Site icon ETHIO12.COM

ህገወጥ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ለመግጠም የሞከሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ እንገጥመላችኋለን በማለት ህገ ወጥ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ይዘው የተገኙ ተጠርጣሪዎች እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም አንድ የሞጆ ከተማ ነዋሪ የሆነ ግለሰብ በላ ሶስት ፌዝ ቆጣሪ እንገጥምለሃለን በማለት አታለው ገንዘብ ቢቀበሉትም፤ ግለሰቡ ሁኔታውን ተጠራጥሮ በአቅራቢያው ለሚገኘውን የሞጆ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ጥቆማ መስጠቱን ተገልጿል፡፡

ማዕከሉም ጉዳዩን ለአካባቢው ፖሊስ በመጠቆም ተጠርጣሪዎቹ ከያዙት ቆጣሪ ጋር እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

መሰል እኩይ ተግባራትና ማጭበርበሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ሲሆን፤ ክቡራን ደንበኞቻችንም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልገሎት ብቸኛና ህጋዊ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ አቅራቢ መሆኑን አውቃችሁ ከደላሎችና ከአጭበርባሪዎች ራሳችሁን እንድትጠብቁ ሲል አገልግሎቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

(ኢ.ፕ.ድ)

Exit mobile version