Site icon ETHIO12.COM

ምንም ሳያርፍ 13,560 k.m የበረረው ወፍ የአለም ሪከርድ ሰበረ

ምንም ሳያርፍ ከአሜሪካ ተነስቶ እስከ አውስትራሊያ ድረስ(13,560 k.m) የበረረው ወፍ የአለም ሪከርድ ሰበረ።

ይህ ወፍ 13,560 k.m (8,435 miles)ከአሜሪካ Alaska ግዛት ተጉዞ ነው Tasmania Australia የገባው።

ይህ ወፍ ከዚህ ቀደም በሌላ ወፍ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ ሰብሮዋል። አንድም ጊዜ ሳያርፍ ውሀ ምግብ ሳይቀምስ ቀጥታ በሮ 11 ቀን ከአንድ ሰአት ሳያቋርጥ ተጉዞ ወደ Tasmania ሄዶ እስኪያርፍ ድረስ ያለው ሙሉ ጉዞ በሳተላይት ተቀርፆዋል።

እንደ Guinness World Records ዘገባ Godwit (Limosa lapponica) የተባለው ይህ ወፍ የታግ ቁጥሩ “234684,” ነው።

ወፉ የበረረው ርቀት በሌላ አነጋገር ሲሰላ ከለንደን እስከ ኒው ዮርክ ያለውን ርቀት ደርሶ መልስ 2 ተኩል ያክላል። ወይም በሌላ አነጋገር የመሬትን ሙሉ ዙርያ circumference 1/3 ኛ ያክላል።

ወፉ ጀርባ ላይ የታሰረለት የ 5G ሳተላይት ምስል እንደሚያሳየው ወፉ የተነሣው October 13 2022 ነው።

Tech Dad p.k via Ahemed Habib

Exit mobile version