Site icon ETHIO12.COM

ተንቀሳቃሽ ንብረትን ዋስትና በማስያዝ የብድር አገልግሎት ማግኘት የሚያስችለው አዋጅ በቅርቡ ይፋ ይደረጋል

ተንቀሳቃሽ ንብረትን ዋስትና በማስያዝ የብድር አገልግሎት ማግኘት የሚያስችለው አዋጅ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ገለጹ።

በኢትዮጵያ ካሉት ዜጎች  አንጻር ብድር የወሰዱ ዜጎች እጅግ አነስተኛ መሆናቸውንም የሚያነሱት ገዢው በሀገሪቱ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች እስካአሁን ከ330ሺ ለማይበልጡ ስዎች ብቻ ብድር መስጠታቸውን ገልጸዋል። በአንጻሩ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ከ6 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ብድር መስጠታቸውን ነው ያነሱት።

አሁን ላይ ይህን ችግር ለመፍታት ተንቀሳቃሽ ንብረትን በዋስትና በማስያዝ የብድር አገልግሎት የሚሰጥበት አዋጅን ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁን ነው የጠቆሙት። በዚህም በተለይ አርብቶ አደሩ እና አርሶ አደሩ እንስሳትን፣ ግመሎችን ፣ የግል ደኖችን፣ የመሬት መጠቀሚያ ደብተሮችን እና የመሬት መብትን በማስያዝ እና በሌሎችም ብድር ማግኘት የሚችል መሆኑን ነው ያነሱት።

ይህ አዋጅም በቅርቡ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ይፋ እንደሚደረግምና ይህ አዋጅም ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ አንጻር ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መሆኑንም ተናግረዋል። በየአካባቢው የሚገኙ የባንክ ቅርንጫፎችና የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትም ዝግጅት  እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

Exit mobile version