Site icon ETHIO12.COM

ከምባታ ባለ 777 ደረጃዎቹ ሀምበሪቾ

የከምባታ ህዝብ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ውስጥ ከሚገኙ ብሔሮች አንዱ ነው።

ውብ ባህሎች እና አስደናቂ እሴቶች ያሉት የራሱ የሆነ የአሥተዳደር ሥርዓት የነበረው በራሱ መንግሥት በንጉሥ ይመራ የነበረ ማኅበረሰብ መሆኑን የአካባቢው ታሪክ አዋቂዎች ይገልጻሉ።

የከምባታ ሕዝብ በተራሮች አከባቢ መስፈሩ ታላቅነቱን ከፍታውን የሚያጎላና በባሕል የበለፀገ መሆኑን ማሳያ አድርጎ ይወስደዋል።

የከምባታ ህዝብ እንደህዝብ የሰፈረበት አካባቢ ደጋማ ቢሆንም ከሰፈረበት የሀምበርቾ ተራራ ዙሪያ እየተስፋፋ በመሄድ እና በሌሎች አከባቢዎች በግብርና: በንግድ እና የተለያዩ የእደ ጥበባት ውጤቶችን በማምረት ከፀሐዩ ሀሩር ራሱን ለመከላከል ቆሜ (ባህላዊ ባርኔጣ) ያመርት እና ይጠቀም ነበር።

• የሀምበሪቾ ተራራ የከምባታ ህዝብ ምልክት

ከምባታን ከሚገልፁት ነገሮች አንዱ የአካባቢው ማህበረሰብ የሰፈረበት የሀምበሪቾ ተራራ ነው።

ሀምበሪቾ ተራራ ከአዲስ አበባ 260 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በደቡብ ኢትዮጵያ በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ ውስጥ ይገኛል። እጅግ ውብ ተፈጥሮን የታደለው ይህ ተራራ ከባህር ወለል በላይ 3058 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል።

ሀምበርቾ ተራራ አንጋጫ፣ ዳምቦያ፣ ቃጫ ቢራና ቀዲዳ ጋሜላ በሚባሉ ወረዳዎች መካከል የሚገኝ፣ ዱራሜን ግርማ የሆናት ራሱ ባለ ግርማ ሞገስ ማራኪ ተራራ ነው፡፡

ከኢትዮጵያ 777 መወጣጫ ደረጃ የተሰራለት ብቸኛ ተራራም ነው።

777 ቁጥር ታዲያ በአካባቢው ከሚኖረው ማህበረሰብ ጋር እጅግ የተቆራኘ በመሆኑ የደረጃው አገነባብ ከዚሁ ትውፊት ጋር ትስስር እንዳለው ተደርጎ ቀርቧል።

አካባቢው የተራራ መውጣት ልምድ ባላቸው/ሀይኪንግ የሚወዱ/ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ቱርስቶች ሳይቀር የሀምበሪቾ ተራራ እየተወደደ በመምጣቱ ከንባታን የቱሪስት ማዕከል በማድረግ ላይ አካባቢውን የጎበኙ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ።

Via EBC

Exit mobile version