Site icon ETHIO12.COM

ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ እና ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ ተፈቱ

በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እና በሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ መዝገብ ተከስሰው በእስር ላይ የነበሩ የህወሓት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 21፤ 2015 አመሻሽ ላይ ከእስር መፈታታቸውን የተከሳሾቹ ጠበቆች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሃፍቶም ከሰተ ገልጸዋል ።

በዛሬው ዕለት ከእስር ተለቅቀው ወደ ቤታቸው መግባታቸው ከተረጋገጡ ተከሳሾች ውስጥ፤ የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ እና ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ እንደሚገኙበት ጠበቃው አስታውቀዋል።

ተከሳሾቹ ዛሬ አመሻሽ ላይ በእስር ላይ ከቆዩበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ወደ ሲ.ኤም.ሲ የመኖሪያ ግቢ፣ ፒያሳ እና ሳሪስ አካባቢዎች በማረሚያ ቤቱ አውቶብስ ከተወሰዱ በኋላ መፈታታቸውን ጠበቃው አስረድተዋል።

እስረኞቹ ወደ እነዚህ ቦታዎች እንደተወሰዱ አስቀድሞ የተነገራቸው ቤተሰቦች፤ በስፍራው ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል ተብሏል።

ዛሬ ከእስር የተፈቱት በዶ/ር ደብረጽዮን መዝገብ የተካተቱ 16 ተከሳሾች እና በሌተናል ጄነራል ታደሰ መዝገብ ስር ክስ ቀርቦባቸው የነበሩ 20 ወታደራዊ መኮንኖች መሆናቸውን ጠበቃ ሃፍቶም ገልጸዋል።

ኤፍ ኤም 107.8

Exit mobile version