ETHIO12.COM

ጥሪኝ ሲጸዳዳ ሳይፈጭ የሚወጣው የቡና ፍሬ ለባለፀጋዎች ብቻ የሚቀርብ ነው

ዶ/ር ፈሰሃ ኃ/መስቀል ያዘጋጁትን ታላላቅ የዱር እንስሳት በኢትዮጵያ የተሠኘ መፅሃፍ ሳገላብጥ ከ ጥሪኝ (civet) ጋር ተፋጠጥኩ።

በጥንታዊት ኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ትልቅ ቦታ ያላት ጥሪኝ በዘመናዊው የኢትዮጵያ ንግድ ውስጥ ቦታ አጥታ – ተረስታ መቆየቷ አስደነቀኝ።

ጥሪኝ ከሆዱም ከገላውም የሚያመነጨው ላቦት ተአምራዊ ነው። በተለይ ቂጡ አካባቢ ጠንካራ መአዛ ያለው እና ለሽቶ ማንጠሪያ እጅግ አስፈላጊ ቅባት (ዝባድ) ያመነጫል።

ጥሪኝ ፍራፍሬም ፣ ስጋም ….ተመጋቢ ነው ። በተለይ የቡና ፍሬ ተመግቦ ሲጸዳዳ ሳይፈጭ የሚወጣው የቡና ፍሬ ለባለፀጋዎች ብቻ የሚቀርብ ነው😀 ። ይህ ቡና ተከሽኖ ለአለም ገበያ ሲቀርብ እጅግ አነቃቂ ዋጋ እንደሚያስገኝ መረጃዋች ያመላክታሉ።

ይህ ድመት መሳይ 20 ኪሎ አካባቢ የሚመዝን ረቂቅ ፍጥረት በምዕራብ ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በስፋት ይገኛል። የጥንት ኢትዮጵያውያን በወጥመድ ይዘው እያራቡ ከሚጠርጉት ዝባድ ብዙ ማግኘታቸው ተፅፏል።

የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ሰዎች በእጅ ያለን ሃብት ለምን ዘነጋን?በአነስተኛ መጠን ብዙ የሚያስገኙ ሃብቶች በወጪ ንግድ ዝርዝር ውስጥ ቢገቡ መልካም አይደለምን?

Via Wudinehe zenebe

Exit mobile version