Site icon ETHIO12.COM

የአኩሪ አተር ምርት ‘አብዮት’ በአማራ ክልል፤

በአርሶ አደሩ ዘንድ አኩሪ አተርን በምግብነት መጠቀም ስላልተለመደ እና/ወይም አኩሪ አተርን ለሌላ ምርት በግብዓት የሚጠቀሙ ፋብሪካዎችም ቁጥር አነስተኛ ስለነበር፣ ግብይቱም በምርት ገበያ አማካይነት ብቻ የሚፈጸም ስለነበር አርሶ አደሩ በስፋት ወደ ማምረት አልገባም ነበር።

በ2013/14 እና በ2014/5 (አኹን) የምርት ዓመታት ግን አኩሪ አተርን በሚመለከት አብዮት ሊባል በሚችል ደረጃ ወደ አርሶ አደራችን ይሕን ሰብል ወደ ማምረት ተሸጋግሯል። አርሶ አደራችን ወደዚህ አኩሪ አተር የማምረት ለውጥ እንዲገባ ያነሳሱት፣ ምቹ ኹኔታ የፈጠሩለት፣ የገበያ ችግር እንዳይገጥመው አመኔታ እንዲፈጥር ያደረጉለት ኹኔታዎች አሉ። ከእነዚህም ውስጥ ዋነኛው ለምርቱ የገበያ ችግር እንዳይገጥመው የሚያመርተው ከሸጠ በኋላ መሆኑ ወይም በሌላ አገላለጽ ከማምረቱ አስቀድሞ የዘይት አምራቾችን ጨምሮ ከባለፋብሪካዎች እና ከውጭ ላኪዎች (Exporters) ጋር ውል በመዋዋሉ (በ Contract Farming በማምረቱ) ነው።

በዚህ የተነሳ በዚህ ዓመት ብቻ አርሶ አደሩ ከ150 ሺ ሔክታር በላይ በ Contract Farming አኩሪ አተር ሰብል ዘርቷል። በግብርናው ዘርፍ የተሠማሩ ባለሀብቶች ደግሞ ከ100 ሺ ሔክታር በላይ በሚሆን መሬት ላይ አዘምረዋል።

አኩሪ አተር በስፋት ካልተመረተ ደብረ ማርቆስ፣ ቡሬና ባሕር ዳር እና መካከለኛም ቢሆኑ ጎንደርና በሌሎች አካባቢዎችም የተገነቡት የዘይት ፋብሪካዎች ዘይት ሊያመርቱ አይችሉም። እነዚህ ፋብሪካዎች ብቻቸውን (በሌሎች የአገሪቱ ክፍል ያሉትንና አነስተኛ የዘይት ፋብሪካዎችን ሳይጨምር) ሙሉ በሙሉ ማምረት ከጀመሩ በግብዓትነት በዓመት ከ20 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የቅባት እህሎችን ይፈልጋሉ።

እስከ ባለፈው ዓመት ድረስ በመላው አገሪቷ የሚመረተው የቅባት እህሎች በጠቅላላው በዓመት የሚመረተው ከ9 ሚሊዮን ኩንታል የዘለለ አይደለም። እነዚህ ፋብሪካዎች በግብዓትነት የሚጠቀሙት የተወሰኑትን የቅባት እህሎች ብቻ ነው። በዚያ ላይ ከሰሊጥ ዘይት ማምረት አልጀመሩም።

ስለሆነም አኩሪ አተርን በስፋት ማምረት ማለት እነዚህ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ወደ ማምረት እንዲገቡ ያግዛል ማለት ነው። ተረፈ ምርቱ ደግሞ ለእንስሳት መኖ እጅግ ተፈላጊ ነው። ለኤክስፖርትም ተፈላጊ ነው።

በዚህ መልኩ በስፋት ከማመረትባቸው አካባቢዎች መካከል በግንባር ቀደም የሚጠቀሱት ጃዊ (አዊ ዞን) ፣ ምዕራብ ጎንደር፣ ሰሜን ምዕራብ ጎንደር ፣ ማዕከላዊ ጎንደር (በተለይም ታችና ማዕከላዊ አርማጨሆ) እና ጠገዴ ናቸው።

ለዚህ የአኩሪ አተር አብዮት ደግሞ የኮንትራት እርሻ አሠራርን በማስፋፋትና በማስተዋወቅ የተሳተፉ ባለሙያዎች (my colleagues) ፣ ማስተባበሩን ማቀናጀቱን ማስተዋወቁን ዘርና ግብዓት ማቅረቡን በፊት አውራሪነት የመሩትና የተገበሩት ከክልል ጀምሮ የዞንና የወረዳ የግብርና ኃላፊዎችና ባለሙያዎች (ኤቲኤን ጨምሮ)፣ የግብርና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፣ የግብርና ምርምር ተቋማት፣ የክልሉ የሰነዶችና ማኅበራት ምዝገባ ኤጄንሲና የወረዳ ዓቃቤ ሕጎች፣ እንዲሁም ይህን አሠራር ተቀብለው ወደ ምርት የገቡ ባለሃብቶችና ከሁሉም በላይ አርሶ አደሮች እጅግ ልትመሰገኑ ይገባቸዋል። በሁለት ዓመታት ብቻ የአኩሪ አተር ‘አብዮት’ አካሒዳችኋልና!

ይሁንና፦

  1. የግብርና ቴክኖሎጂ (ትራክተር፣ ኮምባይነር፣ ትሬሸር) ወዘተ መግዛት እንዲችሉ የሚመለከታቸው የፌደራል መንግሥታትን እገዛና ውሳኔ፣
  2. የኮንትራት ፋርሚንግ አሠራሩን በተሻለ ኹኔታ ለማሳለጥ ረቂቅ አዋጁንና የሕዝብ ተዘካዮች ምክር ቤት በፍጥነት ቢያጸድቀውና እሱን ተከትሎ ደንብና መመሪያ ሳይዘገዩ በሚኒስትሮች ምክር ቤትና በግብርና ሚኒስትር ቢወጡ አርሶ አደሩና ባለሃብቱ ብቻ ሳይሆኑ አገሪቱም የበለጠ ትጠቀማለች።
  3. ሌላው የንግድ ሚኒስትር በኮንትራት ፋርሚንግና በአልሚዎች የተመረተን ሰብል (አኩሪ አተርና ሌሎችም) ለውጭ ገበያ ብቻ እንዲቀርብ ለማድረግ መስከረም 19 ቀን ያወጣው መመሪያ ፋብሪካዎችን ያለግብዓት የሚያስቀር ነውና ሊስተካከል ይገባዋል።

ፎቶው፦

Via wobeshet telegram ፣ማርዘነብ ከሁለት ሳምንት በፊት።

Exit mobile version