Site icon ETHIO12.COM

በጎንደር ከመንግስት የጸጥታ ሃይል ውጪ መሳሪያ ይዞ መገኘት ተከለከለ፣ የተለያዩ ገደቦች ተጥለዋል

የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ክልከላዎችን አስቀመጠ። ኮማንድ ፖስቱ ፤ ክልከላው ” የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል ” የተቀመጠ መሆኑን ገልጿል።

የተቀመጡ ክልከላዎች ምንድናቸው ?

1. በከተማው ያሉ ማንኛውም መጠጥ ቤቶችና ጭፈራ ቤቶች እስከ ምሽቱ 3:00 ሰዓት ዉጭ አገልግሎት መስጠት ተከልክለዋል።

2. በከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለ 3 እግር ባጃጆች ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ዉጭ መንቀሳቀስ ተከልክለዋል።

3. ከተፈቀደለት የመንግስት የፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

4. ድምፅ አልባ መሳሪያዎችን ስለታማ የሆኑ እንደ ጩቤ ፣ ገጀራ ፣ አንካሴ ፣ ጦርና ፌሮ ብረት ወዘተ የመሳሰሉትን ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

5. በህግ የሚፈለጉ ወይም ተጠርጣሪዎችን ሽፋን የሰጠ ፣ የደበቀ ፣ የሀሰተኛ መረጃ ሰጥቶ ያሰመለጠ ፣ የፀጥታ ሀይሎችን የህግ ማስከበር ተልዕኮ ማደናቀፍ ማወክ በህግ ተከልክሏል።

6. በማንኛውም ቦታና ስዓት ጥይትም ሆነ ሮኬት ርችት መተኮስ በጥብቅ ተከልክሏል።

7. በተከለከሉ ቦታዎች በእምነት ተቋማት፣ በገቢያዎች፣ ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ፣ በሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶችና ግሮሰሪዎች፣ ልዩ ልዩ መዝናኛ ቦታዎች ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘትና መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

8. የሠራዊቱን ሚሊተሪ (አልባሳት) ከሰራዊቱ አባላት ውጭ መልበስ የተከለከለ ነው ፦

– የልዩ ኃይል ፣

– የፓሊስ ፣

– የመከላከያ ሠራዊት ፣

– የፌዴራል ፓሊስ ልብስ መልበስ በጥብቅ ተከልክሏል።

9. ያልተፈቀዱ ስብሰባዎችን ማለትም ያለ መንግስት እውቅና ውጭ ስብሰባ ማድረግ ፣ ወታደራዊ ስልጠና መስጠት ተከልክሏል።

10. አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ስራን ማስተጓጎል በጥብቅ ተከልክሏል።

11. የአማራን ህዝብ ከጥቃትና ከውርደት ለመታደግ መስዋትነት የከፈሉ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ከተለያየ አካባቢ ተነስተው ወደ ከተማው የመጡ በከተማው በተዘጋጀው ማረፊያዎች እንዲሰባሰቡ ማሳሰቢያ ተለልፏል። ከዚህ ውጭ በተናጠልም ሆነ በቡድን መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እና ጥይት መተኮስ ተከልክሏል።

12. ፀጉረ ልዉጥ/አጠራጣሪ ሰው ከቤቱ ያሳደረ ፣ያከራየ፣ በሆቴሉ አልጋ ያስያዙ እንዲሁም ለሚመለከተዉ የፀጥታ አካል ጥቆማ ያልሰጠ በህግ  ይጠየቃል።

መረጃው የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ነው።

Exit mobile version