“ጎርጎራን አይቶ መራገም የልቡና ጋንግሪን ነው”

እድሜያቸው ከ140፣000 እስከ 230፣000 የሚገመቱ የድንጋይ መሳሪያወች በጎርጎርጎራ እንደተገኙ ይጠቀሳል። ከክርስቶስ ልደት በፊት 7000 ዓ.ዓ. ጀምሮ የሸክላ ስራ ውጤቶች በአካባቢው ይመረቱ እንደነበር ከአካባቢው በተገኙ ናሙናወች ተነስቶ የኖርዲክ አፍሪካ ኢንስቲቱት ይዘግባል [1] ወደ ቅርቡ ዘመን ስንመጣ፣ ጎርጎራ በዐፄ በእደ ማርያም ዜና መዋዕል ላይ ተጥቅሶ የሚገኝ ሲሆን፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለጥንቶቹ የኢትዮጵያ መሪዎች ማረፊያ እየሆነ መጥቶ በመጨረሻ በአጼ ሱሰንዮስ የአገሪቱ ዋና ከተማ ለመሆን የበቃ ክፍል ነው [2]። የመንዳባ ገዳም በዚሁ ልሳነ ምድር ሲገኝ፣ በ1924 አካባቢውን ጎብኝቶ የነበረው የእንግሊዙ ቺዝማን የገዳሙ አለቃ ፍጹም ስልጣን የነበራቸውና ህግን አምልጦ ገዳሙ ውስጥ የተጠለለ ሰው ማንም እንደማይነካው እንደነበር ይዘግባል[3]። አጼ ሱሰንዮስዋና ከተማቸውን በ1604 ከጉዛራ ወደ ጎርጎራ እንዳዛወሩ በታሪክ ይጠቀሳል። በኋላም በልጃቸው በፋሲልደስ ዘመን መጀመሪያ በዋና ከተማነት የቀጠለ ቢሆንም ቅሉ አጼ ፋሲል ጎንደር ከተማን በዋና ከተማነት በመቆርቆራቸው ዋና ከተማነቱ አቆመ። ለከተማው መዛወር የወባ በሽታ በአካባቢው መኖር እንደምክንያትነት ይገመታል[4]

ጎርጎራ ታሪኩ ለማይገባቸው ሁሉ ሪዞርት ነው። በቃ ዝም ብሎ ለመዝናናት የተገነባ የቅንጦት ፕሮጅርክት ነው። ታሪኩ ለሚገባቸው ግን ጎርጎራ አሽራ ነው። አንዱ የኢትዮጵያ ውበት፣ ልቀት፣ የጥንታዊነት መቆሚያ ማማዋ ነው። ጥያቄው ይህን ቦታ በገባታ ለአገር መርሃ ግብር እንዴት ቅድሚያ ሊመረጥ ቻለ፣ መነሻውስ ምንድን ነው? ማን መርጦ አጸናው? የሚለው በቀናነትና በንጹህ ልቦና ቢጠና ፐሮጀክቱንም፣ አሳቡንም፣አሁን ያለበትን ደረጃ ከማድነቅና ይበልጥ እንዲያምር ከማገዝ የዘለለ ዜናም ሆነ ማጠልሸት ባልሰማን ነበር። ጥቂት ጯሂዎች መሆናቸው ስጋት ላይ ባይጥልም፣ ግን እስከመቼ እንታመማለን? የሚለው ያሳስብላ። መቃወም መልካም ቢሆንም ዘወትር ለመራገም ማታ ማታ ሸሚሽ እየቀየሩ መጮህ ይደንቃል። ደግነቱ የኢትዮጵያ ህዝብ 120 ሚሊዮን ይልቃል። ዌኪፕዲያ ስለ ጎርጎራ ይህን ይላል

ጠቅላይ ሚኒስትር በንስር ዓይን ያዩት ጎርጎራ ወይም ጐርጎራ (የድሮው ጎርጎራ) በጣና ሐይቅ ሰሜን የሚገኝ ልሳነ ምድርና ከተማ ነው። ጎርጎራ ከማሪያም ግምብ (አዲሱ ጎርጎራ) 5ኪሎ ሜትር በስተ ሰሜን ምስራቅ ሲገኝ፣ ከደብረሲና ደግሞ 5ኪሎሜትር በስተ ምዕራብ ይገኛል።

See also  ለአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 6.7 ቢሊየን ችግኝ መዘጋጀቱ ተገለፀ

ቀደም ባለው ዘመን የመንግሥት ስልጣን ላይ የሚገኙ አመራሮች በድብቅ ይዝናኑባት እንደነበረ የሚነገርላት ‹‹ጎርጎራ›› በገበታ ለሐገር ፕሮጀክት ተፈጥሯዊ ይዘቷን በጠበቀ መልኩ ታሪክን አጉልታ የኢትዮጶያን ልክ ከሚያሳዩ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ እንድትሆን ስትመረጥ ያንቋሸሹና ሊተገበር የማይችል ተራ የቅንጦት አሳብ እንደሆነ አሽሟጠው የተናገሩ ነበሩ።

