ETHIO12.COM

የሰዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ አፅም በስደት ካረፈበት ሐገር ወደ ሚያፈቅራት ሐገሩ ሊመጣ ነው!!

(ይትባረክ ዋለልኝ)
የካቲት ወርን የሰዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ የመታሰቢያ ወር በማለት ላለፉት ሶስት ሳምንት ሲካሄር ቆይቶ ነበር::የዚህ የመታሰቢያ ወር የማጠቃለያ ፕሮግራም ትላንት ቅዳሜ የካቲት 25 2015 ዓ/ም ከ8:30 ሰዓት ጀምሮ በደመቀ ስነስርዓት ተጠናቋል::
በዚህ የማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ ይህንን ታላቅ የጥበብ ባለሙያን የሚዘክሩ በርካታ ዝግጅቶች ቀርበዋል:: ከእነዚሁ ዝግጅቶች መካከል ዋናው የነበረው በጎ ፈቃደኛ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን ያካተተ ታስክ ፎርስ ማቋቋም ነበር::

ይህ ታስክ ፎርስም:-
የሰዓሊ ገብረክርስቶስን አፅም በስደት ካረፈበት አሜሪካን ሐገርወደሚያፈቅራት ሐገሩ የሚያስመልስ ;የግጥም ስራዎቹና የየካቲት መታሰቢያው አከባበርን አሳትሞ ለህዝብ የሚያደርስ; በተለይ በመንግስትና በግለሰብ እጅ የሚገኙትን የስዕል ስራዎቹ የሚያሰባስብ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ስድስት ኪሎ ቢዝነስ ፋካልቲ በሚገኘው የገብረክርስቶስ ሙዚየም ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ሙዚየም የሚያደርግ በሐገር ውስጥና በውጭ ሐገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተሰባሰቡበት በጎ ፈቃደኞች ሆነው የሚሰሩ ታስክ ፎርስ ተቋቁሟል::ይህ ታስክ ፎርስ የገብረክርስቶስ ደስታ ቤተሰብን ጨምሮ በሐገር ውስጥና በውጭ ሐገር የሚኖሩ ምሁራንንና የህግ ባለሙያዎችን ያካተተ ነው::
⁃ ፕሮፌሰር አቻሜለህ ደበላ
⁃ ዶ/ር አስፋወሰን አስራተ ካሳ
⁃ ዶ/ር ሄራን ሰረቀ ብርሃን
⁃ ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ
⁃ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ
⁃ አቶ ብርሐነመስቀል ደጀኔ
⁃ አቶ አበበ ባልቻ
⁃ አቶ አገኝሁ አዳነ
⁃ ወ/ሮ አልታየወርቅ ተድላ
⁃ ወ/ሮ አልማዝ ወንድሙ
⁃ አቶ አንተነህ ክፍሌ ደስታ ናቸው::

Exit mobile version