ETHIO12.COM

ጦብያ “የችጋር ታሪኳን ገለበጠች” ሰሞኑን “ከዩክሬን ስንዴ ተላከ” ትንተና ይጠበቃል

ከሰሞኑ ዜጎችን ጭንቀት ላይ የጣለውና ከሁሉም አቅጣጫ በፖለቲካ ፍላጎትና በውጭ ሃይሎች ድጋፍ ተቀጣጥሎ የነበረው ዜና በሰላም ሲቋጭ ኢትዮጵያ ስንዴ ወደ ውጭ መላክ መጀመሯ ተሰምቷል። ዜናውን ተከትሎ ” ዩክሬን ስንዴ ላከች” የሚል ዜና እንደሚተበቅ የሴራውን አካሄድ የሚረዱ ጎን ለጎን ገልጸዋል።

በችጋር፣ በልመና፣ በጠኔና በረሃብ ስሟ ተደጋግሞ የሚጠራው ኢትዮጵያ ስንዴን እንዲ በአጭር ጊዜ አምርታ ወደ ውጭ ትልካለች የሚል ግምት ብዙም ስላልነበር፣ ስንዴ ኤክስፖርት እንደሚጀመር ቀን ተቆጥሮ ሲነገር ” ውሸታም፣ ህልመኛ” በሚል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሲዘለፉ እንደነበር ይታወሳል።

ዘለፋውም ሳያቋርጥ ” እርኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” በሚል መሪ ቃል ሲቀጥል፣ ጎን ለጎን ወረራ መቀልበሱና ስንዴ መዝራቱ፣ ትራክተር መግዛቱና ኮንባይነር ማስመጣቱ እንዳልቆመ በየጊዜው የሚወጡት ዜናዎች ሰሚ ባይኖራቸውም ይህንኑ የገልጹ ነበር።

በኢትዮጵያ ጥቂቶች በማህበራዊ ገጽና በዩቲዩብ ምክንያቱ ግራ በሚጋባ፣ ፍላጎቱ ከምን የመነቸ እንደሆነ መረዳት በማይቻልበት ደረጃ ከክፉ ዜና በስተቀር፣ ከመገዳደልና አስደንጋጭ መርዶ በስተቀር ጤናማ ዜና፣ ተስፋ የሚሰጥ መረጃ ማሰራጨት ባለመለመዱ የስንዴ ዜናም ልክ እንደሌሎቹ ታላላቅ ዜናዎች በሚገባቸው ደረጃ ሽፋን አላገኙም።

ሰሞኑንን በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል የተሰጠውን መግለጫ ተከትሎ “ከቅዱስ ሲኒዶስ ምን እንጠብቅ” ሲሉ 7 ሰአት ከአምስት ደቂቃ ያወሩ፣ በምስሉ የተጠቀሱት አይነት ሚዲያዎች ለሰኮንድ እንኳን ስንዴን ተንተርሰው አርሶ አደሩን ማበረታታት አለመቻላቸው አገራችን ምን አይነት ዜጎችን ስታፈራ እንደነበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ለነገሩን ውድቀት ማስረጃ እንደሆነ የገለጹ አሉ።

የስንዴ ተመረተ ዜና ገዢ፣ ጫኝ፣ ገንዘብ አስተላላፊና ውል ያለው መሆኑ እየታወቀ ” አናምንም” በሚል ለማጣጣል የሞከሩትን በግልብ የሚያቡትም ቢሆን ያለፈው የኩረጃ ትውልድ ውጤቶች መሆናቸው ግልጽ ነው። ጦቢያ የችጋር ታሪኳን ገልብጣ ስንዴ መላኳን የአፍሪካ አገራት አሞካሽተውና አድንቀው፣ ከአረንጓዴ አሻራ ጋር አያይዘው ሲዘግቡ፣ ለምን ሰላም ወረደ በሚል ” የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔና የመንግስት አዲስ ዘመቻ” በሚል አገሪቱን እረፍት የሚነሳ የ4 ሰአት ከ40 ደቂቃ ወሬ ሲረጩ አምሽተዋል።

