Site icon ETHIO12.COM

ኢትዮጵያ Poverty Paradox ውስጥ አይደለችም?

የኢትዮጲያ ጠቅላላ ምርት/GDP በ111.27 ቢሊየን ዶላር ከሰሃራ በታች ሶስተኛው ትልቁ ነው! ነገር ግን በኢትዮጵያ ኢኮኖሚው በምግብም ሆነ ከምግብ ውጪ በሆነ የድህነት መለኪያ (የፀጥታ እና የደህንነት ዋስትናን ጨምሮ) ባለብዙ ጉድለቶች ነው።

ዓለም አቀፍ የገቢ ልዩነቶችን እንመልከት…..

  1. ዝቅተኛ ገቢ/Low income ማለት፡- በዓመት አንድ ግለሰብ በአማካይ ከ1,046ዶላር በታች የሚያገኝ ማለት ሲሆን (አሁን ላይ በኢትዮጲያ ምንዛሬ አንድ ግለሰብ በአማካይ 54ሺ ብር ወይም በአማካይ በወር 4,500 ብር የሚያገኝ እንደማለት ነው)፡፡
  2. ዝቅተኛ መካከለኛ ገቢ/Lower-middle income ማለት፡- በዓመት አንድ ግለሰብ በአማካይ ከ1,046 እስከ 4,095ዶላር መካከል የሚያገኝ ማለት ሲሆን (አሁን ላይ በኢትዮጲያ ምንዛሬ አንድ ግለሰብ በአማካይ ከ54ሺ ብር እስከ 212ሺ ብር ወይም በአማካይ በወር ከ4,500 ብር እስከ 17ሺ ብር የሚያገኝ እንደማለት ነው)፡፡
  3. ከፍተኛ መካከለኛ ገቢ/ Upper-middle income ማለት፡- በዓመት አንድ ግለሰብ በአማካይ ከ4,095 እስከ 12,695 ዶላር መካከል የሚያገኝ ማለት ሲሆን (አሁን ላይ በኢትዮጲያ ምንዛሬ አንድ ግለሰብ በአማካይ ከ212ሺ ብር እስከ 660ሺ ብር ወይም በአማካይ በወር ከ17ሺ ብር እስከ 55ሺ ብር የሚያገኝ እንደማለት ነው)፡፡
  4. ከፍተኛ ገቢ/ High income ማለት፡- በዓመት አንድ ግለሰብ በአማካይ ከ12,695 ዶላር በላይ የሚያገኝ ማለት ሲሆን (አሁን ላይ በኢትዮጲያ ምንዛሬ አንድ ግለሰብ በአማካይ ከ660ሺ ብር ወይም በአማካይ በወር ከ55ሺ ብር በላይ የሚያገኝ እንደማለት ነው)፡፡

ጥያቄ፦ ኢትዮጵያ #ዝቅተኛ ወይስ #ዝቅተኛ_መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ነች?

ለምሳሌ፡- በኢትዮጲያ የነፍስ ወከፍ ገቢ በመንግስት ሪፖርት 1,212ዶላር (ማለትም #ዝቅተኛመካከለኛገቢ ደረጃ) ሲሆን በአለም ባንክ ግምት(የኢትዮጵያ ህዝብ ቢያንስ 117 ሚሊዮን ቢደርስ የሚለው ግምት ተሰርቶ) በኢትዮጲያ የነፍስ ወከፍ ገቢ 960 ዶላር (ማለትም #ዝቅተኛ_ገቢ ደረጃ) መሆኑን ያሳያል እንዲሁም የአለም ባንክ ኢትዮጲያ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ዝቅተኛ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት ተርታ የመሰለፍ ውጥን አላት ይላል (በቅርቡ መንግስት ባወጣው መረጃ ዝቅተኛ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት ተርታ ደርሰናል ብሏል)፡፡

የነፍስ ወከፍ ገቢ የሚሰላው ኢኮኖሚው በዓመት ውስጥ ካንቀሳቀሰው ጠቅላላ ሃብት (GDP) ለጠቅላላ ህዝቡ ሲካፈል የሚመጣው ቁጥር ቢሆንም የመጣው ስሌት ለሁሉም ሰው ይደርሰዋል ማለት አይደለም! የነፍስ ወከፍ ገቢው ትልቅ ሆኖ ጥቂቶች ሃብታም ሆነው ብዙዎች ድሃ የሆኑበት ኢኮኖሚ ሊኖር ይችላል፡፡

የነፍስ ወከፍ ገቢ መጠን የኢኮኖሚ እድገትን በቀጥታ አያሳይም! ምክንያታዊ የሃብት ክፍፍልን አያመለክትም። በነገራችን ላይ የገቢ ደረጃ መጠን በየአመቱ ይከለሳል። ከላይ የተጠቀሰው ደረጃ በ2021 መረጃ ላይ የተመሰረተ ነው።

ለምሳሌ፦ ከፍተኛ መካከለኛ ገቢ /Upper-middle income የሚለውን ብንመለከት በዓመት አንድ ግለሰብ በአማካይ ከ4,095 እስከ 12,695 ዶላር ቢያገኝ (አሁን ላይ በኢትዮጲያ ምንዛሬ አንድ ግለሰብ በአማካይ ከ212ሺ ብር እስከ 660ሺ ብር) በሚለው መነሻ እና ከፍተኛው መካከል የ8ሺ ዶላር ወይም የ400ሺ ብር ልዩነት አለ።

ስለዚህ የአለም ባንክ እንደሚለው ሀገራት የተለያየ መጠንን ይጠቀማሉ። የአውሮፓ ሀገራት መካከለኛ ገቢ እና የአፍሪካ ሀገራት መካከለኛ ገቢ ወሰን ሊለያይ ይችላል። (በአውሮፓ መለኪያ ድሃ ሰው በአፍሪካ መለኪያ ሃብታም ሊሆን ይችላል እንደማለት ነው!)።

የነፍስ ወከፍ ገቢ ስሌት በዓመት ቢሊየን የሚያገኘውንም ሃብታም በዓመት ያለምንም ገቢ በሰዎች ድጋፍ የሚኖረውንም ድሃ እኩል ያደርጋል፡፡ ከፍተኛ ጠቅላላ ሃብት (GDP) እንዲሁም ከፍተኛ የነፍስ ወከፍ ገቢ ባለበት ሃገር ድህነት ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች ኑሮ ምንም መሻሻል የሌለው ሲሆን Poverty Paradox ይባላል፡፡

በዚህ መለኪያ ኢትዮጵያ Poverty Paradox ውስጥ አይደለችም

Source the ethiopian economist view

Exit mobile version