ከሰላም ስምምነቱ በኋላ.. የትህነግ የፊት ደጀኖች ምን እያሉን ነው?!

ጠላት የቱንም ያህል ርቀት ተጉዞ ሁሉን ዐቀፍ ዘመቻ ቢያደርግም፥ የኢትዮጵያ ሕዝብ ራሱንና እናት አገሩን በጀግንነት ተከላክሎ ማስከበር የሚችል ለነፃነቱና ለክብሩ ለኢትዮጵያዊነቱ መስዋዕት ለመክፈል ዛሬም ልክእንደትናንቱ እንደአባቶቹ የማይበገር በባንዳዎች ወሬ የማይፈታ ጀግና ሕዝብ መሆኑን ኢትዮጵያ አለቀላት ብሎ ላሟረተው ለዓለሙም ሁሉ በአሸዋ ላይ እንደተገነባ ቤት አለመሆኗን በተግባር አስመስክሯል።

በቶማስ ጃጃው

ሐገር ለማፍረስ ለወያኔ በተለይ በፕሮፖጋንዳው መስክ (በሌላው ስለማይችሉ ነው) የፊት ደጀን የነበሩት አፍቃሬ ወያኔ የባንዳ ባንዳዎች ምን እያሉ ነው የሚለውን የራሳቸውን ፕሮፖጋንዳና መስመሩን ተከትለን እንመልከተቸው።
በመጀመሪያው የሕግ ማስከበር ዘመቻ የኢትዮጵያ ጦር ከትግራይ ክልል ከመውጣቱ በፊት

“የኤርትራ ጦር ከኢትዮጵያ ይውጣ የትግራይ እናቶች በኤርትራ ጦር እየተደፈሩ ነው፣ ንፁሃን እየተገደሉ ነው፣ ሹካ ማንኪያ ሳይቀር የትግራይ ሕዝብ ሐብት ንብረት ወደ ኤርትራ እየተዘረፈ እየተጫነ ነው፣…”። በጦርነቱ መካከል እና ወደመጨረሻው ላይ ደግሞ የኢትዮጵያ ጦር ከትግራይ ክልል የጥሞና ጊዜ ለሕዝቡ ሰጥቶ ሊወጣ ሲል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን እቃ እየጫነ ዘረፈ ከሚለው ውጭ በተመሳሳይ ስሙን በሐሰት ለማጥፋት(የኦነግ ሰራዊት በሚል ሽፋን ጭምር ) እንደ ኤርትራ ሰራዊት ለማለት ሞክረዋል። እነዚህ የወያኔ የፕሮፖጋንዳ አራጋቢዎች በአማራ ክልል በጎንደር በኩል ሱዳን የኢትዮጵያን ደንበር ጥሶ ጦሩን ይዞ በጉልበት 80 ኪሎ ሜትር ሲቆጣጠር በቢሊየን የሚቆጠር ሐብት ንብረት ሲያወድም ንፁሃን ላይ ጥቃት ሲያደርስ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ሲያደርግ በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ ሲዘግበቡልን ከነበሩት መካከል አንዱስ እንኳን እንደግለሰብ እስከአሁን ድምፅ ለማሰማት የሞከረ አልሰማንም። አላየንም። ጉዳያቸው እንዳልሆነ ጠፍቶኝ ሳይሆን ነገሩን መዝግቡ ለማለት ነው።

