Site icon ETHIO12.COM

ሲኖዶስ ሰላማዊ ሰልፉ መሰረዙን አስታወቀ

ታላላቅ ውሳኔዎችና አህጉራዊ አቋም ይያዝበታል በተባለለት የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ወቅት እንዲካሄድ እለሁድ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ቀን ተቆርጦለት የነበረው ዓቀፍ እና ዓለም አቀፍ የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ቅዱስ ሲኖዶስ መወሰኑንን አስታወቀ።

“በትናትናው እለት ከመንግሥት ጋር ባደረግነው ውይይት መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም ሙሉ በሙሉ የተቀበለ ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ እሁድ የካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም እንዲካሔድ የተወሰነው ሀገር ዓቀፍ እና ዓለም አቀፍ የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል” ሲል ሰልፉን የሰረዘበትን ምክንያት ሲኖዶሱ አመልክቷል።

“መንግሥት ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫው የሰጠውን ቀነ ገደብ ከግምት ውስጥ በማስገባትና ጥሪውን በመቀበል በየካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለአስቸኳይ ውይይት ዝግጁ መሆኑን በተመረጡ የሀገር ሽማግሌዎች አማካኝነት መልእክቱ ሲደርሰን ካለው ወቅታዊ የሰላም እና ጸጠጥታ ሁኔታ አንጻር ጥሪውን በመቀበላችን በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የተመራ ዐሥራ ሁለት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የኤፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት ሰፊ ውይይት ተካሂዷል” በለዋል።

በውይይቱም የተነሱት ነጥቦች በዋንኛነት ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ፤ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ሕግን መሠረት ባደረገ መልኩ ጠብቃ የምትሠራ እና ከዚህ ውጭ ምንም አይነት ድርድር የሌለው መሆኑን ገልጻለች፡፡ በዚህም መነሻ መንግሥት የቤተ ክርስቲያንን አቋም በመቀበል ወደፊትም የቤተ ክርስቲያንን አንድነት እና ሉዓላዊነትን በጠበቀ መንገድ እንደሚሠራ ማረጋገጫ እንድተሰጣቸውም በመግለጫቸው አስታውቀዋል። ውይይቱን ተከትሎ ሰላማዊ ሰልፉን ለመሰረዝ ስምምነት መደረሱን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

በሌላ ዜና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ጉዳይ የሚከታተለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች ምድብ ችሎት የዕግድ ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወሳል።

ፍርድ ቤቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የእግድ አቤቱታ መሠረት ቤተ ክርስቲያኗ አውግዛ በለየቻቸው ተጠሪዎች ላይ የእግድ ትእዛዝ መስጠቱን የቤተክርስቲያኗ መገናኛ ብዙሃን መዘገባቸው ይታወሳል።

Exit mobile version