Site icon ETHIO12.COM

ወደ መቀሌና ሽሬ በሚደረጉ በረራዎች ከታሪፍ በላይ በማስከፈል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ተጠያቂ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ እና ሽሬ በሚያደርጋቸው በረራዎች በአዲስ አበባ እና በመቀሌ ተመድበው የሚሠሩ አንዳንድ ባለሙያዎችና ከአየር መንገዱ ጋር የሚሠሩ ኤጀንቶች  ጉዳይ እናስፈጽማለን ከሚሉ ግለሰቦች ጋር ተመሳጥረው ከተቀመጠው የክፍያ ታሪፍ በላይ ሲያስከፍሉ ስለተደረሰባቸው ተጠያቂ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ እንዳመለከተው÷ ከታሪፍ በላይ ሲያስከፍሉና ኅብረተሰቡን ለእንግልት ሲዳርጉ የተደረሰባቸው በሙሉ  ጉዳያቸው ተጣርቶ ተጠያቂ የማድረግ ሥራ በጋራ እየተሠራ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ወቅት በቀን ወደ መቀሌ የሚደረገው የበረራ ቁጥር  ወደ አምስት ማደጉን እንዲሁም ወደ ሽሬ የሚደረገው በረራም በሳምንት ወደ  ዘጠኝ  ከፍ ማለቱን መግለጫው ጠቁሟል፡፡አስፈላጊው የሰው ኃይል በየበረራ መዳረሻው ተመድቦ ደኅንነቱ በተረጋገጠ ሁኔታ ተጓዦች በቂ አገልግሎት እንዲያገኙ በቁርጠኝነት እየተሠራ መሆኑም ተመላክቷል፡፡[FBC]

Exit mobile version