Site icon ETHIO12.COM

ህዳሴ ግድብ – ሁለት ጣና

የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ በበዚህ አመት መጨረሻ በሚካሄደዉ አራተኛዉ ዙር የዉሃ ሙሌት ግድቡ የጣናን እጥፍ የሚያህል የዉሃ መጠን ይይዛል፡፡ የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ አራተኛዉ ዙር የግድቡ የዉሃ ሙሌት ከፍተኛ የዉሃ መጠን እንድይዝ እየተሰራ ነዉ ብለዋል፡፡ ግንባታዉ በተያዘለት ዕቅድ መሰረት እየተካሄደ መሆኑን የገለፁት የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ በዚህ አመት መጨረሻ በአራተኛዉ ዙር የዉሃ ሙሌት የጣናን እጥፍ የሚያህል የዉሃ መጠን ግድቡ እንደሚይዝ ገልፀዋል፡፡

የዉሃ ሙሌቱ ሲጠናቀቅም ከአስራ አንዱ ተርባይኖች መካከል ግማሾቹ ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምሩም አስታዉቀዋል፡፡ ባለፋዉ አመት ኃይል ማመንጨት የጀመሩት ሁለቱ ተርባይኖችም አሁን ላይ ከሚጠበቅባቸዉ 7 መቶ ሜጋ ዋት ሃይል ዉስጥ 5 መቶ 40 ሜጋ ዋት እያመነጩ ይገኛሉ ነዉ ያሉት፡፡

በቀጣይ ቀሪ ተርባይኖች ኃይል ማመንጨት ሲጀምሩም፣ የሃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን በመዘርጋት ዜጎችን የኤልክትሪክ ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

ከዚህ ባለፈም ከሰሞነኛዉ የግብፅ ወቀሳ ጋር ተያይዞ የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ፤ኢትዮጵያ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ መርህን እንደምትከተል አስታዉሰዋል፡፡

በመሆኑም የእነ ግብጽ ወቀሳና ከሰሳ የሚጠበቅ በመሆኑ አሁን ትኩረታችን መሆን ያለበት በግድቡ ግንባታ ላይ ነዉ ብለዋል፡፡

የካይሮ ፖለቲከኞች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በዓለም አደበባይ ኢትዮጵያን መዉቀሳቸዉን እንደቀጠሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ከሰሞኑም ግብጽ ኢትዮጵያ አሳሪዉን ስምምነት መፈረም አለባት ስትል ለአረቡ አለም ወገኖቿና ለአሜሪካ መንግስት አቤቱታ አቅርባለች፡፡

የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ከሰሞኑ በሳዉድ አረቢያ በተካሄደዉ የባህረ ሳላጤዉ አገራት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ አሳሪዉን ስምምነት መፈረም አለባት ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“ለአሁኑ እና ለመጪው ትውልድ የመልማት መብትን የሚያረጋግጥ እና ትብብራቸውን፣ መረጋጋታቸውን እንዲሁም ደኅንነታቸውን ከስጋት የሚጠብቅ በቅን ልቦና ላይ የተመሠረተ ንግግር በማድረግ አሳሪ ሕጋዊ ስምምነት ላይ እንዲደረስ ለኢትዮጵያውያን ወንድሞቼ በድጋሚ ጥሪዬን አቅርባለሁ” ብለዋል ፕሬዝዳንት አል ሲሲ።

የውሃ ደኅንነት ጉዳይ ከአገራቸው በተጨማሪም ሌሎች የአረብ አገራትንም የሚመለከት መሆኑንም አንስተዋል።
አልሲሲ ይህን ሲናገሩ በመድረኩ ላይ የቻይናዉ ፕሬዝዳንት ሺ ጂፒንግም ነበሩ፡፡

ወደፊት በቻይና እና በአረብ አገራት መካከል በሚኖረው ትብብር ውስጥ የአረብ አገራት የውሃ ደኅንነት ጉዳይ ወሳኝ ስለመሆኑ ገልፀዋል፡፡

ብዙም ሳይቆዩ ደግሞ አልሲሲ በአሜሪካ አፍሪካ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ አሳሪዉን ስምምነት መፈረም አለባት ሲሉ ለአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ነግረዋቸዋል፡፡

ወደ መጠናቀቁ የተቃረበውን የታላቁ ሕዳሴ ግድብን የውሃ ሙሌትና የሥራ ሂደት በሚመለከት ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ በተለይ ባለፉት አምስት ዓመታት ድርድር ቢያደርጉም ከስምምነት ላይ ሳይደርሱ መቅረታቸው ይታወሳል።

ኢትዮጵያ ግን አሁንም ለጋራ ተጠቃሚነት በሬ ክፍት ነዉ አሳሪዉን ስምምነት ግን አልሞክረዉም እያለች ነዉ፡፡

በአባቱ መረቀ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107. 8

Exit mobile version