Site icon ETHIO12.COM

“አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ

በአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ላይ ለመታደም የመጣችው የኒጀር ዜግነት ያላት የፊልም ባለሙያዋ ራህማቶ ኪታ አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም በማድረግ አፍሪካዊያንም እንዲያውቁት ማድረግ ይገባል ብላለች።

ባለሙያዋ የፍራንኮ አፍሪካን ፊልም አዋርድን አሸንፋለች። በሥራዎቿ ዙሪያ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥታለች። የፊልም ጸሐፊ፣ ዳይሬክተር እና ፕሮዲውሰር ራህማቶ ኪታ አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እንዲኾን በአደባባይ ጥረት የጀመረችው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር በማነጋገር መኾኑን አብራርታለች።

በቅርቡም ይፋዊ ደብዳቤዋን ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት መሥጠቷን አብራርታለች። በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የታየላት  “የጋብቻ ቀለበቱ” የተሰኘው ፊልሟ በፊልሙ ዕይታ ማጠናቀቂያ ላይ የተሳታፊዎችን ስም እና ምስጋናዋን በምትገልጽበት ቦታ፤ ጽሑፉን በአማርኛ ቋንቋ በማስፈር ቋንቋውን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ጥረት አድርጋለች።

በዓለማችን በርካታ ቋንቋዎች ያሉ ቢኾንም የራሳቸው የፊደል ገበታ ከታደሉ ጥቂት ቋንቋዎች መካከል አንዱ የኾነው አማርኛ ቋንቋ፤ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ መኾን ይገባዋል፤ ይህንን ማድረግ ስንችል የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን አማርኛ ቋንቋ የአፍሪካውያንም ሐብት መኾን ይችላል ስትል ራህማቶ ኪታ አብራርታለች።

የአማርኛ ቋንቋ 7ተኛ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እስኪኾን ጥረቴን አላቋርጥም ብላለች።

አማርኛ ከምሥራቅ አፍሪካ ውጭ በእስራኤል፣ በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች እና በደቡብ አፍሪካ በብዙዎች ዘንድ የሚነገር ውብ ቋንቋ ስለመኾኑ አብራርታለች። (አሚኮ)

አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ

የኢትዮጵያን ፊደል አማርኛ ቋንቋን የአፍሪካ ኅብረትና የአፍሪካ አሃጉር ፊደል ይደረግ ዘመቻ መጀመሪያ በግሪጎሪያን 1989, በየሐረርወርቅ (የኢትዮጵያ ወርቅ) ጋሻው መስራችነት ተጀመረ። ይህንን ትልቅ ዓላማዋን በጽናት ይዛ ግቧን ለመምታት እነሆ በይፋ በ1990 (ግጎ) ለአፍሪካ መሪዎች በነብስ ወከፍ በማስተዋወቅ ብሎም ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት አሁን የአፍሪካ ኅብረት ጭምር ካስተዋወቀችበት ጊዜ ጀምሮ አንድቀን ሳታቋርጥ ቀጥላበት እነሆ በጉዳዩ ጸንታ እስከዛሬ በመታገል ላይ ትገኛለች።

ከተነሳችበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ እንቅፋቶች በትሕነግ መሪ በመለስ ዜናዊና በግብረ አበሮቹ ጅምሯን ለማኮላሸት የተፈጸሙ ችግሮች ቢያጋጥሟትም፣ እነሆ እስከዛሬ ድረስ ወደኋላ ሳትል ሌሎች አፍሪካውያንን ጭምር በማስተባበር እየታገለች ትገኛለች። ለዚህም አንዱ ይሄ የስም ፊርማ ዘመቻን ጀምራ ለዚህ ዓላማ ይጠቅማሉ ብላ በራስዋ ምርጫና በጎ ፍቃድ በኮሚቲ ውስጥ ያካተቻቸው ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎችን ያካተተው ዓለም አቀፍ ዘመቻ በChange.org ላይ ያቀረበችው ይገኝበታል።”

