Site icon ETHIO12.COM

ስለ አዲስ አበባ ጉዳይ ከደንበጫ ወይም ከዳባት ከንቲባ ጋር መነጋገር አይቻልም!

መሸነፍ ከማይሰለቸው ነውርን ጌጥ ካደረገ ኋይል ጋር መመላለስ ባይጠቅምም አሁንም ሽንፈትን ካባ ነውርን ጌጥ ማድረጋችሁ እንደማይጠቅማችሁና ጥሩ ተፎካካሪ ሆናችሁ በሜዳው ለመቆየት እንደማያስችላችሁ ልነግራችሁ እወዳለሁ!

ስለ አዲስ አበባ ጉዳይ ከደንበጫ ወይም ከዳባት ከንቲባ ጋር መነጋገር አይቻልም!

በትናንትናው ዕለት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከአዲስ አበባ ከንቲባ ክብርት አዳነች አበቤ ጋር ለምን ለውይይት ተቀመጣችሁ የሚል ተንጋሎ እንደመትፋት የሚቆጠር ዘመቻ ከፍተዋል።
ዘመቻውን የሚመሩት በተለመደው የአለቃቀስ ባህላቸው ድንኳን ጥለው ንፍሮ ቀቅለው ነጠላ ዘቅዝቀው ተቀምጠው ውለው የማደር ልምድ ያላቸውና በተደጋጋሚ በፎርፌ የተሸነፉት ናቸው። የፎርፌ ተሸናፊዎቹ ያሳዘናቸው ጉዳይ እንዴት በአዲስ አበባ ጉዳይ ከጎንደር ከዳሞት የመጣ ሰው ከከንቲባ አዳነች አበቤ ጋር ለውይይት ይቀመጣሉ በሚል ሽፋን የተደረገ ይምሰል እንጅ ሽፋኑ ሲገለጥ ዋና አላማው ችግሮች በውይይት እንዲፈታ ካለመፈለግ የሚመነጭ ነው። በአዲስ አበባ የሚታዩ ችግሮችን በተመለከተ በውይይት ለመፍታት ውይይት መካሄዱ ለግጭት አሟሟቂዎች ፈፅሞ ምቾት የሚሰጥ አይደለም።

የአማራ ሸኔ አባላት፣ በመንግስት ውስጥ ያሉና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት ውስጥ ለታሪካዊ ጠላቶቻችን የባንዳ ባንዳ ሆነው ከፊት የተሰለፉ የእፍኝት ልጆች፣ የሌሊት ወፎች፣ በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን የማይፈልጉ ኮንትሮባንዲስቶች፣ ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በተቆርቋሪነት ስም እንቀሳቀሳለን የሚሉ ነገር ግን ኦርቶዶክስን የአማራ ብቻ ሐይማኖት ለማስመሰል ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ የሆኑ በደህንነት ክንፉ በእነ ጌታቸው አሰፋ የተመለመሉ ጨዋ ሰባኪዎች፣ መረጃና ማስረጃ ሳይኖራቸው በመሰለኝና በደሳለኝ የጠላትን ሐሰተኛ የተቀነባበረ መረጃን ሳያጣሩ እንደወረደ የሚውጡ የሐሳብ መስጫ ሳጥኖች፣ የይሁዳ ፍየሎች፣ለወገናቸው እየታገሉ የሚመስላቸው ነገር ግን ሁሌም በጠላት መንገድ የሚነጉዱ የ herd mentality ተጠቂዎች፣በጥፋት አቀጣጣይነት(ፍለጠው ቁረጠው እያሉ ስላንኮሻኮሹ)እንደጀግና ቁጠሩን የሚሉና የሚቆጠሩ የኮርኒስ አይጦች፣ ጭር ሲል የማይወዱና የሚዋረዱ የግጭት ነጋዴዎች፣ የመረጃ ምንጫቸው ፌስቡክ የሆኑ ምዕመናን፣ በእኛ ላይ ተንጠልጥለው እኩይ አላማቸውን ማሳካት ያልቻሉና መቼም ቢሆን የማይችሉ ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኞች በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ አግድም አደግነታቸውን በሚያንፀባርቅ መንገድ እንደለመዱት የቱንም ያህል የስም ማጥፋት ዘመቻ መክፈት ቢችሉ ውጤቱ በፎርፌ ከመሸነፍ የሚያድናቸው አለመሆኑን ማስመር ያስፈልጋል።

በአዲስ አበባ የባለቤትነት ጉዳይ ላይ ተንጋለው ከሚተፉት መካከል 99 በመቶ የሚሆኑት መሰረታቸው ከአዲስ አበባ ውጭ የተወለዱና የሆኑ አሁንም ከሐገር ውጭና ከአዲስ አበባ ውጭ በየወረዳው የሚኖሩ ሰዎች ናቸው። እነዚህ መሰረታቸውና ኑሯቸው ከአዲስ አበባ ውጭ የሆኑ ሰዎች ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች በላይ የአዲስ አበባን የባለቤትነት ጥያቄን ከማንሳት አልፈው ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች እኛ እናውቅለታለን የወደፊት እጣ ፈንታውንም እኛ እንወስንለታለን ብለው በድፍረት ለመተንተንና ለመተብተብ ከመነሳታቸው ባሻገር የአዲስ አበባን ነዋሪ እንደእንቅልፋም እንደዘገምተኛ እንደተላላኪ ወይም ባርነትን እንደመረጠ እያስመሰሉ ለመሳደብ ድፍረታቸውን ተጠቅመው አፋቸውን ሲከፍቱ በተደጋጋሚ ታዝበናቸዋል። ሟርታቸውንም እንዲሁ። አዲስ አበባ የአማራና የኦሮሞ ብቻ ሳይሆን የነዋሪዎቿ የሁሉም ብሔሮች አልፎም የአፍሪካ ከተማ ነች ብለን የምናምነውንና ነዋሪ የሆነውን ሰዎች በሞራል አልባነት ሞራል ተላብሰው በድፍረት ሊተቹን ሞክረዋል። አለማፈር!

ሞት መፈናቀል ግጭት ስድብና እርግማን በሚኖርበት እንጅ ሰላም በሰፈነበት መከባበርና መደማመጥ ባለበት በባትሪ ቢፈለጉ የሚገኙ ሰዎች የባሕሪይ መገለጫቸውን ለምን አንፀባረቁ ብለን አንደነቅባቸውም። መስመራቸውም ግልፅ ነው።
እናም የዚህ ረድፈኞች በውይይት ላይ የሚሳተፉ ሰዎችን ስም ለማጥፋት ለማሸማቀቅ ቀድመው የሚዘምቱት ግጭትን ለማዋለድ እንጅ ችግሮችንና ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት ከሚመነጭ ስሜት አይደለም። በነውረኞች የሚሸማቀቅ ባለሞራል ሰው ባይኖርም ቅሉ!

የፎርፌ ተሸናፊዎች ሽንፈትን ካባ ነውርን ጌጥ አድርጋችሁ በአረንቋ ውስጥ እየዳከራችሁ ጊዜያችሁን ከምታጠፉ አንዴ ቆም ብላችሁ አሁን ላላችሁበት አዘቅት የጣላችሁን ምክንያት ብትመረምሩ ሰልፋችሁን ለማስተካከል ብትቸገሩ እንኳን ጥሩ ተፎካካሪ የመሆን ዕድል ይኖራችኋል።
በፎርፌ ላለመሸነፍ በሜዳው እየተጫወታችሁ ለመቆየት እስኪ ስራ ስሩ ብለን እንመክራችኋለን!!

Tomas jajaw telegram

Exit mobile version