ትግራይ በራች! ደግ ዜና እየተሰማ ነው

ከትግራይ የሚሰማው ዜና ተስፋን የሚያለመልም እየሆነ ነው። ትግራይ አብዛኛው ክፍሏ ጨላምን ተገፎለታል። እርዳታ በአራቱም አቅጣጫ ያለገደብ እየፈሰሰላት ነው። ከኤለኤትሪክ መመለስ ጋር ተያይዞ ወፎጮ ቤቶች ስራ ጀምረዋል። ቀለብ ብቻ ሳይሆን ምንም ትርጉም በሌለው የፖለቲከኞቿ ውስልትና ሳቦቢያ ከትምህርት ተገለው የነበሩ ህጻናት ወደ ትምህርት አውዳቸው ሊመለሱ ተቃርበዋል።

ባለፉት ሁለት ወራት ትግራይ አርፋለች። ልጆቿም ማሰቢያ ጊዜ አግኝተዋል። ፖለቲከኞቿም የተሞረዱ ይመስላሉ። ደቃ የነበረችው ትግራይ ዳግም ታንሰራራ ዘንድ አንድ ሆኖ ከመስራት ይልቅ ጦርነትን የሚጠምቁላትም ወደ ተስፋ መቁረጡ ያቀኑ ይመስላል። ከትግራይ የምሰማው ዜና ህዝብ ” በቃን” ማለቱን ነው። ቀን ይፋ የሚያደርገው የትግራይ እናቶችና ወላጆች ኪሳራ እንዳለ ሆኖ ዛሬ ላይ የትግራይ ሰላም መሆን የመሃል አገሩንም ፋታ ሰጥቶታል። በትህነግ የሚደገፉ በአብዛኛው ጠብ መንጃ እየሰቀሉ ነው። ኦነግ ሸኔ አማራና ኦሮሞ እንዲባላ ንጽሃን ላይ በትሩን እያደባ ማንሳቱ ያልተቀረፈ መከራ ቢሆንም፣ ትህነግ በቀጣይ እነሱን መርዳት የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱ ስጋቱን ከተራ መፍጨርጨር እንደማያዘልለው ለጉዳይ ቅርብ የሆኑ እየገለጹ ነው።

በይፋ ከሸኔ ኦነግ ጋር ግንባር የፈጠረው ትህነግ በይፋ ውሉን ማፍረሱን መግለጽ እንዳለበት እየተጠየቀ ነው። አንዱ የፕሮቴሪያው ስምምነት ይህ በመሆኑ ትህነግ በይፋ ሸኔን ካላወገዘ ሽግር እንደሚኖር የሚገልጹ ” የተግራይ ህዝብ ይህን ሊገፋና ሊያስፈጽም ይገባል” ሲሉ ሰላሙ ይበልጥ የሚጠናበትን አግባብ አመላክተዋል። የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ላይ አተንክሮ ለመስራት እንዲህ ያሉ መተማመንን የሚነሱ ጉዳዮች ላይ እርምት እንዲደረግ ማሳሰብና መግፋት የሁሉም ግዴታ መሆኑንም አክለው የሚገልጹ፣ ለጥያቄያቸው ምላሽ ይፈልጋሉ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ባለስልጣን እንዳለው መቀለን ጨምሮ በርካታ ከተሞች በፖለቲከኞቿ ጥጋብ ከገቡበት ጨለማ ተላቀዋል። ወፍጮ ተንቀሳቅሷል። እህል፣ ነዳጅ፣ መድሃኒት፣ ገንዘብ፣ የባንክ አገልግሎት፣ ስልክ … በየፈርጁ የትግራይን ልብ መልሰው እያደሱ ነው። ስምምነቱም በወጉ እየሄደ መሆኑ እየተሰማ ነው።

ዛሬ የመንግስት ሚዲያ አሃዝ ጠቅሶ እንዳለው ታህሳስ 7/2015 የሠላም ሥምምነቱን ተከትሎ ወደ ትግራይ ክልል ግምታቸው 229 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የህክምና ቁሳቁስ መሰራጨቱን የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ገለጸ።

See also  መከላከያ ሠራዊት በጥፋት ሃይሎች ታግቶ የቆየ 7250 ኩንታል እህል አሥለቀቀ

አገልግሎቱ በመቀሌና በሽሬ የሚገኙ ቅርንጫፍ ቢሮዎቹ በከፊል ሥራ መጀመራቸውንም አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅርቦት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ ለኢዜአ እንዳሉት የሰላም ሥምምነቱን ተከትሎ በሦስት አቅጣጫዎች መድሃኒቶችን ወደ ትግራይ እየተሰራጩ መሆኑን ገልጸዋል።

በመጀመሪያው ዙር 229 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የህክምና ግብዓቶች ወደ ትግራይ ክልል መላካቸውን ጠቁመዋል።

በመቀሌ እንዲሁም በሽሬ የሚገኙ የአገልግሎቱ ቅርንጫፍ ቢሮዎች በከፊል ሥራ መጀመራቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

የመድሃኒቶቹ ዓይነትም የጤና ፕሮግራም መድሃኒቶች (የኤች አይ ቪ/ኤድስ፣ የወባ እንዲሁም የእናቶችና ህጻናት መድሃኒቶች) መሆናቸውን ጨምረው ገልጸዋል።

ለመደበኛ፣ ለሕይወት አድን የሚውሉ መሰረታዊ መድሃኒቶችና ለህክምና አገልግሎትና ለላቦራቶሪ ግብዓት የሚውሉ ኬሚካሎች መሰራጨታቸውን ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።

እንደ ስኳርና ደም ግፊት የመሳሰሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለማከም የሚያገለግሉ መድሃኒቶች መካተታቸውንም እንዲሁ።

የሁለተኛ ዙር የመድሃኒት ሥርጭት በቀጣዮቹ ቀናት እንደሚጀመር በማከለ።

እንዲሁም የመቀሌና የሽሬ ቅርንጫፎች ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ እንዲገቡ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

መድሃኒቶቹን ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲጓጓዙ መደረጉን ጠቁመዋል።

Leave a Reply