Site icon ETHIO12.COM

ወግ አጥባቂው የኦክላሆማ ሴናትር ማ’ናቸው?

የኢትዮጵያን አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል በ December 2021 ከከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ባደረገው ስብሰባ ሴናትር ጂም ኢንሆፍ ኢትዮጵያን በጅኖሳይድ ለመጠየቅ በሴኔት ቢሮ የታሰበው HR_4350 አንቀፅ 6464 Determination of potential Genocide or crimes Against Humanity የሚለው ሙሉ በሙሉ ህጉ መሰረዙን ይፋ ያደረጉት አሳቸው ነበሩ። የኢትዮጵያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ፕሬዝዳንት ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ ለሴኔተር ጀምስ ኢንሆፍ “የክፉ ቀን የቁርጥ ወዳጃችን ነዎት” ሲሉ ምላሽ አድርሰዋቸዋል።

▪️ሴናትር ጂም ኢንሆፍ ማናቸው?
በአሜሪካ በአንድ ደረጃ ከፍ ያለ ስልጣን ካላቸው የሴኔት አባላት መካከል ናቸው። ከኮንግረስ ወይም ከክልል ህግ አውጭ ኮሚቴ አባላት እጅግ ከፍተኛ የሆነ ስልጣን ባለቤት..። በዛ ላይ ክችች ያሉ የኦክላሆማ ወግ አጥባቂ ሴናትር ጂም ኢኖፍ።

አሁን ላይ ከሚመሯቸው ልዩ ልዩ የሴኔት ኮሚቴዎች መካከል የወታደራዊ አገልግሎት እዚጋ እንጥቀስ። ይህ ስልጣናቸው በአሜሪካ የወታደራዊ ፖሊሲ፣ የቴክኖሎጂ ሁኔታ፣ ወታደራዊ በጀት፣ የኒዩክለር መርሃግብር ወዘተ..ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አለው። በተለይም በአሜሪካ የውጭ ወታደራዊ አቋም ላይ ልዩ የውሳኔ ሰጪነት ሚናው ይጎላል።

ሴናትሩ በግንቦት 2021 “ኢትዮጵያ ልትደገፍ ይገባታል ማለታቸው ይታወሳል። ጄም ኢንሆፍ፦
▪️የአሜሪካን የላላ የመሳሪያ ቁጥጥር ፖሊሲ በፅኑ በመቃወም ይታወቃሉ።
▪️የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻንማ እንደኛ እንደ ኢትዮጵያዊያን የሚፀየፉ ናቸው።
በግብረሰዶማዊ ተሟጋች ቡድኖች በግልፅ በጠላትነት የሚታዩ ሲሆኑ ለሰብአዊ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘመቻቸው ከነዚህ አካላት ሁልጊዜም 0 % ነበር የሚሰበስቡት።
▪️የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ምዕራባዊያን የሚነዙት የተጋነነ የስጋት መርዶ ፕሮፓጋንዳ ነው በማለት ይሞግታሉ።
▪️ፀረ እስራኤል የኤክስፖርት ክልከላ (ቦይኮት ac s. 70) ሕግን ከደገፉ ሴናትሮች መካከልም ናቸው። ህጉ በፍልስጤም ተማጋቾች ለቀረቡ ጥያቄዎች በአሜሪካ የተሰጠ ህጋዊ ምላሽ ነበር። 2017 ላይ ሲፀድቅም አሜሪካውያን እስራኤል በሃይል በያዘችው የፍልስጤም ግዛቶች በምትፈፅመው የህግ ጥሰት ሳቢያ ወደ አሜሪካ ለምትልካቸው ምርቶች ከዚህ ቀደም ይሰራበት የነበረው ያለ ቅድመ ሁኔታ የመግባት ባህል ከህጉ መውጣት በኋላ ወንጀል መሆኑን ይገልፃል። እንዲተገበርም በተለያዩ ማዕቀፎች ያበረታታል። በድርጊቱ መሳተፍ ደግሞ በአሜኢካ ፌዴራል ወንጀል እንዲሆን ደንግጓል፡፡

ሴናትሩ የሩሲያ እና ቻይና መስፋፋት አፋጣኝ ምላሽ ያሻዋል በማለት ግምባር ቀደም ተሟጋች እንደመሆናቸው የሴኔቱ ዋናና ቀዳሚ ስራ ሰራዊቱን እንደገና መገንባት መሆን አለበት ብለውም ያምናሉ። በተለይም በደቡብ የቻይና ባሕር ውስጥ የቻይና ወታደሮች ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ዓለም ከፍተኛ ትኩረት መስጠት አለበት ይላሉ፡፡

