ETHIO12.COM

38 ኤልሲ ተከፍቶላቸው አገር ቤት የሚገቡ ምርቶች ታገዱ፤ ውሳኔውን ቅሬታ አላስነሳም

38 አይነት ምርቶች ኤል ሲ ተከፍቶላቸው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ የመታገዳቸው ዜና ቅሬታ አላስነሳም

ምርቶቹ የብሄራዊ ማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ጉሙሩክ ኮሚሽን በጥናት ለይቶ ይፋ ያደረጋቸው ናቸው ተብሏል።

በምርቶቹ ላይ እገዳ የተጣለው ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሆነው ስላልተገኙና የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ገቢ እቃዎች በቂ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ነው ተብሏል።

ምርቶቹ ለሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ምክንያት እንደሆኑና እገዳው ላልተወሰነ ጊዜ እንደሚቆይ የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢና ዋና ኢኮኖሚስት ፈቃዱ ድጋፌ ገልጸዋል።

እገዳ የተጣለባቸው መጠጦች (ውስኪ ወይም ቢራ እና ሌሎች አልኮል መጠጦች)፣ ማስቲካ፣ ቸኮሌት፣ ውሃ፣ ሲጋራ፣ ሰው ሰራሽ ማጌጫዎችና መሰል ቁሳቁስ መሆናቸው ተጠቁሟል።

በግለሰቦች ኤል ሲ ተከፍቶባቸው የሚገቡ መኪናዎችንም እገዳው ይመለከታል ነው የተባለው።

ለባንኮች አዲስ ኤል ሲ እንዳይከፍቱ ደብዳቤ እየተሰራጨ እንደሆነ ምክትል ዋና ገዢው ተናግረዋል።

ባንኮች ከሰኞ ጀምሮ እንዲተገብሩም መመሪያ መተላለፉን ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

1. የተገጣጠሙ የቤት አውቶሞቢሎች እና ባለሶስት እግር ተሸከርካሪዎች (በኤሌክትሪክ ሞትር የሚሰሩትን ሳይጨምር)

2. የተገጣጠሙ ሞተር ሳይክሎች (በኤሌክትሪክ ሞትር የሚሰሩትን ሳይጨምር) እና ብስክሌቶች

3. ከረሜላዎች ማስቲካዎች፣ ቸኮሌት፣ ብስኮቶች እንዲሁም ዋፈሮች

4. የፍራፍሬ ጫማቂ እና የታሸጉ ፍራፍሬዎች አንዲሁም ከፍራፍሬ የተዘጋጁ ጃሞች እና የድንች ጥብሶች

5. ውስኪ፣ ወይን፣ ቢራ እና ሌሎች የመጠጥ አልኮሎች እንዲሁም ሲጋራ

6. የሰው (ሁማን) እና ሰው ሰራሽ ፀጉር (ዊግ)፣ የውበት መጠበቂያዎች፣ ሽቶ፣ ሳሙናዎች፣ እንዲሁም ቦርሳና ዋሌት

7. የገበታ ጨው፣ የዶሮ ስጋ፣ የአሳማ ስጋ፣ ቱናዎች፣ ሰርዲኖች እና ሌሎች የአሳ ምርቶች

8. የእጅ፣ የግድግዳ እና የጠረጴዛ ሰዓቶች፣ ዣንጥላዎች እና ምንጣፎች ይገኙበታል

Exit mobile version