Site icon ETHIO12.COM

“ከሱዳን ግዛት በመነሳት በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት መፈፀም የሚሞክሩ አካላትን ሱዳን አትታገስልም”

ኢትዮጵያና ሱዳን በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ  ያላቸው ትብብር እንዲጎለብት ተቀራርበው ለመስራት ተስማሙ

ኢትዮጵያና ሱዳን በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ  ያላቸው ትብብር እንዲጎለብት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተቀራርበው ለመስራት ተስማምተዋል።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ፕሬዝዳንት  ጄነራል  አብዱልፈታህ አልቡርሃን ጋር በካርቱም በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።

በውይይታቸውም ኢትዮጵያና ሱዳን በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ  ያላቸው ትብብር እንዲጎለብት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተቀራርበው ለመስራት ተስማምተዋል።

የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ፕሬዝዳንት  ጄነራል  አብዱልፈታህ አልቡርሃን በኢትዮጵያ መንግስትና በህወሓት  መካከል የሰላም ስምምነት በመፈረሙ መደሰታቸውን ገልፀው አገራቸው ለስምምነቱ አፈፃፀም ሙሉ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታውቀዋል።

የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊነት የሚያደናቅፉ እንደዚሁም ከሱዳን ግዛት በመነሳት በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ለመፈፀም የሚሞክሩ አካላትን ሱዳን እንደማትታገስ አረጋግጠዋል። (ዋልታ)

Exit mobile version