Site icon ETHIO12.COM

እንዲገለጥልን የልዩ ሃሎችን መሟሟት ከአገራዊ ምክክር ኮሚሽን አካሄድ ጋር እንሳፋው!

በኢትዮጵያ “አንድ” ብሎ አገር፣ የጸጥታ መዋቅር፣ መንግስት፣ ህገመንግስት፣ ሕዝብ፣ ዜግነት እንጂ “አንድ” ብሎ እምነት፣ ቤተርስቲያን፣ ብሄር፣ ልዩ ማንነት፣ መዝሙር አይሰራም። ዜጎች የግል እምነት፣ የተፈጠሩበት ከባቢ፣ ስለ ልቦናና ባህል አላቸው። ይህ ልዩነታቸው ተጋምዶ በትልቋ ባህር ኢትዮጵያ ውስጥ ሲካተት አንድ አገር፣ አንድ ህዝብ፣ እኩል ባለቤትነት፣ እኩል ባለ ጌጥ ያድርገናል። ዘውጌነት የዚህን አንድነት የሚበላና ጡንቻውን አሰባስቦና አደርጅቶ ራሱን በሌሎች ላይ የሚጭን የተራ ስግብግብነት መለያ ነው። ትህነግ ምስክር ነው። ይህ አውዳሚ ዕቅድ ኢትዮጵያ ላይ ከተደፋ ጀምሮ ያተረፍነው በሽታና መከራ እንጂ ሌላ አይደለም። ስለዚህ ካለፈው ተምሮ፣ ማሻሻያ በማድረግ አንዱ ሌላውን አክብሮ ለመቀጠል ተባብሮ መስራት ለልጆቻችን ታሪካና መካም ነገርን ማስቀመጥ ነው።

ወደድንም ጠላንም አሁን ያለው የጎሳ ፖለቲካ አያዋጣም። ከገፋንበትና ዘውጌነቱ ላይ እንቸከል ካልን መጥፊያችንን ከማፍጠን ውጭ ሌላ ምንም አናተርፍም። ስለዚህ የጎሳ ፖለቲካ ከኢትዮጵያ መነቀል አለበት። የዛኔ ይህንኑ ጎሳ እየተከተለ የሚነሳው ጥያቄና የውዥንብር ጎርፍ ይቆማል። ስለዚህ የመጀመሪያው እርምጃ የጎሳ ፖለቲካ ማስፈጸሚያ የሆነው የክልሎች ልዩ ሃይል መሟሟት ነው። ይህ እርምጃ ህገ መንግስቱን እስከመቀየር ስልጣን ከተሰጠው አገራዊ የምክክር ኮሚሽን አረማመድ ጋር በጥምረት ሲታይ የሚያስፈነጥዝ እንጂ የሚያነታርክ ባልሆነ ነበር። ስለዚህ ሁለቱን አብሮ መመለከቱና መረዳቱ ግድ ነው። የህዝብ ጥያቄና ጩኸት ምላሽ ማግነት ሲጀመር መጮህ ለያዡም ለገናዡም አይነት ነውና።

ሰሞኑንን አየሩን የያዘው የክልል ልዩ ሃይሎች ወደ ፌደራል የጸጥታ መዋቅር እንዲካተቱ በፓርቲ ደረጃ ስምምነት የተደረሰበት ጉዳይ ነው። በፓርቲ ደረጃ መግባባት ከመደረሱ በፊት ከህግና ሕገመንግስት አግባብ ውጪ የክልል አስተዳደሮች ከፍተኛ ሃይል ሲገነቡ፣ በፉክክር መልክ በጀታቸውን ለሰራዊት ግንባታ ሲያፈሱ፣ ህዝብ፣ የወደፊቱ ስጋት የገባቸው፣ መከራ የተቀበሉ ሲቃወሙ ነበር። መፍረስ አለባቸው በሚል በግልጽ ቋንቋ ድምጽ የማ ነበር። ይህን የሚክድ ሃይል የለም።

