Site icon ETHIO12.COM

በህገወጥ መንገድ ልዩ ልዩ መድሃኒቶችን ሲያዘዋውሩ የተገኙ በቁጥጥር ስር ዋሉ

መድሃኒት የመሸጥ ሆነ የማከፋፈል ፍቃድ ሳይኖራቸው በህገወጥ መንገድ ልዩ ልዩ መድሃኒቶችን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ሁለት ግለሰቦች በህብረተሰቡ ጥቆማ እና ተሳትፎ እጅ ከፍንጅ ተይዘው ምርመራው መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ህገወጥ ንግድ በማህበረሰቡ ላይ የሚያደርሰውን ጫኛ ለመከላከል አዲስ አበባ ፖሊስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

ፖሊስ ከህብረተሰቡ የደረሰውን ጥቆማ መነሻ አድርጎ ባደረገው ክትትል ሁለቱ ግለሰቦች ምንም አይነት ፈቃድ ሳይኖራቸው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አ/አ B 37519 ዳማስ በሆነ መኪና ልዩ ልዩ መድሃኒቶችን ጭነው ሲንቀሳቀሱ መጋቢት 25 ቀን 2015 ዓ/ም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው እፎይታ የገበያ ማዕከል አካባቢ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የእፎይታ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።

ግለሰቦቹ ልዩ ልዩ መድሃኒቶች ከድሬዳዋ ከተማ በህገወጥ መንግድ ማምጣጣቸውን እና መድሃኒት የመሸጥም ሆነ የማዘዋወር ፍቃድ የሌላቸው መሆኑን ተረጋግጧል፡፡

ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ሆነ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገው እንቅስቃሴ በፀጥታ ስራ ላይ የተሰማሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ሚና የጎላ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋ የህብረተሰቡ ትብብር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

ህገወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ህግን ተከትለው ቢመሰሩ የንግዱ ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ጫንን የሚያስከትል ሲሆን በተለይ ደግሞ ከመድሃኒት ጋር ተያይዞ የሚፈፀም ህገወጥ ድርጊት በሰዎች ጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት በእጅጉ የከፋ ስለሆነ መሰል ህገወጥ ድርጊቶች የማጋለጥ ተግባራት ሊጠናከር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

Exit mobile version