መለስ ዜናዊ ስልጣን ሲቆጣጠር አማርኛ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ የአፍሪካ አንድነት ቋንቋ መሆን አይገባውም ትግሪኛ ካልሆነ ብሎ በአፍሪካን ኅብረት (AU) ላይ ጫና እስኪሞት ድረስ ፈጠረ። ከዛም እነ ስዩም መስፈን፡ ስበሃት ነጋ ከነግብረእበሮቻቸው ቀጠሉበት።”   

አሁን አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት የስራ ቋንቋ እንዲሆን እንተባበር ፊርማችሁን አስቀምጡ። ለሌሎችም ሊንኩን (https://chng.it/WzMPT7RNvW) በማካፈል አሳስቡ።

ከአክብሮት ጋር አመሰግናለሁ እግዜር ይስጥልኝ።

የሐረርወርቅ (የኢትዮጵያ ወርቅ) ጋሻው ።

https://chng.it/WzMPT7RNvW

We, the Pan Africanist activists, diaspora and Africans located in the homeland are asking to register Amharic አማርኛ, the official language of Ethiopia, among the official languages of the African Union. In order to continue to foster unity of our nations, we need representation of the African people within this union. We acknowledge that the all-encompassing statement “and any other African language,” follows the AU’s statement of its primary 5 languages, but that is not enough. The history of imperialism in Africa has often swept over our languages and strong heritage. If we do not give value to our native tongues, who will? As such, we call for the AU to take a stand to acknowledge and lift up the people it serves by giving honor and significance to the native tongues of the land. We Africans don’t need Latin to write our languages.

We call for አማርኛ – Amharic to be added as soon as possible because the Ethiopian nation has been a symbol of freedom for the African people on the Continent and diaspora since the reign of Emperor Minilik II and Emperor Haile Selassie I. Ethiopic-Amharic, is the national and official language of Ethiopian Government, public schools and the majority of the Ethiopian people. It is the written language among Ethiopian’s 200 languages and 82 ethnic groups (115,629,543 people) that is read, written and spoken. In addition, it is electronically written and accessible due to the Ethiopic (Ethiopian) software, just as the other alphabets currently being utilized by the AU.

This campaign was first started by Yeharerwerk Gashaw, in 1989, Dallas, Texas. And brought to the attention of the AU, starting during time the union was still called the Organization of African Unity (OAU). The proposal was presented along with the “War Against Drugs In Africa” And “Abolish Separatists In Africa “, by Yeharerwerk Gashaw, the First Ethiopian International Model, Cover Girl and Actress, Human Rights, Pan Africanist, Political Activist, at the AU’S Headquarter on August 30, 1990. in Addis Abeba, Ethiopia at an official meeting with the then Secretary General of the OAU, Dr. Salim Ahmed Salim, and in the presence of the Ethiopian and OAU Press (article by Ethiopian Herald attached below). It has been a long time coming, and it is the time for change to occur. https://chng.it/WzMPT7RNvW

ለአማርኛ ቋንቋ ተቆርቋሪዋ ኒዤሪያዊት የፊልም ባለሞያ

ፊልሟ ውስጥ አማርኛ ጽሑፍ በማስገባት ለአማርኛ ቋንቋ መቆርቋሯን አሳይታለች ኒዤሪያዊቷ የፊልም ባለሞያ ራማቱ ኪየታ፤ አማርኛ የአፍሪቃ ኅብረት ይፋዊ ቋንቋ እስኪሆን ጥረቴን አላቋርጥም ትላለች። ኒዤሪያዊቷ የፊልም ዳይሬክተር በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ በመሳተፍ ለአማርኛ ቋንቋ መሟገቷን ቀጥላለች። 

ቀሪው ጽሑፍ እዚህ ላይ ይገኛል

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Exit mobile version