ይህ ውሳኔ ሲሰማ ራሱን ከነጻ አውጪ ስም ጋር ሰፍቶ እድሜውን የበላው ትህነግ በገፍ ያሰለጠነውና ከፌደራል ጓዳ ዘርፎ ያስታጠቀው ልዩ ሃይሉ ስሙን ቀይሮ “የትግራይ መከላለያ ሃይል” በሚል ተገዳዳሪ ስያሜ ተበጅቶለት እንዴት አገር፣ የሰው ህይወትና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል እንደፈጠረ ያየነው የቅርብ ወራቶች ትዝታ ነው። የትህነግ እብጠት ያስከተለው አገራዊ ቀውስ ወላፈኑ እንዲሁ በቀላሉ የሚቀየርም አይሆንም። ከዚህ አንጻር “እንዴት ነው አፈጻጸሙ?” የሚል ጥያቄ ካልተነሳ በስተቀር የክልል ጡንቻ እንዲሟሟ መወሰኑ ለክርክር አይቀርብም። ህገ መንግስታዊም ነው። ከዛም በላይ የህልውናችን ቁልፍ ማስቀጠያ ውሳኔ ነው።

ይህን ውሳኔ ቀድሞውኑ “ልክ እንደ ትግራይ መከላከያ ሃይል፣ የአማራ መከላከያ ሃይል መቋቋም አለበት” ሲሉ የነበሩ ወገኖች “ኦሮሞ ሊስለቅጥህ ነው” በሚል ህዝብ ግንዛቤው እንዲንሻፈፍ፣ ብለው ብለው ያቃታቸው የትህነግ ካድሬዎች ደግሞ የድርጅታቸው ትዕቢትና አጉል ጉራ ሲነትብ ውጭ ሆነው የትግራይን ወጣት ባስጨረሱበት ምላሳቸው ” ወልቃይትን ልናስመልስ ነው” በሚል ሲጋቱ ያደጉትን ሴራ እየተፉ አካሄዱን ሊያስተጓጉሉ እየሰሩ ነው።

“ኢትዮጵያ ስትፈርስ ከማየት በላይ የሚያስደስተኝ ነገር የለም” ሲሉ የነበሩ የሴራ አንቃራሪዎችን ወሬ በመስማት፣ በሳቢና ገፊ ፖለቲካ ተናበው የሚሰሩትን የኢትዮጵያ መርገምቶች በመከተል የሚሰራጨው ዜና ልዩ ሃይል የሚሟማው በአማራ ክልል ብቻ እንደሆነ አድርገው እያራገቡ ነው። እዚህ ላይ ወራጅ አለ ለማለት እንወዳለን።

ዝርዝር ውስጥ መግባት ባያስፈልግም ትህነግ የሚታመን ስንጣሪ ስብዕና የሌለው ድርጅት ነው። ትህነግ አልሳካ ብሎት እንጂ በታኝ፣ አፍራሽ፣ የክፋት ሁሉ ቁንጮ የሆነና መላ ገላው በደም የተነከረ ቡድን ስብስብ ነው። ይህ ስብስብ የትግራይን ህዝብ ድፍን አገር፣ በተለይም አማራ ጠላቱ እንደሆነ ለዓመታት ሰብኮ ህዝቡ መሄጃ የሌለው እስኪመስለው ድረስ አማራን ጠላቱ አድርጎ ሲበርግግ እንዲኖር ሆኗል። ይህን አስተምህሮ በወራራው ወቅት የተያዙ መስክረዋል። በድርጅቱም ማኒፌስቶ ሰፍሯል።

ከዚህ አንጻር፣ በወልቃይት ህዝብ ላይ ላለፉት 27 ዓመታት የተፈጸመውን አጅግ አስነዋሪ ተግባር ስንመረምር ይህ ህዝብ ቢሰጋ አይፈርድበትም። ሴረኞቹና በተራ የአማራ ተቆርቋሪነት ስም እንደሚጮሁት ሳይሆን የወደፊቱን ባገናዘበ፣ የአካባቢው ህዝብም ከቆቅ ኑሮ ተላቆ ሙሉ አቅሙን ኑሮው ላይ እንዲያደርግ፣ ከጎረቤቶቹ ጋር ሁሉ በቀናነትና እንደ ድሮው በወዳጅነት እንዲኖር አንድ ሰላማዊ መላ ሊፈጠር ይገባል። ምሁራን ነገር ከማጦዝና በተራ የዘውግ እሳቤ በየሚዲያው ረብ የለሽ ወሬ ከሚረጩ እዚህ ላይ ቁጭ ብለው አሳብ በማሰባሰባና በማጥናት መንግስትን ሊመክሩ ይገባል። የአማራና የትግሬ ምስኪን ህዝብ በጠላትነት ተፈላልጎ አያውቅም፣ ቢያደርጉትም ማብቂያ የሌለው ችግር ውስጥ ከመኖር የዘለለ ዋጋ አያገኙበትም።