ኢትዮጵያ በጀግኖች አርሶ አደረቿ ብርታት የችጋር ታሪኳን “ርሃብ ማለት ኢትዮጵያ ማለት ነው” በሚል በመዝገበ ቃላት የታተመውን ስሟን ዓለም እያየ ስትፍቅ ” ቀና ብለን እንድንሄድ ያደረከን ውዱ አርሷ አደር ” በማለት አድናቆት ስንደረድር በዋልን ነበር። አመራር የሰጡትን ትተን አርሶአ አደሩን ለድካሙ ካላመሰገን ለማን ነው ተቆርቋሪነታችን? “ትግል” የሚባለው ኪስ ማደለቢያ ዘፈን ሰማኒያ ከመቶ ለሚሆነው አርሶ አደር የስኬት ጅማሮ ቅድሚያ ካልሰጠ እነማንን ደጋፊ ሊያገኝስ አስቦ ይሆን? አዲስ አበባን ብቻ?

ፎቶ – ይህ ከችጋር ታሪካችን አንዱ ነው። በ1980 የሆነ።

አባይ ሲገደብና በዛ ሁሉ የባንዶች ሴራ ሙሌቱ በየደረጃው ሲከናወን በተመሳሳይ ” ሌቦች” እያልን ስናወግዝ፣ የአባይ መገደብ የገባቸው ” ኢትዮጵያ የኒኩሌር ባለቤት ሆነች” ነው ያሉት። በዚህ ላይ ስንዴ ሲጨመር ኢትዮጵያ ምን አይነት የፖለቲካ አቅምና ” የአልታዘዝም” ባይነትን እንደምትጎናጸፍ አሁንም የሚያውቁት በስንዴ እጃችንን የሚቆለምሙን ብቻ ናቸው።

አዲስ አበባ በሚስተናገደው የአፍሪካ አንድነት ደርጅት ስብሰባ ማግስት የስንዴ ኤክስፖርት ዜና የተበሰረው ዝም ብሎ ሳይሆን የአፍሪካ አገራት ከልመና እንዲወጡ አሳይቶ ለማነሳሳትና የፖለቲካውን ቸዋታ በግንባር ቀደምትነት ለመምራት እንደሆነ አሁንም ወዳጆቻችን እንጂ እኛ አይገባንም። አየር መንገድም የብሪክስ አገራትን የንግድ ግንኙነት ለማተናከር ከቻይና ጋር ህብረት አድርጎ ወደ ብራዚል የካርጎ በረራ የጀመረውም ዝም ብሎ አይደለም። ይህም የሚገባቸው አሁንም ወዳጆቻችንን ብቻ ነው።

ነገሩ ሁሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” የምናደርገውና ምን ለማድረግ እንዳሰብን የሚገባቸው ጠላቶቻችን ብቻ ናቸው” ሲሉ እንደገለጹት ነው። ለሁሉም ግን የችጋር ታሪክ ተወደደም ተጠላም ተገልብጧል። ዛሬ ከባሌ ነገ ከሁሉም የኢትዮጵያ አቅጣጫ ኢትዮጵያ ስንዴ ለዓለም ትሸጣለች። ይህ ዜና ካላሳበደን፣ ይህ ዜና ካላስፈነጠዘን ቆም ብለን ማሰብ አለብን። ከተቻለ መለቴ ነው። ሰባትና አራት ሰዓት እርግማን እየሰሙ መቆዘምም የባለቤቱ ምርጫ ነው። እኔ ግን “አለ ገና አለ ገና..” እላለሁ። የአፋሩ፣ የአማራው፣ የሶማሌው፣ የደቡቡ፣ የጋምቤላው …… የኢትዮጵያ

ነጻ ስተያየት ሳሙኤል ባይሰጠኝ – ሶደሬ

Exit mobile version