Site icon ETHIO12.COM

የትህነግ ታጣቂዎች ከምሽግ እየወጡ ነው፤ ኤርትራና ኢትዮጵያ ተስማምተዋል

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ታጣቂ ሃይሎች ከመሸጉበት ግንባር እየወጡ መሆናቸውንና መንግስት ከኤርትራ አቻው ጋር የሰራዊት ንቅናቄን በተመለከተ መስማማታቸውን አምባሳደር ባጭ ደበሌ አስታወቁ። የቀድሞው ጄነራል ከትግራይ የሚወጡትን ተለያዩ መረጃዎች ከማድመጥ ምድር ላይ በተገባር እየሆነ ያለውን ማስተዋል እንደሚበጅም አመልክተዋል።

ባላቸው መረጃ ከሰባት ቀን በሁዋላ የትህነግ ታጣቂዎች የታጠቁትን ከባድ መሳሪያ እንደሚያስረክቡ ያመለከቱት ባጫ ደበሌ፣ ታጣቂዎቹ ከያዙት ምሽግ በወጡባቸው አካባቢዎች የመከላከያ ሰራዊት መተካቱንም ገልጸዋል። ቦታዎችን በስም አልጠቀሱም።

የከባድ መሳሪያ ማስረከብያ ጊዜው በተያዘለት ዕቅድ መሰረት አለመከናወኑንን ሳይሸሽጉ ከሳምንት በሁዋላ ቀን ጠቅሰው በሰጡት ማብራሪያ አምብሳደር ባጫ እንዳሉት የከባድ መሳሪያ ማስረከቡ ሂደት ሲጠናቀቅ የኤርትራ ሃይሎች ከትግራይ ክልል የያዙትን አካባቢ በሚለቁበት አግባብ ሰላማዊ ስምምነት መፈጸሙን ገልጸዋል። “የኤርትራ ወታደሮች ግድያ እየፈጸሙ ነው” በሚል ስለሚሰማው የትህነግ አቤቱታና የደጋፊዎቹ ሮሮ ምላሽም ሰጥተዋል።

“ክትትል ይደረጋል” በማለት ምላሻቸውን የጀመሩት ባጫ ጉዳዩ ተራ የስም ማጥፋት እንደሆነና የሚባለው ሁሉ ውሸት እንደሆነ አመልከተዋል። የኤርትራ መንግስት በተደጋጋሚ ከትህነግ የሚሰነዘርባቸው ማስፈራራትና ትንኮሳ እንደሚያሰጋቸው፣ ሮኬትን ጨምሮ የተለያዩ ጊዚያት ጥቃት እንደተሰነዘረባቸው ሲገልጹ እንደነበር ይታወሳል። አቶ ጌታቸው ረዳም ኤርትራን በሮኬትም ሆነ በተለያዩ መልኩ ማጥቃት እንደሚቀጥል መናገራቸው አይዘነጋም። ትህነግ በኤርትራ መንግስት ለመለወጥ አቅዶ እንደሚሰራ ከበፊት ጀመሮ መሪዎቹ ሲያስታውቁ ነበር።

ከለውጡ በሁዋላ ግንኙነታቸውን ያደሱት ኢትዮጵያና ኤርትራ የጸጥታና የደህንነት ውል መፈረማቸውን የሚጠቅሱ የኢትዮጵያ መንግስት እስከፈቀደ ድረስ የኤርትራ ጦር ላይ የትህነግ ሃይሎች ልዩ መብት ሊያገኙ የሚችሉበት ምንም ዓይነት መክንያት ሊኖር እንደማይገባ ይገልጻሉ። መንግስት ከፈለገ ኤርትራን ጨምሮ ሌሎችን አገራት ድጋፍም መተየቀ የሚያስችለው ህጋዊ ስልጣን አለው።

ያም ሆኖ አምባሳደር ባጫ እንዳሉት ኤርትራና ኢትዮጵያ ከትጥቅ ማስፈታቱ በሁዋላ ኤርትራ ወታደሮቿን የምትስብበት መንገድ በስምምነት ተቋጭቶ ተግባራዊነቱ ብቻ እንደሚጠበቅ አመልክተዋል። አምባሳደሩ አምስት ጉዳዮችን አንስተው ስለ ናይሮቢው ዝርዝር አፈጻጸም እንዲያብራሩ ለተጠየቁት ሲመልሱ እንዳሉት ህዝብ መመለከት ያለበት መሬት ላይ ያለውን እውነታ ብቻ መሆን እንደሚገባው ተናግረዋል።

ሽሬ ላይ ከሁለቱም አካላት የተውጣጡ አራት አባላት በስምምነቱ መሰረት የትግራይ ታጣቂዎች ወደ ካምፕ በሜገቡበትና በተመሳሳይ ጉዳዮች የአፈጻጸም ስልት ለመንደፍ ስብሰባ እያካሄዱ መሆኑንንም ገልጸዋል። ሰላም እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ሁሉም ወገን ማንም ከሚያራግበው የፈጠራ ወሬ ተላቆ በተገባር እየሆነ ያለውም ብቻ በማየት ድጋፉን መግለጽ እንደሚገባ አምባሳደሩ አመልክተዋል።