ለወያኔ በተለይ በፕሮፖጋንዳው መስክ በፊት ደጀንነት የተሰለፉት መንገድ ጠራጊዎች (በአማራ ስም ብቻ ሳይሆን የፌደራሊስት ሃይል ነን ብለው በአማራም በሌሎችም በቡድንም ሆነ በተናጠል የሚንቀሳቀሱ የወያኔ የእጅ ስራ የሆኑ ልክእንደ አሻንጉሊት የሚጫወትባቸውና የሚመራቸው ጭምር ያሉበት ነው) ጦርነቱ ወደአማራና አፋር ክልል እየገባና እየሰፋ ንፁሃን ወገኖቻችን በወያኔ እየተጠቁ፣እናቶች እየተደፈሩ፣ ሐብት ንብረት እየወደመ “ጦርነቱ የአብይና የሕወሓት ነው፣ ጦርነቱ እኛን አይመለከትም” ማለትን መረጡ ብቻ ሳይሆን በጦርነቱ የሚሳተፉትንና ይመለከተናል ያሉትን የብልፅግና ወይም የአብይ ወታደር እያሉ ለማሸማቀቅ ሲሞክሩ ታይተዋል።
ከአብይ ወይም ከብልፅግና ጎን መቆም ሊያሸማቀው የሚገባው ወያኔን ወይም አፍቃሬ ወያኔን ሆኖ ሳለ በእነሱ ተቃራኒ የቆመውን ሊያሸማቅቁት ሲሞክሩ የሚሸማቀቅ አካል የሚኖር አይመስለኝም ካለ ግን ችግሩ የሚሸማቀቀው ሰው ነው። አገር እንዳይፈርስ በአማራ ሕዝብ ላይ ሒሳብ እንዳይወራረድበት ጦርነት ያወጀበትን ሃይል ለመፋለም አይደለም ከራሱ ከብልፅግና ከማንስ ጠላት ጋር ቢሆን የሕልውና ጉዳይ ነውና በጠላቴ ጠላት ሂሳብ መተባበሩ ይጠበቃል። ሐገር ለማፍረስ የቆሙ ሰዎች ሳይሸማቀቁ ሐገር ለማዳን የተዋደቁ ሰዎች ሊሸማቀቁ የሚችሉበት ምንም አይነት የሞራል ብቃት የለም። በእንዴትስ አይነት የሞራል ብቃት? ባንዳ ጀሮ ካገኘና አርበኞችን ለማሸማቀቅ ቢሞክር ጥፋቱ የባንዳው አይደለም። ለባንዳዎች መፈንጨት የሾርት ሚሞሪያሞች የድንቁርና መንገስን የንቃተ ሕሊና ማነስን ያመለክታል።

See also  ሞት አቀንቃኝ የግጭት ነጋዴዎች

አማራ ሂሳብ ሊወራረድበት(ማወራረድ ሲገባው) የተከፈተበትን ጦርነት እንዳይከላከል አገሩ እንዲፈርስ እንዲተባበር ከአብይ ወይም ከብልፅግና ጎን መቆም ከሕወሓት ጎን የመቆም ያህል አድርገው ወያኔና አፍቃሬ ወያኔዎች የሚሰጡትን አጀንዳ አምኖ የሚቀበል ሰው የሚያሳየው የብዙሃኑን የንቃተ ሕሊና ደረጃን ነው።
አማራ ራሱን እንዳይከላከል እጅና እግርህን አጣጥፈህ ተቀመጥ ብሎ ያልተቋረጠ የማፍዘዝ የማዳከም የመበታተን ከፍተኛ ዘመቻ የከፈቱበት ለሕልውናው እንደጠበቃ ራሱን እንዲከላከል ለሕልውናው ከፊቱ የቀደሙለት ደግሞ እንደጠላት እንደስጋት ይቆጠር ዘንድ የተደረገው ጥረትና አሁንም የቀጠለው ዘመቻ አዳማጭ ጆሮ ሲያገኝ መመልከት የሚያስደንቅ ነው።