“አገር ሊያፈርሱ ይተጋሉ” በሚል በተወሰኑ መንደረተኞችና የሚከፈላቸው የለሊት አቀንቃኞች ሳያሰለስ ቀን በቀን የሚሰደቡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሁሉንም ጆሮ ዳባ ብለው ጎርጎራን በሃሳብ ሳይሆን በተግባር እውን ለማድረግ ሰሩ። ትችቱ፣ ውግዘቱና ጎርጎራ እኩል ጊዜ መቁጠር ጀመሩ። ጎርጎራ ጥንታዊነቱን ይዞ ሊጠናቀቅ ሶስት ወራት እንደቀረው ተበሰረ።

አብይ የገለጿት ሽሽጓ የታሪክ ማማ – ጎርጎራ

ኤስድሮስ ወደ ጦርነት ሲያመራ የድንግል ማርያምን ታቦት በመያዝ ለውጊያ ይዘምታል፡፡ ኤስድሮስ ሽፍቶቹን አሸንፎ ድል ስለቀናው ለማስታወሻነት የደብረሲና ማርያም ቤተክርስቲያንን እንዳሳነፀ የገዳሙ ታሪክ ያወሳል፡፡ የአፄ አምደ ጽዮን የጦር ባለሟል ኤስድሮስ የትውልድ ስፍራ ደብረሲና በመሆኑ “የደብረሲና ማርያም” ስያሜ ከጦር አዛዡ የትውልድ መንደር ጋር እንደሚተሳሰርም የታሪክ ድርሳናት ይጠቁማሉ፡፡ “ጎርጎራ” የሚለው ስያሜም አካባቢው ላይ ሸፍተው ከነበሩት አራት ሽፍቶች አንዱ የሆነው “ባሻ ጐርጐጎር” የተወሰደ እንደሆነ በአፈ-ታሪክ ይነገራል፡፡

የኢትዮጵያን ቀንደኛ ጠላቶችና ቁንጮ ባንዶችን ጠርጎ ፊቱን ሙሉ በሙሉ ወደ ልማት ለማዞር ዝግጅት ላይ መሆኑንን ያስታወቀው መንግስት ተጨማሪ የገበታ ለአገር ፕሮጀክቶችን ይፋ አድርጎ፣ ሰሞኑንን ጎርጎራ ላይ በመሆን በፕሮጀክቱ አባት አብይ አህመድ አማካይነት “የጎርጎራ ፕሮጀክት የኢትዮጵያን የትናንት ታሪክ፣ የዛሬን እድልና የነገ ሕልም ደምሮ የያዘ ነው” እንደሆነ ተገለጸ። መነገር ብቻ ሳይሆን በገቢር የጎርጎራ ውበት ወጣ። ዜጎች በጎርጎራ እንዲዝናኑ፣ ከቀናነት በተቀዳ ስሜት ጎርጎራን እንዲያደንቁ ተጠየቀ።

ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጎንደር ዳቦ ቤት አስገንብተው ሲያስመርቁ ለሰባት ሰዓታት ስድብ ያወረዱባቸው የ360 “አዋቂዎች” በዳቦ ቤት መገንባትና መመረቅ የተበሳጩበት ምክንያት አድሮ ከመካከላቸው በሚነሳ ነፋስ የሚገለጽ ቢሆንም በተመሳሳይ የጎርጎራን ፕሮጀክት ወቅጠውታል። አልሆነም እንጂ አፍርሰውታል።

“መጨረስ አላማችን ነው” በሚል ብሂላቸው የሚታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ የ“ገበታ ለአገር” ፕሮጀክት አካል በሆነው ጎርጎራ ጉብኝት አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “ጎርጎራ ውስጥ ታሪካችን፣እድላችንና ሕልማችን አለ” ሲሉ በርካቶች የጎርጎራን ታሪካዊ ይዘትና አሻራ ወደሁዋላ እንዲያዩ ተገደዋል። ተሳዳቢዎችም በማንቋሸሽ መንገዳቸው አሁንም እየፈሰሱ ናቸው። ጎርጎራ የቱሪስት መናኸሪያ ሆኖ በባዕዳን ሲወደስ በጥቂት የገዛ ልጆቹ እንዲራከስ ይሰራል።

See also  ከተከዜ ግድብ "ተመቷል" ዜና ጀርባ ያለው ደባ !

