Site icon ETHIO12.COM

የዱባ ፍሬን የመመገብ የጤና ጥቅሞች

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

  1. ለልብ ጤናማነት

የዱባ ፍሬ በቀን ውስጥ ልናገኘው የሚገባውን የማግኒዝየም መጠንን በግማሽ ስለሚይዝ ለልብ ጤናማነት ለአጥንት እንዲሁም ለጥርስ እና ለደም ስሮች ከፍተኛ ጠቃሚነትም አለው፡፡ ማግኒዝየም ድንገተኛ የልብ ሕመምን እና ስትሮክን የመከላከል ጥቅምን ይሰጣል፡፡

  1. በሽታ የመከላከል አቅምን ማዳበር

ዚንክ የሚባለው ንጥረ ነገር በዱባ ፍሬ ውስጥ ይገኛል፡፡ ዚንክ ለሌሎች ዕድገትና ክፍፍል ውስጥ፣ እንቅልፍ፣ የማሽት እና የመቅመስ ችሎታችን እና ለዓይን ለቆዳ ጤና ጠቃሚ ነው፡፡

  1. በኦሜጋ 3 የበለፀገ ነው

የዱባ ፍሬ እንደ ተልባ እና ሌሎች ፍሬዎች በጣም ጠቃሚ በሆነው በኦሜጋ 3 የበለፀገ ነው፡፡

  1. ለፕሮስቴት ጤናማነት

ለወንዶች ጤንነት ጠቃሚነቱ የተረጋገጠው የዱባ ፍሬ በተለይም ለፕሮስጤት ጤናማነት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ጥናቶች አሳይተዋል፡፡

  1. ፀረ ስኳር ሚና

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ የዱባ ፍሬ ኢንሱሊንን መጠን በማመጣጠን ከስኳር ሕመም ጋር ተያይዘው የሚመጡ ሕመሞችን ይከላከላል፡፡

  1. ላረጡ ሴቶች

የተደረገ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ የዱባ ፍሬ ጠቃሚ የሆነውን የኮሌስትሮል ዓይነት በመጨመር እና የደም ግፊት፣የእራስ ምታት፣የመገጣጠሚያ ሕመሞችን በመቀነስ ጠቃሚነትን ይሰጣል፡፡

  1. ለጉበት እና ልብ ጤናማነት

በፋይቦር፣የአንቲኮክሲደንት እና ጤናማ ቅባት የበለፀገው የዱባ ፍሬ ለልብ እና ለጉበት ጠቃሚም ነው፡፡

  1. ለጥሩ እንቅልፍ

በዱባ ፍሬ ውስጥ በብዛት የሚገኘው ትራይፕቶፋን የሚባል ኦሚኖ አሲድ ሰውነታችን ወደ ሴሮቶኒን ቀጥሎም ወደ ሜላቶኒን የእንቅልፍ ሆርሞን በመቀየር ይጠቀምበታል፡፡ ከእንቅልፍ በፊት የዱባ ፍሬን መመገብ ለሰውነታችን የሚገባውን ዕረፍት እንዲያደርግ ይረዳዋል፡፡

እባክዎን ለወዳጆችዎ ያካፍሉ! ጤና ይስጥልኝ

Exit mobile version