰማ ነው።

የአፍሪካ ህብረት ኃይልም ለፀረ ሽብር ዘመቻው የአየር ድጋፍ እየሰጠ ሲሆን አሜሪካም በተመረጡ አካባቢዎች የአየር ላይ ድብደባ ድጋፍ እየሰተች መሆኑ ታውቋል። ከስፍራው ግንኙነት ያላቸው በአውሮፓ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች እንደሚሉት የአልሸባብና የትህነግ መክሰም ይያያዛል።

እነዚህ ክፍሎች እንደሚሉት ትህነግ ከከሰመ በቀጣናው በርካታ ጉዳዮች ይለወጣሉ የሚል እመነት አላቸው።

Exit mobile version