ወደ ጡንቻው ጉዳይ ስንመለስ አስተዋዮች እንደሚሉት ከፍተኛ የቀውስና የችግር ምንጭ የሆኑትን አካባቢዎች በመለየት፣ በሰከነና ህዝብን በማወያየት፣ የልዩ ሃይሉን ፖለቲካዊ መዋቅር በማሳመንና የልዩ ሃይሉ በተቀመጠለት ሶስት አምራጭ መሰረት እንዲስተናገድ ማድረግ ያስፈልጋል። ከእነዚህ ከሚታወቁ አካባቢዎች በዘለለ አማራ ክልልም ሆነ ኦሮሚያ ልክ እንደ አፋር፣ ሶማሌ፣ ደቡብ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል… እኩል ክልል ናቸውና ውሳኔውን ማክበር ግዴታቸው ነው። ሁሉም ዝም ብለው ወደ ተግባር ሲገቡ አማራ ክልል ላይ ብቻ በደፈናው ተግባራዊ እንደማይሆን ማሰብና መንቀሳቀስ ልክ አይሆንም። ከሌሎች ክልሎችም ጋር አያስማም። የትህነግን ጥፋት መድገምም ይሆናል።

ኮሽ ባለ ቁጥር መሳሪያ እየመዘዙ የሚናረቱ ሃይሎች ህዝብን አማረዋል። አፋር፣ ሶማሌ፣ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል … በተደጋጋሚ “ገላመጥከኝ፣ አንድ ክንድ መሬት ዘልቀህ ገባህ” በሚል ሲዋጉና ህዝብ ሲፈናቀል መኖር የለበትም ከተባለ ውሳኔውን መደገፍ እንጂ፣ የውሳኔውን አውድ ወደ ግል የፖለቲካ አጀንዳ በመቀየር ማራገብ ለማንም በጎ ውጤት አይስገኝም። የትህነግ የዛሬ ቁመናና የትግራይ መጨረሻ ጥሩ ምሳሌ ነው። ሲንጋፖር እንደሚሆን ሲነግረን የነበረው ትህነግ ጨለማ ውጦት፣ ድርቅ መቶት፣ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው፣ መንገዶች ፈርሰው፣ መስረተ ለማቶች ወድመው፣ ሆስፒታልና የጤና ተቋማት ባዶ ሆነው፣ በፖለቲካ በሽቅጦ፣ በቁመናው ከስሮ፣ በለቅሶ “አትርፉኝ” ካለ በሁዋላ እነሆ ዛሬ በዳዴ ለዳግም “ጥሩ ክልልነት” እየተውተረተረ ነው።

ይህ የትህነግ የትዕቢትና የደረሰበት ውጤት በተመሳሳይ እብሪተኛነት ለመጓዝ ለሚከጅሉ ማናቸውም ክልሎች የመጨረሻ አክሊላቸው እንደሚሆን ታሪክም፣ ጊዜም አሳይተውናልና እንጠንቀቅ።

ስለ አማራና ኦሮሚያ ብቻ እናወራለን እንጂ ድምሳቸውን አጥፍተው ከፍተኛ ሃይል የገነቡ አሉ። ብዙ ዝርዝር ውስጥ መግባት ባያስፈልግም በየቦታው የተደራጀው ሃይል ባስቸኳይ ወደ ፌደራል የጸጥታ መዋቅር መገባታቸው የህልው ጉዳይ ሆኗል። እላፊ የሄዱ አሉና የአገራችንን አንድነት ለማስጠበቅ አንድ የጸጥታ መዋቅር እንዳይኖር የሚመኙና የሚቀሰቅሱ ዓላማቸውን መመርመር ግድ ነው።