“ትናንት ታሪካችን ነው፤ዛሬ እድልና ነገ ደግሞ በምናብ የምናየው ሕልማችን ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎርጎራ ሶስቱን ቁልፍ ጉዳዮች አጣምሮ መያዙን ገልጸዋል።
የጎርጎራ ታሪክ በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ መጠበቅ ባለመቻሉ ምክንያት ያለውን “ግርማና መስህብ እያጣ እንደነበር” ተናግረዋል። በፕሮጀክቱ አማካኝነት ታሪካዊ ስፍራውን ዳግም እንዲወለድና እንዲታደስ በማድረግ ወደ ነበረበት ክብር መመለስ ብቻ ሳይሆን ልቆ መታየትን አሳይተናል እያሉ በተግባር የሚያሳዩትን መሪ “አገር ሊያፈርስ የተነሳ” በሚል አፍራሽ ስብዕናቸው በሚከፈላቸው መጠን ሊያወግዙ ማታ ማታ ይሰለፋሉ።

በጎርጎራ ፕሮጀክት የተከናወነው ስራ የትውልድ መደመርን ያሳየ መሆኑን በመጠቆም። “ጎርጎራ ትናንት፣ዛሬና ነገን ያስተሳሰረ ድንቅ ስራ ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ አምራና በልጽጋ የምትታይበት ቦታ መሆኑንም ስፍራው ላይ ሆነው ሲያስረዱ፣ ተሳዳቢዎቹ በምናብ አለም ሆነው ህዝብ በአይኑ የሚያየውን ሃቅ ልያሳንሱና ጨክነው ሃሰት እንደሆነ ይሰብካሉ።

ፕሮጀክቱ ታሪካዊ ከመሆኑ ውጪ ጥራት፣ብዛትና ቴክኖሎጂን በሚገባ ያስተሳሰረ ነው ብለዋል። “ጎርጎራ ትውልድ በታሪክ ውስጥ ሊሞላው የሚገባውንና የጎደለውን ሞልቶ እንዲሁም የነበረንን ማነጽና ማላቅ እንደሚቻል የታየበት፤የኢትዮጵያን ተስፋዎች፣ሕልሞችና የምኞታችንን ልክ ያመላከትንበት ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ኢትዮጵያውያን ጎርጎራን መጎብኘትና ሌሎች እንዲጎበኙት ማድረግ እንደሚኖርባቸውም ገልጸዋል። የትኛውም ጎብኚ ጎርጎራን በማየት ያለ ምንም አስረጂ የኢትዮጵያን ታሪክ መማር፣ የኢትዮጵያን ልክ ለማወቅና የኢትዮጵያን ሕልም ለመረዳት እንደሚችል ተናግረዋል።
ጎርጎራ ለትውልድ የሚተላለፍ አኩሪ ስራ መሆኑንም እንዲሁ መግላፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል። “ገበታ ለአገር” ፕሮጀክት ጎርጎራን ጨምሮ ሌሎች ኢትዮጵያ ያሏትን የተፈጥሮ ሀብቶች ውበት እንዲታይና እንዲጎላ ማድረጉን አመልክተዋል።

በቀጣይ ወደ ትግበራ የሚገባው “ገበታ ለትውልድ” ፕሮጀክት የኢትዮጵያን የትናንት ታሪክ፣የዛሬ እድልና የነገ ሕልም በሚያሳይ መልኩ የቱሪዝም ልማት ስራዎች እንደሚከናወኑ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያውያን ብዙ እምቅ የቱሪስት ሀብቶች ፈልቅቆ በማውጣትና በመጠቀም ለትውልድ የሚሸጋገር ስራ ማከናወን እንደሚገባቸውም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ያስገነዘቡት።

“ያደጉ አገራት የእድገት ጫፍ ላይ ደርሰው ሀሳባቸው እያረጀ መጥቷል፤ ኢትዮጵያ እያደገች ነው ወደ ነበርንበት ብቻ ሳይሆን ከዛ ባሻገር ወደ መታደስና ሕዳሴ እየመጣች ነው” ብለዋል።

See also  ኢትዮ-ቴሌኮም፡ ያሸነፈው የቴሌኮም ተቋም ለኢትዮጵያ ምን ይዞ ይመጣል?

ትውልዱ ይሄንን በመገንዘብ ያማረና ለትውልድ የሚያሸጋገር ስራ በየአካበቢው እንዲሰራ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል። የጎርጎራን የዛሬ መልክ ያዩ ይህን አለማድነቅ የልቡና ጋንግሪን እንደሆነም እየገለጹ ነው። ሶማሌና ትግራይ የሚጀመሩት ፕሮጀክቶች ይፋ ሲሆኑ ደግሞ ምን እንደሚባል ለመስማት በጉጉት ለሚጠብቁ ምላሹ “ወሬው እየተደለቀ፣ ሪባኑ ይቆረጣል” ነው።

Leave a Reply