በአፍቃሬ ወያኔዎች አማራ ራሱን እንዳይከላከል በተቀናጀው ሐሰተኛ ትጥቅ አስፈቺ ዘመቻ የአማራ ሕዝብ አላስፈላጊ የሆነ ከባድ መስዋዕትነት እንዲከፍል እንዳላደረጉት፣ አሁን ተመልሰው እኛ ነን ወዳጅህ እኛ ነን የምንቆረቆርልህ ማለታቸው ለእኔ ትርጉሙ እንደሚገባኝ ሁሉንም እንደራሳቸው መቁጠራቸው በአንድ በኩል በሌላ በኩል ደግሞ ለማህበረሰቡ ያላቸውን ንቀት ጥግ መድረሱን ነው። በአማራ ንፁሃን ላይ ጥቃት እንፈፅም፣ ሐብት ንብረት እናውድም፣ እየዘረፍን ጭነን ወደትግራይ ክልል እንውሰድ ይህን የምናደርገው ለሕልውናችን ነውና ተረዱን። አትቀየሙን የሚሉ። አትቀየሟቸው ብትችሉ አመቻቹላቸው አግዟቸው ያሉ መንገድ ጠራጊዎች ከእነሱ በቀር ሌላ ኢትዮጵያዊ እንዴትስ በዚህ መንገድ አድማጭ አገኛለሁ ሞራል ይኖረኛል ብሎ መንቀሳቀስ ይችላል የሚለውን ከእነሱ በስተቀር መመለስ የሚችል ስለመኖሩ እርግጠኛ አይደለሁም።ጦርነቱ አንተን ስለማይመለከትህ እጅና እግርህን አጣጥፈህ ተቀመጥ፤ አይንህን በጨው አጥበን እናሞኝህ ስንለው ያምነናል፤ ብለው አስበው መንቀሳቀሳቸው የሚያስደንቅ ቢሆንም በተቀናጀው ሐሰተኛ ፕሮፖጋንዳቸው እናሞኝህ ሲሉት የተሞኘ የጠላት አጀንዳ አራጋቢ መልሶ ራሱን ወጊ ቁጥሩ የማይናቅ ሰው ፈጥረው ብንመለከትም ነገር ግን ያሰቡትን እኩይ አላማ ጀግናው ሕዝባችን በተባበረ ክንዱ በፅናት ታግሎ እኩይ አክሽፎ መራራ ሽንፈትን አጎናፅፏቸዋል። ምንም እንኳን ሽንፈት የማይሰለቸው ሃይል ቢሆንም ቅሉ!

አማራ ክልልን የፈጠሩትን ክፍለ ሐገሮች ማህበረሰባዊ እረፍት ለማሳጣት አማራ በሚል ስም የሚንቀሳቀሱ አማርኛ ተናጋሪ ወያኔዎችም ሆኑ በፌደራሊስት ሃይሎች በሚል የሚንቀሳቀሱት የወያኔ አሻንጉሊቶች በሰላም ስም ግጭት ለማዋለድ አሁንም እየሰሩ ነው። ከሰላም ስምምነቱ በኋላ የኤርትራ ጦር ይውጣ ወይም ጥቃት እየከፈተ ነው ሲሉ ይሰማሉ ነገር ግን ተስቷቸው የሱዳን ጦር ከኢትዮጵያ ይውጣ ሲሉ አይደመጡም። ከላይ አማራ አማራ ሲሉ ለተመለከታቸው ለአማራ ክልል ተቆርቋሪ ይምሰሉ እንጅ ሽፋኑን ገላልጠው ቢመለከቷቸው ለክልሉ ሰላምና በክልሉ ለሚኖሩ ሕዝቦች ወንድማማችነት ጠንቅ ናቸው።
ለወያኔ በመንገድ ጠራጊነት የተሰለፈው አፍቃሬ ወያኔው ሃይል እሱ እንደሚለው የአማራ ተቆርቋሪ ቢሆን ኖሮ በትግራይ ክልል ተፈፀመ እያለ ካሳየው ተቆርቋሪነት አንፃር ቢችል ከፍ ያለ ያልተቋረጠ ድምፁን ወያኔ ወደአማራ ክልል በሕዝባዊ ማዕበል ጥቃት ከፍቶ ንፁሃን ሲገድል ሴቶችን ሲደፍር ሐብትና ንብረት ሲያወድም ያሰማ ነበር እንጅ እንዴት ይባሱን ወያኔ ይህን የሚያደርገው ለትግራይ ሕዝብ ሕልውና እንደሆነ በማድረግ ሊያቀርብ ይቻለው ነበር?!።

See also  ተበድለን እያለ እንደበዳይ መታየት እስከመቸ?

