Site icon ETHIO12.COM

ከ50 ዓመት በላይ በስህተት ለታሰሩ ሁለት አሜሪካዊያን 36 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ተከፈላቸው

ሁለት አሜሪካዊያን 36 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ተከፈላቸውሁለቱ ዜጎች በማልኮም ኤክስ ግድያ ተጠርጥረው ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በእስር ላይ ቆይተዋል

ግለሰቦቹ ከታሰሩ ከ56 ዓመት በኋላ የታሰራችሁት በስህተት ነው በሚል ምህረት ተደርጎላቸዋል

ከ50 ዓመት በላይ በስህተት ለታሰሩ ሁለት አሜሪካዊያን 36 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ተከፈላቸው፡፡ታዋቂው የጥቁሮች መብት አቀንቃኝ ማልኮም ኤክስ በፈረንጆቹ 1965 በማንሃተን ግዛት ባለ አንድ አዳራሽ በር ላይ ነበር በተተኮሰበት ጥይት ተመቶ ህይወቱ ያለፈው፡፡

የአሜሪካ ፖሊስም በማልኮም ኤክስ ግድያ የጠረጠራቸውን መሀመድ አዚዝ እና ካሊድ እስላም የተባሉ ጥቁር ተጠርጣሪዎችን በህግ ቁጥጥር ስር ያውላል፡፡ እነዚህ ግለሰቦች ላለፉት ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ለሆኑ ዓመታት በስህተት በማልኮምኤክስ ግድያ ተጠርጥረው በእስር አሳልፈዋል፡፡

ቆይቶ ግን የአሜሪካ አቃቢ ህግ ጽህፈት ቤት ግለሰቦቹ የታሰሩት በስህተት ነው በሚል ይቅርታ ያደረገ ሲሆን እስሩን የፈጸመው የኒዮርክ ከተማ ፖሊስ ይቅርታ ጠይቋል፡፡

በዚህ መሰረት ግለሰቦቹ ላለፉት ዓመታት ያላግባብ ለታሰሩበት የ36 ሚሊዮን ዶላር ካሳ የኒዮርክ ከተማ መክፈሉን ቪኦኤ ዘግቧል፡፡ ዴቪድ ሻኒስ የተሰኘው የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ እንዳለው ደንበኞቹ ብእስር ቤት ለተንገላቱበት የኒዮርክ ከተማ 26 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም የኒዮርክ መንግስት ደግሞ 10 ሚሊዮን ዶላር በድምሩ 36 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ተከፍሏል ብለዋል፡፡ የ84 ዓመቱ መሀመድ አዚዝ በህይወት ያለ ሲሆን በማልኮም ወንጀል ተጠርጥሮ አብሮት እስር ለይ የነበረው ካሊድ እስላሚ በፈረንጆቹ 2009 ላይ ህይወቱ አልፏል፡፡ የካሳ ገንዘቡ ለሁለቱም ተጠርጣሪዎች እኩል ይከፋፈላል የተባለ ሲሆን ህይወቱ ያለፈው የካሊድ እስላም ድርሻ ደግሞ ለቤተሰቦቹ እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

አል-ዐይን

Exit mobile version