Site icon ETHIO12.COM

ከቆቦ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት የተላለፈ ውሳኔ

የከተማችንን አሁናዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ የሰዓት እላፊ ገደብ በማውጣት የተለያዩ ክልከላዎችን ማስቀመጥ በማስፈለጉ የከተማ አስተዳደሩ የጸጥታ ምክር ቤት የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል።

1) በከተማችን ከምሽቱ 2:00 እስከ ጧቱ 12:00 ድረስ ማንኛውም የሰውና የተሽከርካሪ ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ::

2) ለግዳጅ የሚፈለጉ ተሽከርካሪዎችን አለመተባበር እና የተለያዩ ምክኒያቶችን በመደርደር ፍላጎት አለማሳደር በፍፁም የተከለከለ ነው::

3) ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ማንኛውም መጠጥ ቤቶች ምግብ ቤቶች የሻሂ ቤቶችና፣ ሆቴሎች ፣ ከተፈቀደለት ስአት ውጭ ቤት ከፍቶ ማስተናገድ የተከለከለ ነው::

4) ፀጉረ ልውጥ ሰዎችን ማሳደር ወይንም ለሚመለከተው ህግ አስከባሪ አካል ጥቆማ ሰጥቶ አለማሰያዝ የተከለከለ ነው ::

5) ማንኛውም የከተማችን ወጣቶች ለወገን ጦር እውነተኛ የኋላ ደጀን የመሆን ሎጀስቲክ እና ተተኳሺ የማቅረብ ግዴታ ዛሬ ስለአለበት ፣ ቆቦ ከተማ የሚገኝ ወጣት በሙሉ ቆቦ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ጽ/ቤት እየተገኛቹሁ ተመዝገቡ ፣

6) በማንኛውም የከተማችን ቤትና የንግድ ቤት ቁማር / ቢንጎ ; ካርታ ; / መጫወት ማጫወት ; የመጫወቻ ቦታ ማከራየት ; በፍጹም የተከለከለ ነው ::

7) በከተማችን ሁሉም የሚገኙ የመንግስት ተቋማት የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች እና የቀበሌ መዋቅር ከመቸውም ግዜ በበለጠ ሁኔታ ለህብረተሰቡ ተደራሺ የሆነ ሙያዊና መንግስታዊ ሃላፊነቱን የመወጣት ግዴታ አለበት::

8)ባጃጂና ወደ ባጃጂ ማህበር አባል ያልገባ
ባጃጂ መንቀሳቀስ አይቻልም ::

9) ሆርን ኦፍ አፍሪካ ኤፍ ኤም 88.0 አሁን ላይ ስርጭት ስለጀመረ ከጧቱ 1:00-3:00 ቀን ከ6:00-80:00 ማታ ከ10:00- 12:00 በአማርኛ ; በትግርኛ ; ስለሚተላለፍ ትከታተሉ ዘንድ እናሳውቃለን ::

10) የሸቀጥ እቃወችን / ክብሪት ; ዳቦ እርሾ ; መድሀኒት ; ዘይት ; ስኳር; አረቂ ወዘተ/ ቦታ ማንቀሳቀስ ; ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ; ህገ-ወጥ ንግድ የተሳተፈ አካል በህግ ይጠየቃል ::

11)በከተማ አስተዳደሩ ጥይት የተኮሰ ያስተኮስ በተቀመጠው ውሳኔ መሰረት በህግ ይጠየቃል

12) በህዝብ መዝናኛ ቦታወች ; በገበያ ማእከል ; በሀይማኖት ተቋማት ; በሆቴልና ካፌ በመሳሰሉት ቦታወች ላይ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ::

ይህ ክልከላ አሸባረውን የትግራይ ወራሪ ሃይልን ቀብረን አማራን ከውርደት ኢትዬጲያንም ከብተና ለመታደግ የሚደረገው ትግል እስከሚጠናቀቅ ድረስ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል:: ይህንን ውሳኔ የማያከበር ግለሰብም ሆነ ድርጅት ላይ የፀጥታ መዋቅሩ አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ጭምር በአጽእኖት እያሳወቀን ለክልከላው ተግባራዊነት ሁላችንም የበኩላችንን እንድንወጣ እናሳስባለን፡፡ ::

የቆቦ ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ም/ቤት
05/02/2015
በቆቦ ከተማ

Exit mobile version