ጠላት የቱንም ያህል ርቀት ተጉዞ ሁሉን ዐቀፍ ዘመቻ ቢያደርግም፥ የኢትዮጵያ ሕዝብ ራሱንና እናት አገሩን በጀግንነት ተከላክሎ ማስከበር የሚችል ለነፃነቱና ለክብሩ ለኢትዮጵያዊነቱ መስዋዕት ለመክፈል ዛሬም ልክእንደትናንቱ እንደአባቶቹ የማይበገር በባንዳዎች ወሬ የማይፈታ ጀግና ሕዝብ መሆኑን ኢትዮጵያ አለቀላት ብሎ ላሟረተው ለዓለሙም ሁሉ በአሸዋ ላይ እንደተገነባ ቤት አለመሆኗን በተግባር አስመስክሯል።

ወደሚሰማበት ሁኔታ መቀየር ይቻላል። በኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝብ የተሰጠውንና የተፈጠረውን ዕድል በአግባቡ በጥንቃቄ መጠቀምም ያስፈልጋል።

በእብሪት እንደተፈጠረው የጦርነት ሁኔታ በጦርነቱ እንደታየው ስሜት በጦርነቱ እንደተመዘገበው አንፀባራቂ ወታደራዊ ድል አይደለም የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት ለትግራይ ሕዝብም ሆነ ለሕወሓት አሁን ላይ እያሳየ የሚገኘው የወንድማማችነት ስሜት። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በድል አድራጊነት ወደመቀሌ ተጠግቶ መቀሌንም ለመያዝ የሚያስችል ዕቅድ አጠናቆ ሳለ የሰላም ድርድር በሚል ከፍፁም አሸናፊነት በመነጬ በይቅርታ መንፈስ ለወያኔ መሪዎችና ለተቀሩት አብረዋቸው ለመቆም ለሚሞክሩት ታጣቂዎቻቸው የወንድ በር የተሰጠው ቁጥሩ የማይናቅ የትግራይ ሕዝብ በተሳሳተ ፕሮፖጋንዳ የወያኔ መሪዎችን ከሚመለከትበት ሁኔታ ለነገ አብሮነትና ወንድማማችነት፣ለሁሉም በሁሉም የምትገነባውን ኢትዮጵያን ከመገንባት አንፃር እነሱን ደምስሶ መቀሌን ከመቆጣጠር ይሻላል በሚል እንደሆነ ይታመናል። ይህን ወርቃማ ዕድል በአግባቡ መጠቀም አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ።

በመጨረሻም ስለኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ ታምነው ለአመኑበት ጉዳይ የሚከፈለውን ሁሉ ዋጋ ለመክፈል ከፊት ለተሰለፉ ኢትዮጵያን ባንዳም ሆነ ባዳ በጦርነት ሊያፈርሳት እንደማይችል በተግባር ላስመሰከሩ ለእነ ዶ/ር አብርሃምና ለመሰል ከትግራይ ክልል ለተገኙ ትግረኛ ተናጋሪዎች ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል። ይድረሳቸው።

ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት መከበር ሲሉ የሚጠበቅባቸውን መስዋዕትነት ለከፈሉ በተለይም ለጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊታችን መልካም የገና በዓል እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ!

ፎቶው
ለዘመናት አገሩን የበይ ተመልካች አድርጎ በነበረው በኪነጥበብ ባለሙያዎች ሲወደስና ሲወቀስ በኖረው ነገር ግን በእኛ ትውልድ ታሪኩን በቀየረው የኋይል ማመንጫ ብቻ ሳይሆን የፅናት፣ የነፃነት፣ የአንድነታችን ማስተሳሰሪያ ዓርማችን የመደማመጥና የመተባበር ማሳያ ምልክታችን በሆነው በታላቁ የሕዳሴ ግድባችን ጉብኝት ላይ የተወሰደ ነው!

ሰላም ለኢትዮጵያችን!!

Leave a Reply