በትህነግ በኩል መንግስትን ከአማራ፣ አፋርና ኤርትራ ጋር ለማጋጨት ሆን ተብሎ ዘመቻ መጀመሩን ጠቅሰን መዘገባችን፣ ጀነራል ጻድቃን “ስምምነቱ አብረው የተሰለፉትን ሃይሎች ይበትናል” ሲሉ በትግርኛ መናገራቸውን፣ እንዲሁም ትህነግ አሁን ላይ ቢፈቀድለት እንኳ ጦርነት የማካሄድ አቅምና ሞራል እንደሌለው ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። ኦባሳንጆ ከስድስት መቶ ሺህ በላይ አምራች ሃይል እንደሞተ ጠቅሰው መናገራቸውና በትግራይ የወደመውን መልሶ ለመገናባት የአንድ ትውልድ እድሜ እንደሚፈጅ ማስታወቃቸው በትግራይ ተወላጆች ዘንዳ ክፉኛ መደናገጥ መፍጠሩ እየተሰማ ነው።

ከሃምሳ ዓመት በሁዋላ ለትግራይ ህዝብ ዙሪያውን ጠላት ከማትረፍ የዘለለ ፋይዳ እንዳልፈየደ አፍቃሪዎቹ ሚዲያዎች እየገለጹ ነው። ቀደም ሲል ከደርግ ጋር በነበረው ውጊያ ስልሳ ሺህ ገደማ ወጣቶችን እንዳጣ፣ ነገር ግን በውጤቱ መንግስት መሆን እንደቻለና ” ጦርነት ባህሉ የሆነ፣ ተራራ የሚያንቀጠቅጥ ትውልድ ፈጥሬያለሁ” ሲል የነበረው ትህነግ አሁን ለሞቱት ህጻናትና ወታቶች፣ እንዲሁም ጡረተኞች ደም ምን አድሮ ሲጠየቅ ምን ማላሽ እንደሚሰጥ ከሰላም ስምምነቱ በሁዋላ ትልቅ አጀንዳ ሆኗል። አብዛኞች እንደሚሉት አሁን ላይ ትህነግ በትግርኛ ሌላ፣ በድርድር ላይ ሌላ እያወራ በሰነድ ላይ የተለየ ፊርማ እየኖረ የሚያደናግረው ይህ ተጠያቂነት እንደሚመጣ አስቀድሞ በማወቁ ነው። በይፋ አይነገር እንጂ ሽሬ ላይ ከህዝብ ጋር በተደረገ ስብሰባ ይህ ጉዳይ በለቅሶ ጭምር ተነስቷል።

ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች ሁሉ ንጹሃንን ጨምሮ ወታደሮች መሞታቸው ሃቅ ቢሆንም፣ ትህነግ ወደ ደብረብርሃን ተጠግቶ ዳግም በዘመቻ በሁሉም ግንባር ተሸንፎ ሲወጣ ከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ እንደደረሰበት ” ሶስት መቶ ሺህ በላይ ወጣቶች ህይወት መንግስትን እንጠይቃለን” ሲሉ የባይቶና አመራሮች በጀርመን ድምጽ አማካይነት ከትግራይ መግለጫ መስተታቸው ይታወሳል። አሁን ኦባሳንጆ ከሉት ጋር ሲዳመር ቁጥሩ ይንራል። ይህ ሁሉ ወጣትና አምራች ሃይል ለምን ሲባል እንዳለቀ፣ ውጤቱ ምንን አስከተለ … ጉዳዮች ቀጣይ አጀንዳ እንደሚሆኑ ከወዲሁ ምልክቶች እየታዩ ነው።

ከአንዳንድ ምንጮች እንደሚሰማው በትግራይ ስልክ፣ ሞባይልና ኢንተርኔት በይፋ ሲለቀቅ ልጆቻቸውን ያጡ ቤተሰቦች ራሳቸው ይፋ የሚያደርጉት መረጃ የትህነግን ቀጣይ ማንሰራራትና በፖለቲካው መስክ በህይወት የመቆየቱ ጉዳይ የሚወስን ስለመሆኑ ነው። በመቀለ ገና ካሁኑ ተያያዥነት ያላቸው ተቃውሞዎች እየተሰሙ ነው። ጦርነት ከቆመ “ልጆቻችን” የሚሉ እየተሰማ ነው። ሁሉም ሆኖ ግን በትግራይ ህዝብ ጦርነት እንደሰለቸው አመልካች መረጃዎች አሉ።

በደቡብ አፍሪካው ስምምነት መሰረት ምንም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ እንደሌለና ትግበራውም በዚህ መልኩ እንደሚካሄድና እየተካሂደ መሆኑንን የኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ አመልክተዋል።

Exit mobile version