ከላይ እንዳልነው ልዩ ትኩርት ከሚያሻቸው አካባቢዎች ውጭ በሁሉም ክልሎች የፌደራል ሃይል የሚባል መዋቅር ባስቸኳይ እንዲሟሟ ኢትዮጵያን የሚወድ ሁሉ ሊደግፈው የሚገባ ጉዳይ ነው። ክልሎች የሚያዙት ከተራ ፖሊስ የዘለለ ሃይል በኢትዮጵያ ምድር ሲከስም ኢትዮጵያ ትጸናለች። ትህነግ ላይ እየታየ ያለ መጠነኛ መለሳለስ ከድርጅቱ ባህሪና ተፈጥሮ አንጻር ስለማያዋጣ ወደ ጥብቅ አቋም ተቀይሮ ሊተገበር ይገባል። ህዝብም እየተፈጸመ ያለውን እንዲያይ ማድረግ አስፈላጊ ነው።

መንግስትን ጨምሮ ከተለያዩ ወገኖች እንደሚሰማው፣ ዛሬ የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሃይል ግዙፍ ሃይልና አቅም ገንብተዋል። “እናት አገሬን” ያሉ ልጆቿ የተደረገላቸውን ጥሪ ተቀብለው ኢትዮጵያ ኦና ተደርጎባት የነበረው የመከላከያ ሃይሏ አስተማማኝ እንደሆነ ምስክሮቹ ብዙ ናቸው። መከላከያን ወይም ፌደራል ፖሊስን እንዲቀላቀሉ ጥሪ የቀረበላቸው የክልል ልዩ ሃይል አባላትና አመራሮች “የክልል” ከመባል በላይ ” የኢትዮጵያ” መባሉ ክብርና ኩራት እንደሚሆንላቸው ማስተማር ሲገባ ሚናቸው ግልጽ ያልሆነ ሚዲያዎች እዛው የዘውጌ ኩሬ ውስጥ ተቀርቅረው እንዲቀሩ እየጮሁ ነው። ለምን?

በጥንቃቄ ከማድርግ ውጭ ልዩ ሃይል የሚባለውን የዘውጌዎች ሃይል ማፍረስና ወደ ፌደራል የጸጥታ መዋቅር መመለስ በምድራዊ መመዘኛዎች ሁሉ ትክክል እንደሆነ እናምናለን። በተደጋጋሚ ጽፈናል። በህልውናው ዘመቻ ሁሉም ወገን የተዋደቀው ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፣ ወይም ለብልጽግና ወይም ለተወሰነ ሃይል ሳይሆን ለአገር ነው። ሁሉም ውለታቸው በትውልድ ይታወሳል። ባንዳዎች በንድነት እንደሚታወሱ ሁሉ ከመከላከያ ጋር ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው አገር ያጸኑ ታሪካቸው በወርቅ ይጻፋል።

ዛሬ በባዕዳን አገር በተቋቋሙ ሚዲያዎች ውስጥ ሆነው የቀጠሯቸውን አገራት ዓላማ በገዛ አገራቸው ላይ ሲረጩ የነበሩ፣ አሁንም እየረጩ ያሉ፣ በተለይም በህልውና ዘመቻው ወቅት አለቆቻቸው በሚያዟቸው መሰረት ኢትዮጵያ እንድተተራመስ ሲሰሩ የነበሩ ባንዳ የሚዲያ ባለሙያዎች በባንዳነት ታሪክ እንደተመዘገቡ ሁሉ ይህ ኢትዮጵያን የማጽናት ልዩ አጀንዳ፣ ቀጣዩ እርምጃ ምን ሊሆን እንደሚችል አመላካች መሆኑን በመረዳት እናንተ ያልተገዛችሁ የኢትዮጵያ የሚዲያ ሰዎች አግዙ። ታሪክ እናንተንም በአንድ ወቅት በባንዳዎች አናት ላይ አስቀምጦ የነሳችኋል። የባንዳዎቹ ልጆች ሲያፍሩ የናንተ ቀና ብለው በኩራት ይሄዳሉ። የባንዳ ልጅ፣ የጀግና ልጅ ይሉሃል ይህ ነው። እናም ህገመንግስቱን እስከ መቀየር ስልጣን የተሰጠው የሽግግር እርቅ ኮሚሽንን እርምጃ ለሚያጤኑ፣ የጎሳ ፖለቲካ ለስለቻቸው፣ የክልል የዘውጌ ሃይሎች መዋቅር መሟሟት ወዴት እንደሚወስደን ካልገባን ችግር ነው። ሰውየው ” የናደርገውን የሚያውቁት ጠላቶቻችን ናቸው” እንዳሉት።

Exit mobile version