Site icon ETHIO12.COM

የጎንደር ከተማ በባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላይ ያወጣው አዲስ ውሳኔ

የጎንደር ከተማ አስተዳደር  ከባጃጅ ጋር ተያይዞ ያገጠሙ እያጋጠሙ ያሉና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን በጥናት እንዲለዩ አድርጓል።በጥናቱም ቀላል የማይባሉ የአሰራር ግድፈቶች ስለመኖራቸው አረጋግጧል።ከተማ አስተዳደሩ ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ ባጃጅ ወደ ከተማው እንዳይገባ ክልከላ ቢያደርግም የተለያዩ አካላት ቅንጅት ፈጥረው በሰሩት ሀላፊነት የጎደለው ተግባር በሽ የሚቆጠሩ የወረዳ ባጃጆች ወደ ከተማው እንዲገቡ በማድረግ ህጋዊ የከተማ ባጃጆች ክፉኛ እንዲጎዱ ማድረጋቸውን ጥናቱ አመላክቷል።

– አዲስ ባጃጅ ወደ ከተማው ለማስገባት=70,000 (ሰባ ሺህ ብር ለከተማ አስተዳደሩ የገቢዎች ተቋም ገቢ ማድረግ ይኖርበታል)

– የከተማ ፍቃድ ባይኖራቸውም የነዳጅ ድጎማውን እንዲጠቀሙ የተፈቀደላቸው የከተማ ፍቃድ ለማግኘት 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር ለገቢዎች ተቋም ስለመክፈላቸው መረጋገጥ አለበት)

– ከሰው እጅ ያለ ባጃጅ ወደከተማው በማስገባት የከተማ ፍቃድ ለማግኘት 100,000(መቶ ሺህ ብር ለገቢዎች ተቋም ስለመክፈላቸው መረጋገጥ አለበት)

– ከጉሙሩክ በጨረታ አሸንፈው የከተማ ፍቃድ ለማግኘት ለሚመጡ ባጃጆ 100,000 ብር (ለገቢዎች ተቋም ስለመክፈላቸው መረጋገጥ አለበት)

– ከኮድ ሁለት ወደ ኮድ አንድ ለመቀየር ለሚፈልጉ =30,000(ሰላሳ ሽህ ብር ለገቢዎች ተቋም ስለመክፈላቸው መረጋገጥ አለበት)

– እስከ ህዳር 30 ባለው ቀነገደብ ውስጥ የሚጠበቅበትን አሟልቶ የከተማ ፍቃድ ሳይኖረው ከተማው ላይ አገልግሎት ሲሰጥ የተገኘ ባጃጅ=30,000 ብር ተቀጥቶ ከከተማው እንዲወጣ የሚደረግ ሲሆን ተግባሩም ከህዳር 19/2015 እስከ ህዳር 30/2015 ዓ/ም ብቻ የሚፈፀም ይሆናል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር  ከባጃጅ ጋር ተያይዞ ያገጠሙ እያጋጠሙ ያሉና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን በጥናት እንዲለዩ አድርጓል።በጥናቱም ቀላል የማይባሉ የአሰራር ግድፈቶች ስለመኖራቸው አረጋግጧል።ከተማ አስተዳደሩ ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ ባጃጅ ወደ ከተማው እንዳይገባ ክልከላ ቢያደርግም የተለያዩ አካላት ቅንጅት ፈጥረው በሰሩት ሀላፊነት የጎደለው ተግባር በሽ የሚቆጠሩ የወረዳ ባጃጆች ወደ ከተማው እንዲገቡ በማድረግ ህጋዊ የከተማ ባጃጆች ክፉኛ እንዲጎዱ ማድረጋቸውን ጥናቱ አመላክቷል።

እነዚህንና ሌሎችንም ግኝቶች መሰረት በማድረግ ከተማ አስተዳደሩ አዳዲስ ውሳኔዎችን ለመወሰን የተገደደ ሲሆን ወሳኔዎችን ተግባራዊ ለማድረግም የተለያዩ ኮሚቴዎችን አቋቁሟል።ውሳኔውን ለማደናቀፍና የመንግስትንና የህዝብን ጥቅም በማሳጣት የራሳቸውን ፍላጎት ለማሟላት የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች የሚያጋጥሙ ከሆነም ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ ለመውሰድ በሚያመች መንገድ ልዩ የምርመራ ቡድን እንዲቋቋም ተደርጓል።

ተግባሩን በውጤታማነት ለመምራት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችም እንዲጠናቀቁ ተደርጓል። ጎን በጎንም የመንግስትንና የህዝብን ጥቅም በማሳጣትና ተግባሩን ለማደናቀፍ የሚሞክሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ለማጣራት የሚያስችል ስራ ተሰርቷል። የከተማ ፍቃድ ሳይኖራቸው አላቸው የሚል መረጃ በመስጠት ግለሰቦችን ላልተፈለገ ወጭ የዳረጉ አካላትን ለይቶና ከግለሰቦች የሚመጣን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ምርመራም የሚካሄድ ይሆናል።

ውሳኔው ተግባራዊ ይሆን ዘንድ አስፈላጊውን እገዛ ከማድረግ ይልቅ ለማደናቀፍ የሚሞክሩና ያለከተማ አስተዳደሩ እውቅና በራሳቸው ስልጣን የወረዳ ባጃጅ አስገብተው በተገኙ አካላት ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃም ለመውሰድ የምንገደድ ይሆናል።ህጋዊ ሆነው ሳለ ኮምፒዩተር ያልገባላቸው ካሉ በጥንቃቄና በጥልቀት በማጣራትና እውነታውን ፈልገን በማግኘት መፍትሄ የምንሰጥ ሲሆን የተሳሳተ መረጃ በመያዝ ለማጭበርበር የሚሞክር ካለ ሰንዶችን ይዘን የምርመራ አካል የምናደርግ ይሆናል።

   የጎንደር ከተማ አስተዳደር

Exit mobile version