Site icon ETHIO12.COM

በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ

በአሜሪካ የዴሞክራት 117ኛው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ ህወሃትን በመደገፍ ወጥተው የነበሩ ማዕቀቦችና ሌሎችም አስገዳጅ ሕጎችና ረቂቅ ሕጎች ሙሉ በሙሉ መሰረዛቸው ተገለፀ። መረጃውን ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት ነው።

አዲሱ የሪፐብሊካን 118ኛው ምክርቤት ኮንግረሱን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠሩ የዲሞክራቶች ረቂቅ ህጎች ሙሉ በሙሉ ጊዜው ያለፈባቸው ሆነዋል ተብሏል።

የካውንስሉ ሰብሳቢ ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ፣ ይህ እንዲዘገይ ለሰራችሁ የካውንስሉ አባላትና ዩኒቲ ፎር ኢትዮጵያ ትልቅ ምስጋና አለን ብለዋል።

ምክር ቤቱ አክሎም፣ አሁን በዜጎች ላይ እየተከሰተ ባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዙሪያ ምን ማድረግ በሚኖርብን ጉዳይ ዙሪያ ከአዲሱ የኮንግረሱ መሪ ኬቨን ማካርቲ ሃላፊዎች ጋር ንግግር መጀመሩን አቶ አምሳሉ ካሳው ለአባላቱ አስታውቀዋል ሲል ገልጿል።

በተያያዘ ዜና፤ የኢትዮጵያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል፣ ለከፍተኛ ስብሰባ ከእስራኤል ባለስልጣናት በወቅቱ ጉዳይ ጋር ለመወያየት ልዩ የልኡካን ቡድን ዛሬ ከአሜሪካ ተነስቶ ወደ እስራኤል የሚገባ መሆኑን ተጠቁሟል። (#የዓባይልጅ – አዲስ ማለዳ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Exit mobile version