▪️ስለ አፍሪካ
ጂም ኢኖፍ አፍሪካ ውስጥ የአሜሪካ ጠንካራ ጦር መኖር አለበት እያሉ መለፈፍ የጀመሩት በዘመነ ትራምፕ ጀምሮ ነበር። አፍሪካ ለአሜሪካ ብሔራዊ ወታደራዊ ስትራቴጂ ወሳኝ ናት በማለት አስከዛሬም ይናገራሉ። በቅርብ በተደረገ የሴኔት ምክክር ላይ ለፕሬዝደንት ባይደን “ክቡር ፕሬዝዳንት እንደ ወታደራዊ አገልግሎት ኮሚቴ ሰብሳቢነቴ ብሔራዊ የመከላከያ ስትራቴጂያችንን ውጤታማ አፈፃፀም ማረጋገጥ ቅድሚያ የምሰጠው ነው” ሲሉ ተደምጠዋል። አክለውም “ከቻይና እና ሩሲያ ጋር ለመወዳደር ፣ የአሜሪካን ብሔራዊ ደህንነት ለማስጠበቅ አፍሪካ ቁልፍ ሚና እንዳላት ለመናገር እሻለሁ” ነበር ያሉት።

የቻይና እና ሩሲያ መስፋፋት “ለአሜሪካ ብልፅግናና ደህንነት ዋነኛ ፈተና ሆኗል” ሲሉም አሳስበዋል፡፡ ሲቀጥሉም
“ላለፉት 20 ዓመታት በ164 አገራት ጉብኝቶች አካሂጃለሁ። ቻይና በጅቡቲ ወታደራዊ ሰፈር ማቋቋሟ ድንገተኛ ክስተት አለመሆኑንም ልነገርዎ እችላለሁ። ቻይና በዓለም ላይ በጣም ጠቃሚ በሆነው የባህር ትራንስፖርት መስመር ጅቡቲ ላይ ስትራቴጂካዊ በሆነ መንገድ ወታደራዊ አቅም ያለው ወደብ ገንብታለች፡፡ ቻይና አገራትን በእጇ ለማስገባት መሠረተ ልማቶቻቸውን አንዳንዴም ብሔራዊ ሉዓላዊነታቸውን በእዳ ለመቆጣጠር እየሰራች ነው። ከሰሃራ በታች ቢያንስ 46 የወደብ ፕሮጀክቶችን በገንዘብ ትደግፋለች ወይም ትሠራለች፡፡
ቻይና በአፍሪካ ብልጽግና ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ከማሳረፋም በተጨማሪ ወሳኝ የሆኑ የባህር መስመሮችና ኮሪደሮችን በእጇ አሰረገብታለች። አፍሪካ ለብሔራዊ ጥቅማችን ቁልፍ መድረክ ሆና መቀጠል እና መቀጠል አለባት” ነው ያሉት።

▪️ቻይናን ለመመከት የተቋቋመው አራትዮሽ
Quadrilateral Security Dialogue | QUAD
የአራትዮሽ ደህንነት ውይይት (QUAD) አራት አገሮችን ያቀፈ ሲሆን – ጃፓን ፣ አሜሪካ ፣ አውስትራሊያ እና ህንድን ይዞ. በ 2007 ተመሰረተ። በተለይም በ 2017 እንደገና ሲቋቋም ቻይናን ለመገዳደር በማሰብ ነበር።
ፕሬዝዳንት ጆ ቢደን ወደ ስልጣኑ ከመጡ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ የአራትዮሽ ደህንነት ውይይት ስብሰባ፣ “ኳድ” ከሁለት ወር በፊት ተደርጓል። በዚህ ህብረት መጠናከር ላይ ጂም ኢኖፍ ቀዳሚ አቀንቃኝ ናቸው።

የአሜሪካ ወታደራዊ በጀት ይመንደግ የሚለው ሌላው የኢኖፍ መለያ ነው። ከሮናልድ ሬገን እስከ ትራምፕ አሁንም በባይደን ዘመን የመከላከያ በጀት አንሷል በማለት አምርረው በመቃወም በመውቀስ ይታወቃሉ።
እጅግ ሞገደኛ ሴናትር ናቸው። በትራምፕ ዘመን የመከላከያ አባላት ጥቅማጥቅም እንዲሻሻል ባደረጉት ግፊት ያሰቡትን በማስፀደቅ በተግባር አስመስክረዋል።
ከህንድ ጋር አለማቀፍ ስትራቴጂክ አጋርነት በህግ አስወስነዋል። የቻይናን ስጋት ለመፋለም እንደሳቸው እልከኛ ያለም አይመስልም። እንደ መፍትሄ የሚወስዱትም
1, ወታደራዊ ቴክኖሎጂን ይበልጥ ማሳደግ።
2, ወታደራዊ በጀት ማሳደግና ጉልበትን ማፈርጠም።
3, የቻይና ባላንጣ አገራትን ማቅረብና መወዳጀት፤
4, ከቻይና መዳፍ የገቡትን አጋሮች ፈልቅቆ ለማውጣት አገራቱ ምን ይሻሉ በማለት ፍላጎታቸውን ማሟላት፤ የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው።

esleman abay #የዓባይልጅ

Exit mobile version